2012-10-01 15:09:01

ብፁዕ አቡነ በቺዩ፦ ለወቅታዊው ዓለም የክርስቶስ ተስፋ አብሣሪዎች


የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ኵላዊት ቤተ ክርስትያን እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓመታዊ የቅዱስ ገብርኤል ሊቀ መላእክት በዓል እንዳከበረች የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ ገብራኤል መልአክ የጋዜጠኞች የመገናኛ ብዙሃን ሠራተኞች በጠቅላላ የመገናኛ ብዙሃን ጠበቃ ቅዱስ በመሆኑ፣ እንደተለመደው በዚህ RealAudioMP3 ዓመታዊ በዓል ምክንያት በራዲዮ ቫቲካን ሕንፃ በሚገኘው ብሥራተ ገብርኤል ጸሎት ቤት፣ የቅድስት መንበር ዋና ጸሓፊ የይፍዊ ጉዳይ ተንከባካቢ ቢሮ ምትክ ኃላፊ ብፁዕ አቡነ አንጀሎ በቺዩ ለራዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኞችና የግብራዊ ሙያ አባላትና በጠቅላላ ለራዲዮ ቫቲካን ሠራተኞች መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ በዓል ምክንያት ለሦስት የራዲዮ ቫቲካን ጋዜጠኞች የክብር ማእርግ ተሰጥተዋል።
ብፁዕ አቡነ በቸዩ በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት፦ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኞች የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ድምጽ በመሆን፣ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዲስ ብሥራት አብሳሪዎች ናችሁ” በማለት፦ ያለብን ኃላፊነት ምንኛ ዓቢይ መሆኑ በማስታወስ፦ የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኞች የአዲስ ብሥራት ድምጽ ናቸው፣ ልክ እንደ ማርያም በጎልጎታው ምሥጢር የሚያልፍ የትንሣኤ ተስፋ የሚኖር አዲስ ብሥራት ለመኖር የተጠሩ ናቸው። በሰብአዊ ክፋት ለጠፋው ኅብረተሰብ መዳን የማርያም እምነት እንዳስፈለገም” ጠቅሰው፣ “እንደ ማርያም በትንሣኤ ያመነ እምነት ለመኖር ተጠርተናል፣ ብለዋል።
“የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ተስፋን የሚያነቃቃ ብሥራት ነጋሪ ነውና ይኸንን ጥሪው በእሴቶች ቅድመ ተከተል የተመራ ሆኖ ትክክለኛና እውነትኛ የዜና ምንጮችን ለይቶ እውነትን በማንጸባረቅ ተስፋ የሚያነቃቃ፣ የክርስቶስ ፍቅር ድህነት ለመላው የዓለም ሕዝብ በእግዚአብሔር የተፈቀረ መሆኑ የሚያረጋገጥ ቃል የሚበሥር ነው። ብለዋል።
በመጨረሻም ባረገው መሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ በተካሄደው የመልካም በዓልም መግለጫ ጉባኤ የቫቲካን ረዲዮ የመርሃ ግብር ዋና አስተዳዳሪ አባ አንድረያ ኮፕሮቭስኪ ባሰሙት ንግግር የቫቲካን ረዲዮ ህዳሴና የተራቀቀ የእደ ጥበብ ውጤቶችን በመጠቀም ያሳየው መሻሻልና እድገት ማብራራታቸው ሲገለጥ፣ በመጨረሻም በሃንጋሪ ቋንቋ ለሚሰራጨው የቫቲካን ረዲዮ ክፍል ጋዜጠኛ ማርታ ቨርትሰ በህንድ ቋንቋ ሥርጭት ጋዜጠኛ እናቴ ማርይ ተረዛ እንዲሁም ለቫቲካን ረዲዮ ግብረአዊ ሙያ ሠራተኛ አለሳንድሮ ካንዲ የክብር ሽልማት መሰጠቱ ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.