2012-10-09 09:52:35

13ኛው መደበኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ ጉባኤ


13ኛው መደበኛ የጳጳሳት ሲኖዶስ አጠቃላይ ጉባኤ ዛሬ ጥዋት በጳውሎስ 6ኛ አደባባይ በ262 አበውና ከተለያዩ አብያተ ክርስትያናት የተጠሩ ተወካዮችና ሊቃውንት በተገኙበት በቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ መሪነት ዛሬ ጥዋት ስብሰባውን ጀመረ፣ ስብሰባውን በጸሎት የከፈቱት ቅዱስነታቸው ሲሆን በሥርዓተ ጸሎቱ ስብሐተ ነግህና መዝሙራተ ዳዊት በላቲን ቋንቋ ከተዜሙ በኋላ ቅዱስነታቸው እትአመን የሚለው የጸሎተ ሃይማኖት መግለጫና ፍቅርን እንደ የአዲስ ስብከተ ወንጌል መነሻ ማእከል ያደረገ ጥልቅ ስብከት አቅርበዋል፣
በቤተ ክርስትያን የሚሠራው እግዚአብሔር መሆኑን በልባችን የምናምን ከሆነና ክርስቶስን ለመላው ዓለም ለማሳወቅ የሚያቃጥል ፍላጎት ያለን እንደሆነ ብቻ ነው ሰባክ ያነ ወንጌል ለመሆን የምንችለው ሲሉ ስብከታቸውን የጀመሩ ቅድስነታቸው በብዙ ሰዎች ልብ ሆኖ የሚያስቸግር ጥያቄ እንዳለና ጥያቄውም በቤተልሔም ግርግም የተወለደው ሕጻን የሰው ልጅ ታሪክን በስደትና በግድየለሽነት ተከቦ ሳለ የለወጠው አሁንም ከሁለት ሺ ዓመታት በኋላ እግዚአብሔር ማን ነው ከሰው ልጆችስ ምን ያገናኘዋል የሚሉና የሚመስልዋቸው መሆናቸውን እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል “ከሰማዩ ጸጥታ ወዲያ ከሰው ልጅ ታሪክ ደመናዎች ወዲያ እግዚአብሔር አለ ወይስ የለም፧ ካለስ ይህ እግዚአብሔር ያውቀናልን ከእኛ የሚያገናኘውስ ምን ይሆን፧ ይህ እግዚአብሔር በጎ ነው ለመሆኑ በጎ ነገር በዓለማችን ሥልጣን አለው ወይስ የለውም፧ ይህ ጥያቄ ዛሬም እንደ መጀመርያው ዘመናዊ ነው፣ ብዙዎች እግዚብሔር የሚለው ቃል አሳብ ብቻ ነው ወይስ በእውነት አለ፧ እንታድያ ለምን አይሰማም ብለው ይጠይቃሉ ሲሉ ከጠየቁ በኋላ ወደ መሠረታዊው ቃል ወንጌል ትርጉሜ መለስ በማለት ቃሉ እጅግ ጥንታዊ ሆኖ ዋነኛው ትርጕሙ ዜና ሠናየ የምሥራች ዜና ነው፣ በጥንታዊው ግሪካዊ ጸሓፊ ሆመር ተጠቅሶ እናገኘዋለን ትርጉምም የድል ዜና ሲሆን በሁለተኛው ኢሳያስም በብሉይ ኪዳን እናገኘዋልን ትርጉምም የእግዚብሔር ደስታ የሚያበስር የምሥራች ድምጽ፤ ምሥራቹም የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ እንኳን የእግዚአብሔር ዝምታ የሰው ዝም ማለትም ከባድ ነው፣ አዳምና ሔዋንን ከገነት ካባረረ ወዲህ ጌታ ጌታ ለረዥም ግዜ ዝም ካለ በኋላ አልፎ አልፎ በአበው ካልሆነ በቀር በአካል አልተናገረም፣ ዝምታው እጅግ ከባድና ረዥም ነበር፣ ወንጌል ማለት እግዚአብሔር ሕዝቡን አልረሳም፣ ተናገረ የደስታ ድምጽ ተሰማ ማለት ነው፣ ጊዜው በደረሰ ጊዜም ቃሉ ሥጋ ሆነ፣ በታላቅ ጩኸትም ተናገረ፣ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ድህነትም መጣ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር ዝምታውን አደፈረሰው እግዚብሔር ተናገረ እግዚአብሔር አለ ያውቀናል ያፈቅረናልም በታሪካችን ገባ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ቃሉ ነው፣ እርሱም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆኖ እግዚአብሔር እንደሚያፈቅረን ለእኛ ሲል እስከ ሞት እንደደረሰና ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፣ ይህንን ለመቀበል ከእኛ የሚያስፈልገው ምን ይሆን ምንስ እናድርግ፣ የምሥራች ቃል ሰሚ ያስፈልገዋል፣ የእኛ ሥራ ማዳመጥ ነው፣ ሥራውን የሚያደርገው እግዚአብሔር ስለሆነ እኛ የምናደርገው ምንም የለም መቀበል ብቻ ነው፣ የሚያገርና የሚያድን እርሱ ብቻ ነው፣ ሐዋርያትም ይህንን ነው ያደረጉት፣ በመጽሓፈ ሰዓታት በ9ኛው ሰዓት በሚደገመው ጸሎት እንደ በጰራቅሊጦስ ለእኛም መንፈስ ቅዱስ ላክልን ይላል፣ ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ያደረጉት በጸሎት መጠባበቅ ነው፣ በመጨረሻም መንፈስ ቅዱስ ተቀበሉ፣ እኛም እንደዛው ለአዲስ ስብከተ ወንጌል ስንዘጋጅ እግዚአብሔር ሊናገረን መንፈስ ቅዱስ እንዲያበራልን በጸሎት መጠባበቅ አለበን፣
እግዚአብሔር ተናግረዋል፣ ይህ ኃላፊ አንቀጽ ቢመስልም በእግዚአብሔር ኃላፊና ትንቢት ስለሌለና ዘለዓለማዊ ስለሆነ አሁንም ይናገራል ሁሌ ይናገራል፣ እርሱ እንዲመራን እኛም እንድንከተለው ረጋ እንበል፣ ስብከተ ወንጌልም ይህ ነው፣ ሁሉን የሚጀምረው መንፈስ ቅዱስ ለመላክ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው፣ የእኛ ተግባር ከእርሱ መተባበር ነው፣ ብለው እግዚብሔር እየተናገርን መሆኑን ግለጠዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘውም እላይ በተጠቀሰው ጸሎት ሌሎች ሁለት ቃላት እትአመን ኮፈስዮ የሚለውን እና የፍቅር ሥራ ካሪታ የሚለውን ቃላት እንደ የአዲስ ስብከተ ወንጌል አእማድ በመውሰድ አንድ ባንድ በመዘርዘር፣ እትአመን የሚለው ይዘት እንዳለው ይህም የእግዚአብሔር መገለጥ በምሥጢረ ሥጋዌና ምሥጢረ ፋሲካ በመካከላችን መገኘት ሲሆን ይህ ኮንፈስዮ የሚለው የእምነት ቃል ከክርስትና በፊት ፕሮፈስዮ ማለትም ቃል መስጠት ሆኖ በፍርድ ቤት የሚዘወተር እንደነበረና በክርስትና ግን በኮንፈስዮ ተተክቶ ሰማዕትነትንና ምስክርነትን መተማመንን እንዳጠቃለለ አመልክተዋል፣ ሰማዕትነት ማለት ሕይወትን ለመስጠት ደምን ለማፍሰስ ዝግጁ መሆን ሥቃይን ለመቀበልን እስከ ሞት ታማኝ መሆን ማለት ነው፣
ቅዱስ መጽሐፍ እምነት በልብና በአፍ እንደሚገኝ ይናገራል፤ ሆኖም ግን ለምስክርነት ለሕዝብ ይፋ መውጣት አልበት፣ ለባውያን ፍጡራን ስለሆንን አ እምሮ አችን ሊያሰላስለውና ሊቀበለው እንዲያው ሕዋሶቻችንን መሙላት አለበት፣ ስለዚህ እትአመን ኮንፈስዮ ሁሉን ያጠቃልላል፣
ሁለተኛው ቃል ፍቅር ነው፣ ፍቅር እምነትን እውን የሚያደርግ እተግባር ላይ የሚያውል መለኮታዊ ኃይል ነው፣ እንዲያው እንደ እሳት ነው፣ መቀጣጠል አለበት፣ ኢየሱስም እሳቱን ሊያቀጣጥል እንደመጣ ይናገራል፣ ሉቃስ ወንጌላዊም የጴንጠቈስጤን ሁኔታ ሲገልጥ መንፈስ ቅዱስ በሓዋርያት ላይ እንደ እሳት ላይ ላያቸው እንደወረደ ይገልጣል፣ እሳት ያሞቃል፣ ይደመስ ሳልም የፍቅር እሳት ግን ያሳድሳል ያሞቃል ወደ ጓደኛም ይሸጋገራል፣ ሲሉ ዋነኛው የስብከተ ወንጌል መነሻ ራሱ እግዚአብሔር መሆኑንና ለስብከተ ወንጌል ዝግጁ ለመሆን መጀመርያ እኛው ራሳችን መሰበክ እንዳለብን ይህም እት አመን ብሎ መመስከር ለሰማዕትነት ዝግጁ መሆን በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ እንደሐዋርያ በጸሎት መጠባበቅ እንዳለብን አሳስበዋል፣

ቅዱስነታቸው ከስብከት በኋላ የስብሐተ ነግሁ ጸሎት መዝጊያ ቡራኬ ሰጥተው ጉባኤው ተጀመረ፣ ከዚህ በመቀጠል ቅዱስነታቸውን ወክለው የሲኖዶሱ ሊቀመንበር የሆንግ ኮንግ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ጆን ቶንግ ሆን ናቸው፤ ብፁዕነታቸው ለቅዱስ አባታችንና ለሲኖድስ አባቶችና ለእንግዶች ሰላምታ አቅርበው ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል ሶስት ነጥቦች እንደሚያስፈልጉ እነዚህም ከእግዚአብሔርና ከሰው ልጆች ጋር መወሃሃድ ራስን መስዋዕት እስከ ማድረግ የላቀ አገልግሎት ማበርከት እና ትምህርተ ሃይማኖት መሆናቸውን በማመልከት የእምነታችን ቀናተኛ መስካሪዎች መሆን አለብን ሲሉ ንግግራቸውን ደምድመዋል፣ ከብፁዕነታቸው በኋላ መድረኩን የተረከቡ የሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች ናቸው፣ ብፁዕነታቸው ስለሲኖዶሱ ጉዞ እና ከተጠነሰሰበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን ምን እንደተደረገ በሰፊው ለጉባኤው ሪፖርት አቅርበዋል፣
ብፁዕ አቡነ ኒኮላ ኤተሮቪች የሲኖዶሱ መግቢያ ሲያቀርቡ በወንጌለ ማርቆስ ፍጻሜ ላይ የምናገኘው ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ሐዋርያትን “ወደ መላው ዓለም ሂዱ ወንጌልን ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ” (ማር 16፤15) በማለት የቤተ ክርስትያን ተልእኮ ይጀምራል፣ በዚህም ቤተ ክርስትያን ወንጌል ለመስበክ እንደተፈጠረችና ለዚህም እንደምትኖር ገልጠዋል፣
ይህንን ሲኖዶስ ለማዘጋጀት ቀላል እንዳልነበረና ብዙ እንደተሠራ በመንፈዊ ጐን ጸሎትና አስተንትኖ በንባበ መለኮታዊ ጎን ብዙ ጥናትና ምርምር በተክኒካዊ በአዘገጃጀት በኩልም ብዙ ውጣ ውረድ እንዳለፈ ገልጠዋል፣ ከብዙ ጥረት እና ስብሰባዎችና መመካከር በኋላ መጋቢት 4 ቀን 2011 ዓም ሊነያመንታ ወይም መመርያ ጥያዌዎችና አስተያየት መሰብሰብያ ቅጾች ተዘርግተዋል ኅዳር 1 ቀን 2011 ዓም 90.5% የመላው ዓለም ካቶሊካውያን አብያተ ክርስትያን መልስ የሰጡ ሲሆን የሲኖዶሱ የአጠቃላይ ጽሕፈት ቤት ሁሉ አጣርቶ ለቅዱስ አባታችን አቅርቦ በሰኔ ወር 19 ቀን 2012 ዓም የመሥርያ ሰንዱ ኢንስትሩመንቱም ላቦሪስ እንደቀረበ ገልጠዋል፣
የሲኖዶሱ ርእስ “እምነት ለማስተላለፍ አዲስ ስብከተ ወንጌል” ሆኖ ሲኖዶሱ ከዛሬ እስከ ጥቅምት 28 ቀን እንደሚዘልቅ ከተወሰነ በኋላ ከብዙ ውጣ ውረድ እነሆን ዛሬ እዚህ ተገኝተናል ካሉ በኋላ በሲኖዶሱ 262 የሲኖዶስ አባቶች ይሳተፋሉ፣ የአባቶቹ ብዛት ከዛሬ በፊት ከተደረጉ ሲኖዶሶች ከፍ ያለ ነው ይህም ሲኖዶሱ ምንኛ ያህል አስፈላጊ መሆኑን ያመልክታል፣ ከኤውሮጳ 103 ከአመሪካ 63 ከአፍሪቃ 50 ከኤስያ 39 ደግሞ ከኦሽያንያ ይሳተፋሉ፣ በተጨማሪም 45 ሊቃውንትና 49 ታዛቢዎች እንደሚሳተፉ ገልጠዋል፣ በሌላ በኩል ደግሞ እኅቶች ከሆኑ 13 አብያተ ክርስትያን ተውካዮቻቸውን እንደላኩ ከእነዚህ የካንተርበርይ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊልያምስ እፊታችን ጥቅምት 10 ንግግር እንደሚያደርጉ ኤኩመኒካዊው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ በርተለሜዎስ አንደኛም ጥቅምት 11 ቀን በሚያርገው የእምነት ዓመት መክፈቻ መሥዋዕተ ቅዳሴ ተገኝተው ከቅዱስነታቸው ጋር እንደሚጸልዩና ልዩ ሰላምታ እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል፣ የሂላርዮን ሞስኮ ፓትርያርክ ሕዝባዊ ግኑኝነት ኃላፊም ቤተ ክርስትያናቸውን ወክለው በሲኖዶስ እየተሳተፉ መሆናቸው እንዲሁም የዓለም አቀፍ መቶዲስት ምክትል ሊቀ መንበር ሳራ ዳቪስ እየተሳተፉ ናቸው፣ ሌሎች ሶስት ለየት ያሉ ል ኡካን እንዳሉም ግለጠዋል አንደኛው የተዘ ማኅበረ ክርስትያን ኃላፊ አልዋ ሲሆኑ የወጣቶች ስብከተ ወንጌል በሚመለከት ንግግር እንደሚያደርጉ ሁለተኛ የአመሪካ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር ሊቀ መንበር ላማር ቨስት ናቸው፣ ሶስተኛው ደግሞ የጳጳሳዊ ሳይንስ አካዳማኢ ሊቀመንበር ቨርነር አርበነር የፕሮተስታንት አባልና በ1978 ዓም የመድኃኒት ኖቤል ሽልማት የተቀበሉ ናቸው፣ ቨርነር ጥቅምት 12 ቀን በሳይንስና በእምነት መካከል ስላለው ግኑኝነት ንግግር እንደሚያደርጉም አመልከተዋል፣
ሲኖዶሱ ሲካሄድ ለማኅበራዊ ብዙሓን መገናኛ በተለያዩ ቋንቋዎች መግለጫ የሚሰጡ 5 ጋዜጠኞች ተዘጋጅተዋል፣ ከዛሬ ጥቅምት 8 ቀን ሐሙስ ጥቅምት 18 ቀን አርብ ጥቅምት 26 ቀን እና ቅዳሜ ጥቅምት 27 በስተቀር ይህ ቡድን ጋዜጠኞችን በየቀኑ ያገኝዋቸውል፣ የሲኖዶሱ አባቶች በ32 ረዳቶች እና በ30 ተርጓሚዎች ሊታገዙ ናቸው፣ ባጠቃላይ በዚሁ መደበኛ አጠቃላይ ጉባኤ ከ400 ሰዎች ይሳተፋሉ፣ሲሉ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.