2012-10-08 14:34:19

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ትላትና ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ 13ኛው መደበኛው የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በይፋ ከፈቱ


“አዲስ አስፍሆተ ወንጌል የክርስትና እምነት ለማስተላለፍ” በሚል ርእስ ዙሪያ እንዲወያይ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2012 ዓ.ም. እንዲካሄድ የጠሩት 13ኛው መደበኛው ጠቅላይ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. በአጸደ ቅዱስ ጴጥሮስ RealAudioMP3 በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በይፋ በማስጀመር፣ የጠሩት ሲኖዶስ፦ በእያንዳንዱ የሰው ልጅ ሕይወት ተስፋ የሚያሰጠው እምንት ዳግመ ግኝት ለመለየትና አመች ሁኔታ ለመፍጠር” ያለመ መሆኑ ባሰሙት ስብከት ገልጠው አክለውም በአሁኑ ወቅት በኅብረተሰብ ዘንድ አቢይ ቀውስ እያጋጠው ያለው ምሥጢረ ተክሊልና ኵላዊ የቅድስትና ጥሪ አኗኗር ላይ በማቶከር የምሥጢረ ተክሊል ክብር በማብራራት እቃቤ እንደሚያሻው ገልጠው፣ ቤተ ሰብ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ተቀዳሚ ተወናያን ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ትላትና የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በይፋ ለማስጀመር በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለቅድስት ኢልደግራዳ ዘ ቢንገንና ለቅዱስ ዮሐንስ ዘአቪላ በይፋ የቤተ ክርስትያን ሊቅነት እንዳወጁላቸውም ሲታወቅ፣ መሥዋዕተ ቅዳሴ የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ፒሮ ካጠናቀሩት ዘገብ ለመረዳት እንደተቻለው፦ “አስፍሆተ ወንጌል ወንጌልን በማንኛው ጊዜና ሥፍራ አንኳር መልእክቱና ፍጻሜው የፍቅርና የሰላም ምልእክት የመለወጥና የእርቅ ጥሪ የሚያቀርብ መለያውም ስቁል ኢየሱስ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ የሚያበሥር ነው” ብለዋል።
ቅሱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የዚህ የጠሩት ሲኖዳዊ ጉባኤ ትርጉም ሲያብራሩ፦ “ይህ አዲስ እስፍሆተ ወንጌል ላይ በማተኮር የሚካሄደው የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ምሥጢረ ጥምቀት ተቀብለው ነገር ግን ከቤተ ክርስትያን ርቀው አለ ክርስትና ተግባር የሚኖሩት ላይ ያነጣጠረ” መሆኑ ገልጠው፣ “እነዚህ የቤተ ክርስትያን ልጆች ዳግም ከዚያ ለኅልውናችን ጥቅል ትርጉም የሚሰጥና የኅልውና ትርጉምና ሰላማችን ከሆነው ከክርስቶስ ጋር በአዲስ መንፈስ ለመገናኘት እንዲችሉ የጸጋ ምንጭ የሆነው በግል በቤተሰብና በማኅበራዊ ሕይወት እውነተኛ ኃሴትና ተስፋ የሚሰጠው እምነት ዳግም ለማግኘት የሚችሉበት መንገድ ለማመላከት ነው” እንዳሉ ጋዜጠኛ ፒሮ እስታወቁ።
ቅዱስ አባታችን የእለቱ የወንጌል ምንባብ ጠቅሰውም፦ “እግዚአብሔር በሙሉ ኃይል በርቱዕ አንደበት እንደሚናገር የሚያረጋግጥ ምልክት የሆነው በአሁኑ ወቅት በተለያየ ምክንያት ለአደጋ ተጋልጦ የሚገኘው በአንድ ወንድና በአንድ ሴት መካከል የሚጸናው ውህደት በሚሰዋ፣ ፍርያማና ፈጽሞ የማይሻር በሆነ ፍቅር ‘አንድ አካል’ የሚያደርገው ምሥጢረ ተክሊል፣ ከእምነት ጋር የተቆራኘ ነው። ስለዚህ የእምነት ቀውስ ለምሥጢረ ተክሊል ቀውስ መሠረት ነው። ቤተ ክርስትያን ከጥንት ጀምራ እንደምታስተምረውም ምሥጢረ ተክሊል ላይ የጸናው ጋብቻ የአስፍሆተ ወንጌል ተቀባይ አካል ሳይሆን ባለ ቤት ጭምር ነው። እንዳሉ የገለጡት ጋዜጠኛ ፒሮ አያይዘውም፦ “ቅድስና ባህላዊ የማኅበራዊ ፖለቲካዊ ሃይማኖታዊ ልዩነት የማይመለከተው ልሳኑም ለሁሉም ግልጽ የሆነ የአዲስ ሕይወት ምንጭ ወደ ሆነው ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚያቀርብ አዲስ ዜና ፍቅርና እውነት የሚል ነው” እንዳሉ አስምረውበታል።
“በቅድስና ጥሪ የሚገለጠው የክርስትና ሕይወት ተጨባጭ እይታው፣ ፍጹምነት የሌለው የክርስትያን ሕይወት በትህትና በመመልከት ለአስፍሆተ ወንጌል እንቅፋት የሆነውን ግላዊና ማኅበራዊ ግድፈቶችን የእዝግዚአብሔር ሁሉን ቻይነት በማወቅ ከሰብአዊ ድካምነት ጋር የሚገናኝ የእምነት ሕይወት ነው። ስለዚህ ለመለወጥ ያቀና አለ ምንም ቅን ቅድመ ዝግጅት ስለ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለመናገር አይቻልም” ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ቅስዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና እሁድ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፣ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አብነት የሆነውን የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ሕይወት በማስታወስ በቅዱስ ትውፊት የሚገለጠው ለማርያም ዘ ሎረቶ የሚቀርበው የልመና ጸሎት ጠቅሰው ሁሉም ምእመናን በግልና በማኅበራዊ በቤተሰብአዊ ሕይወት ጸሎት ሮዛሪየም እንዲያዘወትሩ በተለይ ደግሞ በዚህ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን በይፋ በሚጀመረው የእምነት ዓመት ወቅት የመቍጸሪያ ጸሎት ያለው ክብር በመለየት ሁሉ ይኸንን ጸሎት በመኖር እንዲበረታ አደራ ካሉ በኋላ፣ “በመቁጸርያ ጸሎት የክርስቶስ ምሥጢሮችን በማስተንተን የእምንት አብነት በሆነቸው ማርያም ለመመራት ፈቃደኞች ለመሆን መላ ኅልውናችን ወንጌላዊ ቅርጽ እንዲኖረውና በወንጌል የተካነ ሕይወት እንድንኖር የሚደግፈን አቢይ ጸሎት እንድገም” በማለት በመጨረሻም ጸሎት መልኣከ እግዚአብሔር ደግመው ከውጭና ከውስጥ የመጡትን በብዙ ሺሕ የሚገመቱት መእመናን ሁሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሰላምታን አቅርበው ለተጀመረው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ እንዲጸልዩ ጥሪ በማቅረብ “እያንዳንዱ ክርስትያን ክርስቶስንና የእርሱ የሰላም መልእክትን ለሌሎች ለማሳወቅ መጠራቱን ዳግም አድሶ ይኸንን የታደለው ኃላፊነቱ እንዲኖር” አደራ እንዳሉም ልእክት ጋዜጠኛ ኢዛቤላ ፒሮ ገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.