2012-10-08 14:38:48

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “ሲኖዶስና አጽምዖት”


“አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ክርስትና እምነት ለማስፋት” በሚል ርእሰ ሥር የተመራው ትላትና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በይፋ ያስጀመሩት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ለቤተ ክርስትያን አቢይ ጸጋ መሆኑ ሲኖዶስና አጽምዖት በሚል ርእስ ሥር የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል RealAudioMP3 ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በሳምንት ማብቂያ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል፣ የመላ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ውሳኔ መሠረት በሮማ ጳጳስ ዙሪያ በሃገረ ቫቲካን “ጌታ የቤተ ክርስትያን ሕይወት በተገባና በትክክለኛው መንገድ እርምጃዋን በማስቀጠል የእርሱ መንፈስ የሚናገረውንና እርሱ የሚሰጠው ሃሳብ በማዳመጥ በጋራ ለመጓዝ” በጋራ በመገናኘት፣ ለመናገርና ለመወይየት ብቻ ሳይሆን ለመዳመጥም ጭምር መሆኑ፦ “እግዚአብሔር በጋራ ለማዳመጥ እንዱ ጳጳሳ የሌላው ልምድና ገጠመኝ የሚያስተውልበት፣ በእምነት ቋንቋ የሚወያዩበት ልብና ጆሮ የሚሰጣጡበት በጠቅላላ ካቶሊካዊነት የሚስተጋባበት ቅዱስ ጉባኤ እንደሚኖሩ” ገልጠዋል።
ልክ በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንደታየው “ቅዱስ ማዳመጥ የሚስተጋባበት፣ የመላ ካቶሊካዊት ብፁዓን ጳጳሳት ከሮማ ጳጳስ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ጋር ያላቸው ውህደትና አንድነት የሚመሰክሩበትና ቅዱስነታቸ ለሚያነቃቁት የቅድስት ቤተ ክርስትያን ተልእኮ ታዛዥነታቸውን የሚመስክሩበት ቅዱስ ጉባኤ ነው” ብለዋል።
የዚህ ትላትና በይፋ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ተጀምሮ ያለው ሲኖዶስ ዋና ርእስ፦ “አስፍሆተ ወንጌል የክርስትያን እምነት ለማስተላለፍ” የሚል መሆኑ አባ ሎምባርዲ በርእሰ ዓንቀጹ ጠቅሰው፣ ይህ ርእስ የአሕዛብ ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ በጻፋት መልእክት ምዕ. 9 ቁ. 16 “የምሥራቹን ቃል ማብሠር ግዴታዬ ስለሆነ የምመካበት ነገር አይደለም፣ እንዲያውም የምሥራቹን ቃል ሳላበስር ብቀር ውዮልኝ” ሲል በጥልቅ ስሜት የገለጠው የክርስትና እምነት የማስፋፋቱ ክርትስያናዊ ኃላፊነት ላይ ያነጣጠረ ነው። ለሚቀጥሉት ሦስት ሳምንታት ብፁዓን ጳጳሳት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያለን እውቀትና እርሱን በመከተል የምንኖረው ክርስትያናዊ ሕይወት አማካኝነት የድኅነት መልእክት ትላትና ዛሬ ነገ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲመጣ እምነት በዚህች ምድር እንዲያገኝ በሚለው መንፈሳዊነት ዙሪያ እንደሚወያዩ ገልጠው፣ ብፁዓና አበው እርስ በእርሳቸው ለሚደማመጡበትና መንፈስ ቅዱስ ለሚያዳምጡበት ሲኖዶስ እንጸልይ በማለት ርእሰ ዓንቀጹን አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.