2012-10-01 15:04:33

የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ፦ “አዲስ የቤተ ክርስትያን ተራምዶ”


በሳምንት ማገባደጃ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የሚያቀርቡት የቅድስት መንበር ርእሰ ዓንቀጽ በመቀጠል እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መስከረም RealAudioMP3 29 ቀን 2012 ዓ.ም. “አዲስ የቤተ ክርስትያን ተራምዶ” በሚል ርእስ ሥር በማቅረብ፣ ኵላዊት ቤት ክርስትያን በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ አማካኝነት ያወጀችው የእምነት ዓመት፣ አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ የሚካሄደው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት ክብረ በዓል፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻና መላ ሂደቱን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት በተቃና ፍጻሜ ላይ እንዲደርስ ለመጸለይ በሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ያደርጉት ሐውጾተ ኖልዎ ዝክረ 50ኛው ዓመት ምክንያት እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ የሚያካሂዱት ሐውጾተ ኖልዎ የሚኖርበት ወር” መሆኑ አስታውሰው፣ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከመሾማቸው ገና ብፁዕ ካርዲናል እያሉ ስድስት ጊዜ መንፈሳዊ ንግደት፣ ከተሾሙ በኃላም አንድ ጊዜ ሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ሐውጾተ ኖልዎ ማከናወናቸው” አባ ሎምባርዲ ባቀረቡት ርእሰ ዓንቀጽ አስታውሰዋል።
“ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መክፈቻ ዓመታዊ በዓል እመ መለኮት መዝጊያውም በዓለ ቅድስት ድንግል ማርያም እርሱም አለ አዳም ኃጢኣት የተጸነሰችበት በንጽሕት ድንግል ማርያም በዓል መጠናቀቁና፣ ቅዱሱ ሲኖዶስ ‘ብርሃነ አሕዛብ’ ውሳኔውን ማርያም ለሕዝበ እግዚአብሔር የተስፋና የመጽናናት ምልክት መሆንዋ በሚያስገንዘብ ቃላት” መደምደሙንም አባ ሎምባርዲ አብራርተው፣ “የቤተ ክርስትያንና የሕዛበ እግዚአብሔር ተራምዶ ማርያማዊ ነው” ብለዋል።
“ከር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛ ጋርና እንደ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የትህትናና የደስታ ብሥራተ አዋጅ እንዲሁም ትስብእቱ ለእግዚአብሔር፣ ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልኩም የሲኖዶስ ወር የእምነት አመት በኢየሱስና በእኛ እናት ተበረታትተን በተገባና በሙላት ለመኖር አብረን እንጓዝ” በማለት ያቀረቡትን ርእሰ አንቀጽ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.