2012-10-01 15:00:48

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ ቤተ ክርስትያን ያለፈ ታሪክ ሳይሆን ህያው የምታከብር ነች


በኤሚሊያ ሮማኛ ክፍለ ሃገር በፎርሊ ቸሰና እውራጃ ባኞ ዲ ሮማኛ ከተማ እ.ኤ.አ. በ 1412 ዓ.ም. የአበ ምኒየት ላዛሮ በቅዱስ ቁርባን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ ሥጋሁ ወ ደሙ ላይ ለነበራቸው የእምነት ጥርጥር ያስወገደው የምሥጢረ ቅዱስ ቁርባን ተአምር፣ እርሱም በመሥዋዕተ ቅዳሴ ወቅት እውነተኛው የደም RealAudioMP3 ጠብታ ተአመር የታየበት ቀን ዝክረ 600ኛው ዓመት ምክንያት በፍልሰታ ለማርያም ባዚሊካ ያረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ባሰሙት ስብከት፦ “ቤተ ክርስትያን የታሪክ ነበር እርሱም ያለፈ ታሪክ ሳይሆን ኅያውነትን ነው የምታከብረው፣ በተለይ ደግሞ ቅዱስ ቁርባን በምትሠራበት ወቅት፣ ዝክረ ትውስተ ታሪክ ለማስተጋባት መታሰቢያ ለማድረግ ሳይሆን ኅያውነት ያለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋሁ ወደሙ እንደ ጌታችን ቃል በምሉእ ተመሳሳይ መልኩ የሚቀርብበት ነው። በአሁኑ ወቅት መሥዋዕተ ቅዳሴ ለመከታተል ሰንበትን አክብር ለሚለው ክርስትያናዊ ጥሪ ቸል እየተባለ በተለያየ ምርጫና ሁኔታ በተዋከበው ዓለም የሚታየው የትርጉም የለሽ ኑሮ ቅዱስ ሥጋሁ ወደሙ ለሚሰጠው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅርብ እንሁን እርሱን በመቀበል ብቻ ነው የምናሸንፈው” ብለዋል።
ዛሬም ልክ እንዳለፈው 600 ዓመት እንዳለፈው 2000 ዓመት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ህያው የነበረ ያለ የሚኖር ነው፣ ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓመት በዓል እንዲከበር፣ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን እንዲከበር ያወጁት የእምነት አመት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ሲኖዶስም ሲጠሩ አለ ምክንያት አይደለም፣ ስለዚህ ሁላችን ቤተሰቦች ካህናት ደናግል ምእመናን በእምነት እንድናድግ ነውና፣ ከልባችን መጠራጠርን እንዲያስወግድ እምነቴን ጨምርልኝ እንበለው” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.