2012-10-05 14:17:52

ዓለም አቀፍ የሁለተኛው ቫቲካን ጉባኤ ዓውደ ጥናት በቫቲካን


ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት በቫቲካን የሚገኘው ቤተ መዝገብ በውስጠ ማኅደር የሚያጠቃልላቸው የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መዝገቦች አማካኝነት እርሱም “የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አበው መዝገቦች እይታ ሥር ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ግንዛቤ” በሚል ርእስ የተመራ ጳጳሳዊ የሥነ ታሪክ ኮሚቴና ጳጳሳዊ ላተራነንሰ መንበረ ጥበብ የሥነ ሁለተኛው ቫቲካን ጥናትና ምርምር ማእከል በጋራ ያዘጋጁት RealAudioMP3 ዓለም አቀፍ አውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 3 እስከ ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ይህ በቫቲካን የተካሄደው ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ በጉባኤው አበው ግል ማህደር እይታ ላይ ያተኮረ በመሆኑ የዚያኑ የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ሂደት ብቻ ሳይሆ የነበረው ስሜትና መንፈስና ትርታውም ጭምር ዳግም የሚያስተጋባ መሆኑ ቅድስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ፍሪማ የተኖረበት ለዓውደ ጥናቱ ባስተላለፉት መልእክት ጠቅሰው፣ “የሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አበው ምስክርነትና ተዘክሮ የዚያኑ ቅዱስ ጉባኤ መንፈስ በቤተ ክርስትያን ሕይወት ህያውነቱ ምስክር ነው” እንዳሉ ዓውደ ጥናቱ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ቸቺሊያ ሰፒያ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
ይህ የስነ ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ ጥናትና ምርምር ከስነ ታሪካዊ ሂደቱና ከሰነዳቱ ስነ ትንተና የተንደረደረ ጥልቅ ጥናት ለማነቃቃት ዓልሞ የተካሄደው ዓውደ ጥናት ሲሆን የሚላኖ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ፦ “በር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ አርቆ አሳቢነትና አነሻሽነት የተካሄደው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዳግም ማንበብ ብቻ ሳይሆን ር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንዲካሄድ የገፋፋቸው ምክንያት ለይቶ በጥልቀት ማጥናት አስፈላጊ ነው። ቅድስት ቤተ ክርስትያን ከቅድስት ሥላሴ የተወለደች ወደ እግዚኣብሔርና ለሕዝቦች ድህነት ያቀናች መሆንዋ ዳግም የመሰከረ ቅዱስ ጉባኤ ነው። ስለዚህ ከዚህ በመንደርደር የጉባኤ ሰነድ ነጣጥሎ መመልከት ሳይሆን በተያያዥነት ስልት መጤን አለበት፣ ማለትም የይዞታው ሙሉእነት ላይ ለማተኮር እያንዳንዱ የጉባኤ ውሳኔ ለይቶ ማወቅ አስፈላጊ ነው። ስለዚህ ከተናጥል ወደ ምሉእነት፣ ከሙሉእነት ወደ ተናትጥል የሚል ስልት መከተል ወሳኝ ነው” ሲሉ በተካሄደው ዓውደ ጥናት ተገኝተው በሰጡት አስተምሆሮ እንዳሰመሩበት ልእክት ጋዜጠኛ ሰፒያ ገለጡ።
“ቅድስት ቤተ ክርስትያን የሰውን ልጅ ለማዳንና ከሰው ልጅ ጋር ለመገናኘት ሲል የመጣው ኅያው ምሥጢር በሥርወ እምነት ትምህርት ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ጭምር መተላለፍ እንዳለበት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በሰነዶቹ ሂደት ውስጥ አስምሮበት ይገኛል። እያንዳንዱ ክርስትያን በግልና በማኅበር ደረጃ በሁሉም የሰብአዊ የህልውና ስፍራዎች ሊያስተጋባውና ሊመሰክረው መጠራቱንም ተመልክቶ ይገኛል። ርእሰ ሊቃነ ጳጵሳት ጳውሎስ ስድስተኛ፣ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቀጥሎም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ይኽ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ጥሪ በመለየት አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ ተገንዝበው፣ ለየት ባለ መልኵ በኤወሮጳና ቀድምት ወንጌል በተሰበከባቸው አግሮች በተከስተው ክርስትናን በልምድ የመኖር ፈተና በክርስትናው ህይውት ጉዞ በደከሙት አገሮች ሁሉ ዳግም ለማነቃቃትና ካጋጠማቸው የተዛማጅ ባህል ወረርሽን ለማላቀቅ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል እንዲነቃቃት አድርገዋል። ቅዱስ አባታችንም ‘አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ለክርስትና እምነት መስፋፋት’ በሚል ርእስ ዙሪያ የሚያወይ የመላ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ሲጠሩ አለ ምክንያት አይደለም፣ ይኽ ደግሞ ለኅብረ-ባህሎችና ኅብረ-ያይማኖቶች ኅብረተሰብ አቢይ ተዋጽኦ ነው” እንዳሉ ጋዜጠኛ ሰፒያ አስታውቀዋል።
ፕሮፈሰር ፊሊፐ ቸናዎ ከተካሄደው ዓወደ ጥናት ፍጻሜ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ትክክለኛው ሥነ ተነብቦና ሥነ ትርጉም እርሱም በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ድርጊት እይታና ሂደቱም ያለፈ ታሪክ ድግምግሞሽ ሳይሆን ለውጥና ኅዳሴ ጭምርም መሆኑ ያስገነዘበ፣ በዚህ እይታ የተመራ ዓወደ ጥናት ነው። ስለዚህ ይህ ዓውደ ጥናት እነዚህ ሁለት የእይታ መንገዶች መሠረት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊና ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለትክክለኛ ግንዛቤና ምንባቡን ለመምራት የሰጡት ሥልጣናዊ ትምህርት የሚጎላበትም ነው። በይዞታውና በታሪካዊ ሂደቱ አማካኝነት ጉባኤው ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች ያተኰረባቸው ጥያቄዎችን በመለየት አለ ምንም ቅድም ርእዮተ ዓለም መሠረት በትክክል ለመገንዘብ የሚያግዝ ዓውደ ጥናት” እንደነበር አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.