2012-10-03 14:26:04

ሶሪያ፦ የአገሪቱ ሃይማኖታዊ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብት ለማዳን የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ጥሪ


በሶሪያ እልባት ያጣው የእርስ በእርስ ግጭት በእጅጉ የሚጎዳው ንጹሕ የአገሪቱ ዜጋ መሆኑ የሶሪያ አቢያተ ክርስትያን በጋራ ባወጡት መግለጫ አበክረው፣ ከዚህ ተከስቶ ካለው አደጋ ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ የባህል ቅርስ ተብሎ የሚንገርለት የሶሪያ ሃይማኖታዊ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርስ ማዳን የሁሉም ኃላፊነት መሆኑ RealAudioMP3 አቢያተ ክርስትያኑ በጋራ በፊደስ የዜና አገልግሎት በኩል ባስተላለፉት ሰነድ ይገልጣሉ።
የአቢያተ ክርስትያን የጋራው የጥሪ መልእክት በአለፖ የሚገኘው ታሪካዊ ሱክ ላይ የተጣለው የውድመት አደጋ ማግሥት መሆኑ የጠቀሰው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ በሶሪያ የአቢያተ ክርስትያን መሪዎች ያስተላለፉት መልእክት በቅድሚያ ለተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፡ የሥነ ምርምርና የባህል ተንከባካቢ ድርጅት እንዲሁም የምስራቅ አቢያተ ክርስትያን ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር የባህል ጉዳይ ለሚከታተለው ለጳጳሳዊ ምክር ቤት መሆኑ ገልጦ፣ በሶሪያ ተከስቶ ያለው ግጭት የአገሪቱ ባህላዊ ታሪካዊ ምህዳሮችን ቤተ መዘክሮችን የሚነካ የሚያወድም ከመሆኑም ባሻገር፣ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋሞች አቢያተ ክርስትያን መስጊዶች ሙክራቦች ገዳማትና ቅዱሳት ሥፍራዎች ላይ ያነጣጠረ መሆኑ ገልጠው፣ ዜጎች ባህል ሥነ ቅርስ ታሪካዊ ምህዳሮች ከጥፋት እናትርፍ የሚል ጥሪ ያካተተ መልእክት መሆኑ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.