2012-10-02 15:07:46

የ2013 ዓም የብዙሓን ማኅበራዊ መገናኛዎች ዓለም አቀፍ ቀን


የ2013 ዓም የብዙሓን ማኅበራዊ መገናኛዎች ዓለም አቀፍ ቀን በማኅበራዊ መገናኛዎች አውታሮች ላይ የሚያተኩር ሆኖ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ኢንተርነትን ለስብከተ ወንጌል እንድንጠቀም ያሳስባሉ፣ ለቀኑ የሚተላለፈው መል ክት አ ር እስትም “ማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች፤ የእውነትና የእምነት በሮች አዲስ የስብከተ ወንጌል ቦታዎች” ይላል፣ ይህ ለ47ኛ ጊዜ ለሚከበረው የ2013 ዓም ዓለም አቀፍ የብዙኃን ማኅበራዊ መገናኛዎች ቀን መሪ ቃል ይፋ የሆነው ትናንትና ነው፣ የኢንተርነት ጥቅምን በሚመለከት መልእክትና የዲጂታል ዘመናችን ለአዲስ ስብከተ ወንጌል የሚያቀርበው እክል በሚል ር እስ “ኢንተርነትን ለአዲስ ስብከተ ወንጌል እንደመሣርያ መጠቀም ብቻ ሳይሆን ራሱ ኢንተርነትን መስከብ አለብን፣ ምክንያቱም የዘመናችን ሰው ራሱን ለመግለጥ የሚጠመቀመው በዲጂታል ማእከልነት ስለሆነ” ይላል፣
የመል እክቱን ይዘት ለማብራራት የቺቭልታ ካቶሊካው ዳረክተር አባ አንቶንዮ እስፓዳሮ ለቫቲካን ረድዮ በሰጡት ቃል “በዚሁ የእምነት ዓመት ሊታወጅ ቀርቦ ባለበት ግዜ ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ በመል እክቱ ር እስ የተጠቀሙት ብቻ ብዙ ምሳሌዎች እንዲያው ቅንያዊ የሆኑ ሰምና ወርቅ ለበስ ቃላት አሉ፣ በር ስፋራ የሚሉ ቃላት እንዲሁም እውነት እምነትና ስብከተ ወንጌል ጥልቅ ትርጉም አላቸው፣ ለብዙ ሰዎች ይህ አባባል ድንገተኛ ሊሆንባቸው ይችላል ምክንያቱም ለአንዳንድ ሰዎች የብዙኃን ማኅበራዊ መገናኛዎች ለመገናኘትና ሓሳብ ለሓሳብ ለመካፈል የሚያገለግሉ መሣርያዎች ሲሆኑ ለሌሎች ደግሞ ለሃይማኖት ይቅርና ለትምህርትም በተለይ ለወጣቶች እጅግ አደገኛ አድርገው ይመልከትዋቸዋል፣ ቅዱስነታቸው ግን ይህን ሁሉ አልፈው በእነዚሁ መገናኛዎች ላይ አትኩረዋል፣ በሌላ አነጋገር እነኚህ አውታሮች ምንድር ናቸው፧ የተጠቀምናቸው እንደሆነስ ምን ይከሰታል፧ ለዚህም ነው እንደ በር የገለጥዋቸው፣ በዚሁ ሥልጣኔና በአዲሱ ተክኖሎጂ ግፊት ሰብአዊ የመገናኘት ቦታም ተፍጥረዋል፣ ተክኖሎጂው ብቻ ሳይሆን በስተጀርባው ሁሌ የሰው ልጅ እንዳለ ላለመዘንጋት ነው፣
ቅዱስነታቸው በመል እክታቸው ስለ አጠቃላይ ማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛዎች አይደለም የሚናገሩት፣ በዘመናችን ልዩ መተሳሰር በመፍጠር ለመተዋወቅ እውቀት ለማግኘት ተመኵሮ ለመለዋወጥ ቦታ የሰጠና በር የከፈተው ተክኖሎጂ ስለሆነ “ተክኖሎጂ የሰው ልጆች ክርስቶስን እንዲያገኙ ሊረዳ ይችላል ወይ፧” ብለን መጠየቅ አስፈላጊነቱ አሁን ነው፣ የዘመናችን ሰው የሚኖረው አከባቢ ወይም ሁኔታ ደግሞ በዚሁ ስለሆነ ቃለ ወንጌልን እዛ ማድረስ አለብን፣ ለዚህም ቅዱስነታቸው አከባቢው ራሱ ኢንተርነቱ በቅድሚያ መሰበክ ስላለበት የስብከቱ ወንጌሉ ኃላፊት እንድንቀበል አደራ የሚሉት፣ ሁኔታው ለውይይትና ግኑኝነት ዕድል ስለሚሰጥ የዘመናችን ሰዎችም በብዛት ስለሚጠቀሙት እኛም የግድ ልንጠቀመው ያስፈልጋል፣ ችግሩ ግን የዚህ ዓይነት ግኑኝነት ተክኖሎጂካዊ ብቻ ስለሆነ ስብከተ ወንጌሉ ወደ ተጨባጭ ሰብ አዊ ግኑኝነት የማሸጋገር ሁኔታን መጋፈጥ አለበት፣
ዓለም አቀፍ የብዙኃን ማኅበራዊ መገናኛዎች ቀን የዛሬ 50 ዓመት ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤ አባታቶች አስደናቂ ነገሮች (ኢንተርሚሪፊካ) በሚለው ሰነድ ያቆመው ዕለት ነው፣ ቅዱስነታቸው ለዚሁ ዕለት የመረጡት አ ር እስትም የጉባኤው አባቶች ምን ያህል ትንቢታውያን እንደነበሩ ያመለክታል፣ ቃለ እግዚአብሔር ከሰው ልጆች ሥልጣኔ ጋር በመጓዝ በየጊዜው በሚፈጠሩ መሣርያዎች ይሰራጫል፣ ምንም እንኳ የተክኖሎጂ ውጤቶች ንጹሕ ባይሆኑም በጥንቃቄ መጠቀሙ የወንጌል ሕይወትን በዚሁ አውታሮች ዘመን እንደሚግባ በመኖር ልንሰብክ እንችላለን፤ በማለት አስተያየታቸውን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.