2012-10-05 14:21:40

ዓለም አቀፍ የሥነ ዝርያ ሰብእ ጉባኤ በቫቲካን ቤተ መዘክር


የሥነ ምድር ጥናት የሥነ ዝርያ ሰብእ ጥናት ውጤቶች አማካኝነት የዓለማችን ባህላዊ ውርሻዎች መለያ ለማቀብና ይኸንን ዓቢይ ሃብት ዓቅቦ የማኖሩ ኃላፊነት የሁሉም መሆኑ ለማሳሰብ በሥነ ዝርያ ሰብእ ላይ ያተኮረ በቫቲካን የተካሄደው የሁለት ቀናት ዓውደ ጥናት ዛሬ መጠናቀቁ ሲገለጥ። ይህ በቫቲካን ቤተ RealAudioMP3 መዘክር የሰው ልጅ ጎሳ ሥነ እውቀታዊ አገላለጥ ጉዳይ ያተኮረው ዘርፉ ያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ አውደ ጥናት በማስመልከት የዚህ ዓይነቱ የቤተ መዘክር ክፍል ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ የሥነ ዝርያ ሰብእ መግለጫ የሆኑት ቅርሶች ጉዳይ አስተዳዳሪ ብፁዕ ኣቡነ ኒኮላ ናፐሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ሲያመለክቱ፦ “የሥነ ዝርያ ሰብእ መግለጫ ሃብት የተኖረበት ቤተ መዘክር ዓለም አቀፋዊ መልክ ያለው ሁሉንም የዓለማችን ህዝቦች የሚወክል ነው። ስለዚህ ይኽንን ዘርፍ በአንድ ቤተ መዘክር እንዲኖር ማድረግ ለሕዝቦች መተዋወቅና መቀራረብ መሠረት መጣል ማለት ይሆናል። ይህ ቤተ መዘክር በውስጡ ያቀባቸው የተለያየ የሕዝብ ጎሳ ቁሳቁስ ያተኰረ ሳይሆን ሠሪው ወይንም የፈጠረው ሰው ባህሉና ማምንነቱ የሚመለከት ነው። ብለዋል።
የሰው ልጅ ጎሳ ሥነ እውቀታዊ አገላለጥ ጉዳይ የሚከታተለው ቤተ መዘክር የጥገናና የእድሳት ቤተ ሙከራ አስተዳዳሪ ስተፋኒያ ፓንዶዚ በበኩላቸውም፦ “እንዲህ ያለ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ዓለም አቀፋዊ ጉባኤ በቫቲካን ቤተ መዘክር ማስተናገዱ የቫቲካን ቤተ መዘክር በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ክብርና ለመላ የዓለም ሕዝብ የሚሰጠው አስተዋጽኦ እውቅና መስጠት ማለት ነው። በዚህ በቫቲካን ቤተ መዘክር የታቀቡት የታሪክ ቅርሶች ታሪካዊ ስነ ቅቦችና ንድፎች ሓውልቶች በሚገባ አቅቦ ለትውልድ የማስተላለፍ ጉዳይ የሚከታተለው የግብራዊ ሙያ ቤተ ሙከራ ዓለም አቀፋዊ ልምድ ያለው በመሆኑ፣ የቫቲካን ቤተ መዘክር ለቅርሶች ተገቢ እቃቤ የሚሰጠው ቀዳሚነት ግምት የሰጠ ጉባኤ ነው” ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.