2012-10-10 13:54:20

ሲኖዶስ፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል መፈክር ብቻ ሆኖ እንዳይቀር


በአገረ ቫቲካን የሲኖዶስ የጉባኤ አደራሽ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በተገኙበት 142 የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት በማሳተፍ እየተካሄደ ያለው ሲኖዶስ በትላትና ጧት ውሎው፣ በሶሪያ ሰላም እንዲረጋገጥ በአንድ ድምጽ የሰላም ጥሪ፣ ለስደተኞች አቢይ ግምት እንዲሰጥና ቤተ ክርስትያን እምነት በመኖር RealAudioMP3 ረገድ የገዛ እራሷ ህሊና ትመረምር ዘንድ አስተንትኖና ሃሳብ የቀረበበት እንደነበር የገለጡት የራዲዮ ቫቲካን ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ፒሮ ቀጥለውም፣ የሲኖዶስ ከቀትር በኃላ ውሎው፣ የብፁዓን ጳጳሳት ጉዳይ ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል ኦሌት ለተጋባእያኑ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2008 ዓ.ም. የእግዚአብሔር ቃል ርእስ ዙሪያ የተወያየው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍጻሜ Verbum Domini-ቃለ እግዚአብሔር በሚል ርእስ ሥር የደረሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያው ምዕዳን በዓለም እንዴት ባለ መልኩ ግንዛቤ እንደተሰጠው ላይ ያተኮረ ንግግር ማቅረባቸው አስታውቀዋል።
የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ያለው የሶሪያ ወቅታዊው ሁኔታ በመጥቀስም ለአገሪቱ የሰላም ጥሪ በማቅረብ፣ መረጋገት ይረጋገጥም ዘንድ ሁሉ ስለ ሶሪያ ሰላም መረጋገጥ እንዲጸልይ በመማጸን ወደ የሲኖዶሱ ዋና ርእሰ ጉዳይ በመግባት፣ ለስደተኞች ተገቢ ግምት እንዲሰጥ በተለይ ደግሞ ስደተኞው ያላው የባህል የእምነት ሃብት በተስተናገደበት አገር አስፈላጊ ትኵረት እንዲያገኝና ብዙውን ጊዜ የአስፍሆተ ወንጌል ቀዳሚ ተወናያን ሆኖ እንደሚገኝም የሲኖዶስ አበው በማረጋገጥ፣ አለ ምንም አድልዎና ተጽእኖ ሰብአዊ መብቱ ተከብሮለት መለያው ለማቀብ ይችል ዘንድ መደገፍ አስፈላጊ መሆኑ ተሰምሮበታል።
በመቀጠልም ቤተ ክርስትያን እምነት የመኖሩ ጥሪዋ በተመለከተም፣ የቅዱሳት ምሥጢራት ሕይወቷ ቢሮክራሲያዊ ከማድረጉ ታማኝነቷ ከሚያዳክመው እክል፣ እምነት በሚኖር ህይወት ለማስወገድ ትችል ዘንድ ለመደገፍ የኅሊና ምርመራ ታደርግ ዘንድ ሲኖዶስ በማሳሰብ የቃለ ወንጌል ሰባኪ ከመሆን በፊት በቃለ ወንጌል መሰበክ አስፈላጊ መሆኑ ከተስተዋለ በኋላ፣ በተለያየ ሥፍራ በቀውስ ላይ የሚገኘው የንስሐ ምሥጢር፣ አቅቦና አክብሮ የመኖር ክርስትያናዊ ጥሪ በማነቃቃቱ ረገድ ቤተ ክርስትያን ትተጋ ዘንድ በውስጠ ቤተ ክርስትያናዊ ውይይቶች ሳትዘጋ በትህትና በሚሠዋ ፍቅር አማካኝነት ወንጌል ለማቅረብ በልኡክነት ጥሪ መትጋት እንዳለባት ያሳሰበው ሲኖድስ አክሎ፣ በውሉደ ክህነት አባላት የሚፈጸመው እንቅፋት ከወዲሁ ለመቆጣጠር እንዳይኖርም ለማድረግም ለውሉደ ክህነት ለቤተሰብም የተሟላ ተገቢ ሕንጸት አንገብጋቢ መሆኑ በማብራራት፣ ካለ ተገቢ ሕንጸት ሰባኪ ወይንም የእግዚአብሔር ቃል አብሣሪ ለመሆን እንደማችል አበክሮ አሳስበዋል።
ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ሂደት መፋጠንና መረጋገጥ በቅድሚያ ከዛለውና ከማያሳትፈው ሐዋርያው ግብረ ኖልዎ ተላቆ ጽኑና የሚያሳትፍ ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ማቅረብና ካህናት በጋለ ስሜትና ሕይወት አዲስ ዜና ለማበሰር እንዲችሉ፣ ቀጣይነት ያለው የተልእኮ ወንጌል ሕንጸት እንደሚያሻቸው በዚሁ ጉዳይ ላይ በማተኮርም መላውን ዓለም ለመንፈስ ቅዱስ ጥበቃ በማቅረብ ልክ እንደ ማርያም የስብከተ ወንጌል ቀዳሜ አርአያ፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ውበት የአስፍሆተ ወንጌል መገልገያ የመሆን ጥሪው ማነቃቃትና በእምነትና በሥነ ጥበብ መካከል ውይይት አስፈላጊ መሆኑ የጠቀሱት ብፁዓን የሲኖዶስ አበው አያይዘውም ልክ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ብፁዓን ጳጳሳት ያነቃቁት የተረገዘው ሕፃን የመባረክ ሥነ ሥርዓት በሁሉም አገሮች ብፁዓን ጳጳሳት ዘንድ ሊተገበር የሚገባው መልካም አርአያ መሆኑ ጠቅሰው፣ ይኽ ደግሞ ቤተሰቦች ወደ ቤተ ክርስትያን ለማቅረቡ ዓላማ አቢይ ድጋፍ ነው ካሉ በኋላ፣ የመከላከያ ኃይሎች የሰላም መሣሪያ ለመሆንና ለመላ ሰው ዘር ጥቅም መረጋገጥ አገልግሎት የተጠሩ በመሆናቸውም ምክንያት ከዚህ አንጻር ካለባቸው ኃላፊነት ጋር የሚስተካከል ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት ማግኘት እንደሚኖርባቸው ብፁዓን አበው አሳስበዋል።
ብፁዓን የሲኖዶስ አበው በመቀጠልም፣ በሲኖዶስ በታዛቢነት በመሳተፍ ላይ ከሚገኙት ውስጥ የሉተራን ቤተ ክርስትያን አባል ወንድም ሲሞ ፐኡራና የአመሪካ የቅዱስ መጽሓፍ ማኅበር ሊቀ መንበር ዶክተር ላማር ቨስት ንግግር ያደመጡ ሲሆን፣ ሲሞ ፐኡራ ምሥጢረ ጥምቀትና የቤተ ክርስትያን ወንጌላዊ ልኡክነት በሚል ርእስ ዙሪያ ባሰሙት ንግግር፦ ክርስቶስን ፍትህ በማነቃቃት መመስከር ያለው አስፈላጊነት ሲያመለክቱ፣ ዶክተር ላማር ቨስት በበኵላቸውም ባሰሙት ንግግር፦ በዓለም ዝግመተ ለውጥ ያለ ቢሆንም ቅሉ ቅዱስ መጽሓፍ የማይለወጥ ዘወትር አዲስ” መሆኑ ገልጠው፣ የማይሻረውና የማይለወጠው የእግዚአብሔር ቃል ብቻ ነው” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታወቁ።
የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ከቀትር በኋላ ባካሄደው ጉባኤ፣ ከአምስቱ ክፍለ ዓለም የተወጣጡ ብፁዓን ጳጳሳትን ወክለው ባስደመጡት ንንግ ላይ በማተኮር ቀጥሎ መዋሉ ሲገለጥ፣ ንግግር ያሰሙት ብፁዓን ጳጳሳት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል በክልላዊና በሰበካ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሚሰጠው ግንዛቤና ዓለማዊነት ትሥሥር በአገሮችና በአካባቢዎች ማኅበራዊ ሰብአዊና ቤተ ሰብአዊ ተጨባጭ ጉዳይ ላይ እያስከተለው ያለው ለውጥ የለየ የዓለማዊ ትሥሥር ተጋርጦ ላይ ያተኮረ እንደነበር የገለጡት ልእክት ጋዜጥኛ ፒሮ አያይዘውም፣ እስያ በጋራው ውይይት አፍሪካ ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ አፍሪካውያን የአፍሪካ ልኡካነ ወንጌል እንዲሆኑ ባሉት ጥሪ ላይ በማተኮር በክፍለ ዓለሚቱ እየተስፋፋ ያለው የሙስሊሞች አክራሪነት በጽናትና እምነትን በመመስከር ለመጋፈጥ፣ ኤውሮጳ ክርስትያናዊ ተዘክሮዋ መዳከም የሚታይባት ቢሆንም በውስጧ የሚከሰቱት አወንታዊ የቤተ ክርስትያን ክንዋኔዎች በመጥቀስ፣ በዚህ የመገናኛ ብዙሃን እጅግ ተጽእኖ ያደረበት ማኅበረሰብ የሚኖርባት ክፍለ ዓለም፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ክርስትያናዊ ግብረ ገብ ማነቃቃትና ቃልና ሕይወት ያጣመረ ምስክርነት ወሳኝ መሆኑና እንዱሁም ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መረጋገጥና በክልሉ የምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የምትኖረውና ምእመናኖችዋ ውሉደ ክህነት የሚመሰክሩት እምነት ላይ የሚያስተነትንና ዓለማውያን ምእመና የአስፍሆተ ወንጌል ተወናያን መሆን እንደሚጠበቅባቸው በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ እንደነበርም ተገልጠዋል።
በመጨረሻው የኦቻይና ክልል ቤተ ክርስትያን አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ከወጣቱ ትውልድ መጀመር በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ በጠቅላላ በክፍለ ዓለሚቱ ያሉት ማኅበራዊ ባህላዊ እና ጎሳዊ ተጨባጭ ጉዳዮች ግምት የሰጠ መሆን እንዳለበት ክፍለ ዓለሚቱን ወክለው ንግግር ያስደመጡት የሲኖዶስ አበው እንዳመለከቱ ልእክት ጋዜጠኛ ፒሮ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.