2012-10-10 13:56:55

ሲኖዶስ፦ ብፁዕ አቡነ ላሃም፣ በሶሪያ እርቅ እንዲሰፍን የሁሉም ድጋፍ አስፈላጊነት


በዚህ በአገረ ቫቲካን በመካሄድ ላይ ባለው የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በመሳተፍ ላይ የሚገኙት በደማስቆ ለምትገኘው የመልኪታ ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ሶስተኛ ላሃም ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ በቅድሚያ የሲኖዶስ RealAudioMP3 ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኤተሮቪችና መላ የሲኖዶስ ብፁዓን አበው ሶሪያን በማስታወሳቸው አመስግነው፣ በሶሪያ ተከስቶ ያለው ውጥረት ሶሪያ ብቻ የሚመለከት ሳይሆን፣ መላ መካከለኛው ምስራቅ የሚመለከት ጉዳይ ነው። በተለይ ደግሞ ሶሪያ ሊባኖስ ዮርዳኖስ ፍልስጥኤምና እስራኤልን ጠቅሰው፣ የሶሪያ ውጥረት እነዚህ አምስቱ አገሮች በቀጥታ የሚመለከት ችግርና የሁሉም የተለያዩ ሃይማኖቶች ሰላማዊው የጋራው ኑሮ የሚነካ አቢይ ችግር ነው ስለዚህ ሶሪያዊ ችግር አድርጎ ብቻ መመልከት ስህተት ነው ብለዋል።
በሶሪያ ተከስቶ ያለው ውጥረት እንዲወገድ በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሶሪያ ባህላዊ ታሪካዊ ሃይማኖታዊ ማኅበራዊና ሰብአዊ ሃብት ማዳን ላይ ያተኮረ ለሰላማዊ ውይይት እማኔ የሚል የሰላም ጥሪ በማቅረብ ላይ ትገኛለች፣ ኢየሱስ በፍልስጥኤም ክርስትና በሶሪያ ነው የተወለደው፣ ስለዚህ የመላ ዓለም ማኅበረ ክርስትያን ከነዚህ አገሮችና ከዚህ የመካከለኛው ምሥራቅ ክልል ጋር ያለው ትሥሥር ግልጽ ነው። የሶሪያው ችግር የሁሉም ችግር መሆኑ ለመረዳቱም አያዳግትም ካሉ በኋላ፣ “እርቅ በሶሪያ በጠቅላላ ለመካከለኛው ምስራቅ ሰላም መረጋገጥ ብቸኛው መንገድ ነው” በሚል ርእስ ሥር ለሲኖዶስ ያሰሙት ንግግር ጠቅሰው፣ “ሶሪያ ለእርቅ መደገፍ ምዕራቡ ዓለም ከምስልምና ሃይማኖት ጋር ለሚያካሂደው ውይይት መደገፍ” ማለት ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.