2012-10-02 15:11:21

የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


ውድ ውንድሞችና እኅቶች RealAudioMP3
የዛሬው እሁድ ወንጌል የቅዱስ ማርቆስ ምዕራፍ 9 ከቍ 38-41 ሆኖ ክርስቶስ ካከናወናቸው አንዱን አጋጣሚ የሚገልጥ እንደነገሩ አለፍ ሲል የተፈጸመ ቢሆንም ጥልቅ ምሥጢር የያዘ ክፍል ነው፣ ታሪኩ እንዲህ ነው፣ ወጣትና ቀናተኛ የነበረው ዮሐንስ ሐዋርያ የኢየሱስ ተከታይ ያልሆነ አንድ ሰው በኢየሱስ ስም አጋንንትን ሲያወጣ ባዩት ጊዜ ከልክለውት እንደነበር ለኢየሱስ ይነግረዋል፣ ኢየሱስ ግን እንዳይከለክሉት ይነግራቸዋል ከዚህ አጋጣሚ በመነሳትም ሐዋርያቱን ሊያስተራቸው ይጀምራል፣ እግዚአብሔር የማኅበራቸው አባላት ባልሆኑም መልካም ነገሮች እንዲሁም ተአምራትም ሊፈጽም እንደሚችል ይነግራቸዋል፣ አያይዞም ለእግዚአብሔር መንግሥት መተባበር የሚችል ሁሉ ለመልእክተኛየ አንድ ብርጭቆ ውኃ የመስጠት ቀለል ያለ የመልካም ተግባር ሳይቀር የመተባበር ምልክት መሆኑን እወቁ ይላቸዋል፣ ቅዱስ ቅጎስጢኖስ ይህንን ጥቅስ ሲገልጥ “በካቶሎካዊት ቤተ ክርስትያን ማለትም ቤተ ክርስትያን ባጠቃላይ ካቶሊክ ያልሆነ ሊገኝ ይችላል እንዲሁም ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ውጭ ደግሞ ካቶሊካዊ ሊገኝ ይችላል” ይላል፣ ስለዚህ የቤተ ክርስትያን አባላት መቅናት የለባቸውም ነገር ግን ከማኅበሩ ውጭ የሆነ ሌላ ሰው በክርስቶስ ስም መልካም ሥራ ሲያደርግ ባዩበት ቍጥር ተግባሩ በቅኑ ኅልናና በአክብሮት እስከተፈጸመ መደሰት አለባቸው፣ በቤተ ክርስትያን ውስጥም አንዳንዳንዴ ሊያጋጥም እንደሚችል በቤተ ክርስትያን የሚደገረግው የተለያዩ መልካም ሥራዎች ለመቀበልና ዋጋ ለመስጠት የሚያስቸግራቸውም ሊገኙ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን ሁላችን ዘወተር በእነኚህ ተግባሮች ጌታ በቤተ ክርስትያኑና በዓለም በሚያደርጋቸው ቍጥር ስፍር የሌላቸው አስደናቂ ነገሮች አንዱ ሌላውን ማድነቅና ዋጋ መስጠት አለብን፣
በዛሬው ሥር ዓተ አምልኮ ንባባት የቅዱስ ያዕቆብ መልእክት ምዕራፍ ከቍ.1-6 ዋስትናቸውን ባከማቹት ሃብትና በኃይላቸው ዓመጽ የሚተማመኑት ሃብታሞችንና ቅኑ ያልሆኑትን ሐዋርያዊ ዘዴ በተሞላበት ሲገስጻቸው እንመለከታለን፣ ቸዛርዮ ዘአርለስ ይህንን በተመለከተ በሚያቀርበው ሐተታ “ሃብት ለመልካም ሰው በምሕረት ሥራ ለሌሎች ስለሚያካፍለው ምንም ሊጐዳው አይችልም፣ እንዲሁም በተፈጥሮው ክፉ ለሆነ ሰው በስግብግብነት ሊያጠራቅመው ወይንም ለማይሆን ነገር በትኖ ሊያጠፋው ለሚችል ሰው ሊረዳው አይችልም” ይላል፣ የያዕቆብ ሐዋርያ ቃላት ያለንን ንብረት በስግብግብነት ከመከማቸት ይልቅ ሁሌ በሁሉም ደረጃ በእኩልነትና በግብረገብነት ለመተባበርና ለጋራ ብጎ አገልግሎት እንድናውለው ኃይለኛ ጥሪ ያቀርብልናል፣
ውዶቼ በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በእያንዳንዱ መልካም ተግባርና ዓላማ ካለ መቀናናት እንድንደሰትበትና ያሉንን ምድራዊ ሃብቶች ለሰማያዊ ሃብት ፍለጋ በጥበብ ለመጠቀም እንድንችል ዘንድ እንማጠን፣ ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣ከመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት በኋላ ምሥራቅ ኮንጎን የሚመለከት ጥሪ አቅርበዋል፣ “በዚሁ ቀናት ውስጥ በደሞክራስያዊት ሪፓብሊክ ኮንጎ ምሥራቅ ክፍል በሚገኘው ሕዝብ ላይ እየወረደ ያለው በከፍተኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሳይቀር ትኵረት የተሰጠበት ችግር በብርቱ ስሜትና አሳቢነት እየተከታተልሁት ነው፣ በግጭቱ ምክንያት የሥቃይ የዓመጽና የጭንቀት ሰለባ ከሆኑት በተለይ ደግሞ ከስደተኞች ከሕጻናትና ከሴት ልጆች ጐን መቆሜን እገልጻለሁ፣ የውይይትና የብዙ ንጹሓን መከላከያ ሰላማዊ መንገዶች ተገኝተው በፍትሕ የተመሠረተ ሰላም እስኪመልና በፈተና በሚገኘው እና በመላው አከባቢው በወንድማማችነት የመኖር መንፈስ እንዲታይ እግዚአብሔርን እለምናለሁ፣







All the contents on this site are copyrighted ©.