2012-10-08 14:30:44

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሲኖዶስ የመክፈቻ ዋዜማ ለሁለት ቅዱሳን የቤተ ክርስትያን ሊቅነት ክብር አወጁ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከሎረቶ ማርያማዊ ቅሱስ ሥፍራ ሓውጾተ ኖልዎ ሁለት ቀን ፍጻሜ በኋላ ትላንትና እሁድ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 7 ቀን 2012 ዓ.ም. የጀርመን የመካከለኛ ዘመን ቅድስት ኢልደግራዳ ዘ ቢንገንና በ 1500 ዓ.ም. የኖረ የስፐይን ተወላጅ ቅዱስ ዮሐንስ ዘአቪላ በይፋ የቤተ ክርስትያን ሊቃውንት RealAudioMP3 በማለት እንደሰየሙዋቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው የቤተ ክርስትያን ሊቅነት አዋጅ ላወጁላቸው ሁለት የቤተ ክርስትያን ቅዱሳን ልጆች በማስመልከት የቅዱስና ጉዳይ የሚከታተለው ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃል ምልልስ፦ “የቤተ ክርስትያን ሊቅነት አዋጅ፦ ቅድስት ቤተ ክርስትያን ለመለኮታዊ ግልጸት ግንዛቤ አቢይና ጥልቅ አስትዋጽኦ ለሰጡትና የቤተ ክርስትያን ቲዮሎጊያዊ ቅርስ ያበለጸጉ የምእመናን በእምነትና በፍቅር እድገት መረጋገጥ ለተንከባከቡት ቅዱሳን ልጆችዋ በመለየት በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የምትሰጠው ክብር” መሆኑ ገልጠው፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን ሊቃውንት፦ “የወንጌላዊ እውነት ለይተው ያሳወቁና በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ በምእመናን ዘንድ በቃልና በሕይወት ለሚሰጠው ምስክርነት ያነቃቁ ናቸው” ብለዋል።
“የቅዱስ በነዲክቶስ ደናግል ማኅበር አባል የጀርመን ተወላጅዋ ቅድስት ኢልደግራድ ዘ ቢንገን የደናግል ማህበር መሥራች የሁለት ገዳማት አመ ምኒየት በግልጸተ እውነታ የቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት አዲስነት እማኔና በጥልቀት ለመገንዘብ የሚደግፍ ትልቅ ሥራ የፈጸሙ፣ የምሥጢረ ሥላሴ፣ ምሥጢረ ትስብእት፣ ምሥጢረ ቤተ ክርስትያንና የምሥጢረ ሰብአዊነት ቲዮሎጊያዊ ቋንቋ ፍቅር በሚያስቀድም ሊቅነት በማነቃቃት ጥልቀቱና ስፋቱ እንዲሁም ይዞታውን ያብራሩ፣ ሰው የሥጋና መንፈስ ውህደት መሆኑና ሥጋ ጫና ሳይሆን ለዘለዓለማዊ ሕይወት የተጠራን መሆናችን ከሥነ ፍጻሜ እርሱም የሰው ልጅ እድል ፋንታ ጋር የተያያዘ መሆኑ በቃልና በሕይወት ያስተማሩ እ.ኤ.አ. ከ 1098 እስከ 1179 ዓ.ም. የኖሩ ቅድስት ናቸው” ካሉ በኋላ አያይዘውም ቅዱስ ዮሓንስ ዘአቪላ በማስመልከትም፦ “እኚህ ከ 1500 እስከ 1569 ዓ.ም. የኖሩ የስፐይን ተወላጅ ቅዱስ በታደሉት ጥበብ እንደ ቅዱስ ኢግናዚዮስ ዘ ሎዮላ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ዘእግዚአብሔር እንደ ቅዱስ ፍራንቸስኮስ ቦርጃ እንደ ቅዱስ ቶማስ ዘቪላኖቫ እንደ ቅዱስ ጴጥሮስ ዘአልካንታራ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ዘሩበራ፣ እንደ ቅድስት ተረዛ ዘኢየሱስ፣ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ ዘመስቀል የላቁ የትምህርተ ክርስቶስ አስተማሪና የቅድስት ቤተ ክርስትያን ሥርወ እምነት በሙላት የሚከተልና የተገነዘበ አቢይ ሰባኪ” በማለት ገልጠው፣ “መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 45 ከቁጥር 11 እስከ 12 ያለውን እርሱም ‘ልጄ ሆይ ስሚ’ በሚል ርእስ ሥር የካቶሊክ ቤተ ክርስትያን መንፍሳዊነት የሚገልጥ እምነት ለማስተላለፍ የሚበጅ የክርስትና የእምነት አንቀጽ፣ የስነ ሥልት ጽማሬ የሚመክር፣ የክርስቶስ የአዳኝነት ምሥጢር የሚያብራራ የእግዚአብሔር ፍቅር ርእስ ያደረገ ሰነድ፣ ጸጋ ጥምቅት የተቀበሉ ሁሉ ለቅድስና መጠራታቸው የቅድስና ጥሪ ኩላዊነት ገጽታውን በተለይ ደግሞ ካህናት በቅድሚያ አብነት መሆን እንደሚጠበቅባቸው የሚያስገነዝቡ ሰነዶች ትተውልን ያለፉ የቤተ ክርስትያን ልጅ ናቸው” በማለት ቅድስት ቤተ ክርስትያን በቅድስት ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት የቤተ ክርስትያን ሊቅነት ስያሜ በይፋ ለምን እንዳወጀችላቸው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አብራርተዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.