2012-10-02 15:18:18

የአባ አለግራ ሥርዓተ ብፅዕና


አባ ጋብርኤለ ማርያ አለግራ የተባሉ ፍራንቸስካዊ መነኵሴና የቅዱስ መጽሓፍ ሊቅ ለመጀመርያ ጊዜ ቅዱስ መጽሓፍን በቻይና ቋንቋ የተረጐሙ ትናንትና ብፁዕ ተብለዋል፣ የብፅዕናቸው ሥነ ሥርዓትም በአቺረያለ ቤተ ክርስትያን አደባባይ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛን ወክለው እዛ በተገኙ የቅዱሳን ጉዳይ የምትከታተል ማኅበር ኃላፊ በሆኑ በብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ አማቶ ተፈጸመ፣ በሥርዓቱ የፓለርሞ ሊቀ ጳጳስ እና የሲቺልያ ረኪበ ጳጳሳት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል፤ የሆንግ ኮንግ ካዲናል ጆን ቶንግ ሆን፤ የንኡሳን አኃው ካፑቺኒ ማኅበር ጠቅላይ ኃላፊ ጥቀ ክቡር አባ ኾዘ ሮድሪገዝ ካርባሎ እና ከሲቺልያ ሃገረ ስብከቶች የተሰበሰቡ ብዙ ምእመናን ተገኝተዋል፣
ብፁዕ አባ ጋብር ኤለ ማርያ አለግራ በሲቺልያ አከባቢ ሳን ጆቫኒ ላ ፑንታ በምትባል ከተማ በካታንያ ክፍለ ሃገር በ1907 ዓም ተወለደ፣ በ23 ዓመት ዕድሜው የን ኡሳን አኃው ካፑቺኒ ማኅበር ካህን ሆነ፤ ለስብከተ ወንጌል ቻይና ሂዶ በፐኪኖ ከተማ የፍራንቸስካውያን የቅዱስ መጽሐፍ ጥናት ትምህርት ቤት መሥረተዋል፣ ከዛ በውግያ ምክንያት ወደ ሆንግ ኮንግ ተሸጋግረዋል፣ ለ26 ዓመታት በትጋትና ጥራት ሰርተው ቅዱስ መጽሓፍን ወደ ቻይና ቋንቋ ተርጉመዋል፣ በ1976 ዓም በቅዱሳን ሞት ከዚህ ዓለም ተለይተዋል፣ ቤተ ክርስትያንም ሕይወታቸውን እና የነበራቸውን መንፈሳውያን ኃይላት መርምራና አጥንታ በትናንትናው ዕለት ስማቸውን በብፅ ዕና ደረጃ በመዝገበ ቅዱሳን አሰፈረችው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.