2012-10-05 14:14:26

አሲዚ፦ ዓውደ ጥናት “Il Cortile dei Gentili-የአህዛብ ቅጥር ግቢ”
“የማይታወቅ እግዚአብሔር” (ግብረ ሓዋ. 17፣23)


የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት “Cortile dei Gentili-የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ርእስ ሥር የተመራ የዓለማችን አበይት እና አንገብጋቢ በፍልስፍና በቲዮሎጊያ በሥነ ኅልውና ርእሰ ዙሪያ የሚቀርቡት ጥያቄዎችና መልሶቻቸውንም መሠረት በማድረግ አማኞች እና ኢአማኒያን ሊቃውንትና ምሁራንን RealAudioMP3 የሚያወያይ እምነት እና ምርምር የማይነጣጠሉ የሚደጋገፉ መሆናቸው ለማረጋገጥ ዓልሞ ያነቃቃው መርሃ ግብር በመቀጠል እ.ኤ.አ. መስከረም 13 እና 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በዚያች ሉተራናዊ ባህልና በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ቅጥ አልቦ ዓለማዊነት ባህል እጅግ በተስፋፋባት ስለ እግዚአብሔርም ሆኖ ባጠቃላይ ሃይማኖታዊ ርእሰ ጉዳዮች በማይነሳባት አገረ ስዊድን “ዓለም ከ-ወይም አለ-እግዚኣብሔር” በሚል ርእስ ሥር ካካሄደው ዓውደ ጥናት በመቀጠል እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 5 እስከ ጥምቅ 6 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ “የማይታወቅ እግዚአብሔር” (ግብረ ሓዋ. 17፣23)” በሚል ርእስ ዙሪያ እምነት እና አልቦ እምነትን የሚያወያይ ዓውደ ጥናት እንደሚያካሄድ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚና የቅዱስ ገዳም ዘአሲዚ የዜናና ማኅትመት ጉዳይ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኤንዞ ፎርቱናቶ እንዲሁም ደራሲ ቪቸንዞ ቸራሚ እ.ኤ.አ. መስከረ 26 ቀን 2012 ዓ.ም. በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱ ጠቁመን እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ በዚህ ዓወደ ጥናት የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖ እና ሌሎች የኢጣሊያ አበይት የፖለቲካ አካላት ከውስጥና ከውጭ አገር መጥ አማንያንና ኢአማንያን ምሁራን እየተሳተፉ መሆናቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. በይፋ የሚጀመረው ያወጁት የእምነት ዓመት ላይ ያማነጣጠር ዓወደ ጥናት የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት በአሲዚ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ለማካሄድ መሻቱንም ከተማይቱ ለውይይትና ለአዲስ አስፍሆተ ወንጌል አብነት መሆነዋ ግምት በመሰጠት መሆኑ ተገልጠዋል። በዚህ “አንድ የማይታወቅ፣ እግዚአብሔር” በሚል ርእስ ሥር 40 ሊቃውንት አስተምህሮ የሚሰጡበት ዓውደ ጥናት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም. በኢጣሊያ ሰዓት አቆታጠር ከምሽቱ 5 ሰዓት የኢጣሊያ ርእሰ ብሔር ጆርጆ ናፖሊታኖና የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ በቫቲካን ረዲዮ በቀጥታ የሚተላለፍ የዓውደ ጥናቱ ርእስ ዙሪያ በሚያካሂዱት ውይይት በይፋ ተጀምረዋል። እንደሚታወቀውም ይህ ዛሬ የተጀመረው አሕዛብ ቅጥሪ ግቢ ዓውደ ጥናት የታዳጊ ወጣት ቅጥር ግቢ እንዲሁም ወጣት ታዳጊዎችን የሚያሳትፍ የትረካ ቅጥር ግቢ ዓውደ ጥናት ያካተተ እንደሆነም ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት ካሰራጨው መግለጫ ለመረዳትተችለዋል።
ብፁዕነታቸው እንዳመለከቱትም፦ “እስከ አሁን ድረስ የተካሄዱት የአህዛብ ቅጥር ግቢ ዓውደ ጥናቶች ካስገኘው ውጤት አንጻር ሲታይ አወንታዊ መሆኑና አብያተ ክርስትያን ለአማንያን ብቻ ሳይሆን ከኢአማንያን ጋር ለመወያየት በሮቻቸውን ክፍት መሆኑ ሲያረጋግጥ በሌላው ረገድ ስለዚሁ ዓውደ ጥናት በማስደገፍ በመገናኛ ብዙኃን ብዙ የማይባል በመሆኑ ይህ የመገናኛ ብዙኃን ግድ የለሽነት ተጋርጦውን ለመቀረፍ የሚያነቃቃ መርሃ ግብር ነው” ብለዋል።
የቅዱስ ገዳም ዘአሲዚ የዜናና ኅትመት ጉዳይ ዋና አስተዳዳሪ አባ ኤንዞ ፎርቱናቶ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ጥቅምት አራት ቀን የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ ዓመታዊ ክብረ በዓል ባከበረችበት ዕለት ማግሥት መሆኑ ዘክረው፣ ይህ በአሲዚ የሚካሄደው የአሕዛብ ቅጥር ቅቢ የቅዱስ ፍራንቸስኮስ ቅጥር ግቢ በማለት ሰይመው፣ የአሲዚው ቅዱስ አምነት የሚጎላበትና የዚህ ቅዱስ ማንነት የሚስተነተንበት ሰዎችን የሚያገናኝ መርሃ ግብር ነው” ብለዋል።
በመጨረሻም ደራሲ ቪንቸንዞ ቸራሚ “ይህ ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት በማዘጋጀትና በማነቃቃት የሚያካሂደው ባህላዊ ዓውደ ጥናት በጥልቀቱና ይዞታው አንጻር ሲታይ በኢጣሊያ ብቸኛ አቢይ የባህል መድረክ ነው ለማለት እደፍራለሁኝ” ብለዋል።
በዚህ በአሲዚ የሚካሄደው የአሕዛብ ቅጥር ግቢ ዓውደ ጥናት ዘጠኝ ግኑኝነቶችና 40 የተለያዩ የባህል ሊቃውንት አስተምህሮ የሚቀርብበት መሆኑ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.