2012-10-03 14:10:01

ሎሬቶ ቅዱስ አባታችንን ለማስተናገድ በጉጉት ትጠባበቃለች


ነገ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በይፋ ከማስጀመራቸው ቀደም በማድረግ መላ ቅዱስ ጉባኤው በቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃ ሥር እንዲመራ የእርሷን አማላጅነት ለመጸለይ በሎረቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የፈጸሙት RealAudioMP3 ሐውጾተ ኖልዎ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት ብሎም የእምነት ዓመትና ዳግመ አስፍሆተ ወንጌል ዙሪያ የሚወያየው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ በማርያም ጥበቃ ሥር እንዲከናወን ለመጸለይ በዚያ የሥነ ታሪክና የሥነ ጥንተ ቅርስ ምርምር የሚያረጋግጠው በናዝሬት የቅድስት ድንግል ማርያም የነበረው መኖሪያ ቤት የታቀበበት ሎሬቶ የሚገኘው ቅድስት የናዝሬቲቱ ቤት ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደሚያከናውኑ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ የቫቲካን ረዲዮ ለጣልያንኛ ቋንቋ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጓራሺ ለኵላዊ የቅድስት ቤት ማኅበር ዋና አስተዳዳሪ አባ ጁዜፐ ሳንታረሊ፣ የዚያ ታሪካዊ በናዝሬት የቅድስት ድንግል ማርያም መኖሪያ ቤት የታቀበበት ቅዱስ ሥፍራ መሆኑ የሚያረጋግጠው መረጃ በተመለከተ ላቀረበላቸው ቃለ መጠይቅ ሲመልሱ፣ የሎሬቶ የሚገኘው ቅዱስ ቤት በሎሬቶ በሚገኙት ድንጋዮች ሳይሆን ከናዝሬት በመጡት የመሠረት ድንጋዮች የተገነባ መሆኑ የሥነ ጥንተ ቅርስ እንዳረጋገጠው ጠቅሰው የቤቱ አቀማመጥና ንድፍም ልክ በፍልጥኤም እንደ ሚገነቡ ቤቶች ሲሆን፣ የአይሁድና የክርስትና እምነት መግለጫ የሆኑት የተቀረጹ ጽሑፎች የተኖረበትና፣ እ.ኤ.አ. ከ 1290 እስከ 1294 ዓ.ም. ባሉት የዓመታት ገደብ ከናዝሬት ወደ ሎሬቶ የመጣ የዚያ የናዝሬቱት ቅድስ ቤተ መኖሪያ የተገነባበት ድንጋይ መሆኑም የቤተ ክርስትያን ትውፊት ያረጋገጠዋል ብለዋል።
የሥነ ጥንተ ቅርስ ጥናት እንደሚያረጋገጠውም በናዝሬት የነበረው የማርያም ቅዱስ ቤት ሙክራብ አምሳያ በተገነባው ቤተ ክርስትያን ሥር የሚገኝ እንደነበርና ከሦስተኛው ክፍለ ዘመን ወዲህ በመስቀል ጦርነት ወቅት የናዝሬት ቅዱስት ቤት ላይ የቢዛንታይን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስትያን መገንባቱ ገልጠው እንደሚገመተው የቤቱ ድንጋይ በ 1469 ወደ ሎሬቶ ተዛውሮ በኢጣሊያ የቶስካና ክፍለ ሃገር ተወላጅ ታዋቂው የሥነ ሕንጻ ንድፍ ሊቅ ጆርጆ ማሪኒ አማካኝነት ተድፎ መገንባቱ የቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር ያረጋግጠዋል።
በአሁኑ ወቅት የቅድስት ቤት አስተዳዳሪ እንዲሁም ከተለያዩ አገሮች ወደ ሎሬቶ ቅዱስ ቤት ለመንፈሳዊ ንግደት የሚሄዱትን በዚያ ቅዱስ ሥፍራ መሥዋዕተ ቅዳሴ ለማሳረግ የሚመጡት ካህናት የሚያስተናግድ የጸሐፊ ቢሮ፣ የማርያም መንፍሳዊነት የሚያነቃቃና ኵላዊ የቅድስት ቤት ማኅበር ለሥርየተ ኃጢአት ወደ ማርያማዊ ቅድስ ሥፍራ የሚመጡትን የሚያስተናግድ የአናዛዥ ጳጳሳዊ ማኅበር አባላት፣ በየዓመት መሰከረም 8 ቀን የሚከበረው የቅድስት ድንግል ማርያም ልደት በዚህ ቅዱስት ቤት የሚከበር አቢይ በዓል መሆኑና ለዚህ በዓልም ከውስጥና ከውጭ የሚጎርፉ ዓበይት የመንግሥት አካላት ጭምር የሚገኙባቸው የመንፈሳውያን ነጋድያን ሱታፌ አቢይ መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.