2012-10-10 13:59:52

ብፁዕ አቡነ ሚካሊክ፣ ለተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ውህደት በጸሎት ተግቶ መንቃት


የፖላንድ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ሚካሊክ በበኩላቸውም ከቫትካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ የጉባኤው መርሃ ነገር እንደሚያመለክተውም “የአስፍሆተ ወንጌል አንኳር ከኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም ሰው ጋር መገናኘት” የሚል መሆኑ ያመለክታል፣ ስለዚህ RealAudioMP3 ሞትን አሸንፎ ከተነሳው ከክርስቶስ ጋር መገናኘት በጸሎት የተደገፈ በቅዱሳት ምሥጢራት የጸና ሲሆን ብቻ ነው የክርስትና እምነት ለማስተላለፍ የሚቻለው፣ ካሉ በኋላ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ወንጌል በእኛ ሕይወትና ለእኛ ሕይወት ያለው ክብር መመዘኛ ነው፣ ስለዚህ የተቀበልነውን ክርስትና ላይ ማስተንተን እጅግ ወሳኝ ነው። ልባችን በኢየሱስ ክርስቶፍ ፍቅር ካልተቀጣጠለ ኢየሱስ ክርስቶስ ለሌሎች ለማቅረብ እንዴት ይቻላልን፣ ከሕይወት ውጭ የምናቀርበው ኢየሱስ የሌሎችን ልብ ሊነካ ይችላል ብሎ ለመናገር ያዳግትታል በማለት አስፍሆተ ወንጌል የመንፈስ ቅዱስ ሥራ መሆኑ መዘንጋት የለበትም ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት እምነት የተጋረጠበት እክል ለካቶሊክ ቤተ ክርስትያን ብቻ ሳይሆን ለሌሎች አቢያት ክርስትያን ጭምር አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑ በፖላንድ ያለው ሁኔታ ጠቅሰው ካብራሩ በኋላ ይኽ ደግሞ ለአቢያተ ክርስትያን የጋራው ውይይት መረጋገጥ አቢይ ምክንያት ነው። በቅርቡ የሞስኮና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ርክስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ኪሪሊ በፖላንድ ባካሄዱት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት በፖላንድ ከምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጋር የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸው ጠቅሰው፣ ይኽም በጋራ ለአስፍሆተ ወንጌል ተልእኮ ለመተባበር እምነት የተጋረጠበት ወቅታዊው እክል ለመቅረፍ ለመተባበር የደረሱት ስምምነት ነው። በማኅበራዊና በቤትሰብ እንዲሁም በግል ሕይወት የእግዚአብሔር ሕልውና ግልጽ ለማድረግ የሚል ዓላማ ያለው መሆኑ አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.