2012-10-01 14:58:49

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ከካስተል ጋንዶልፎ ተሰናበቱ


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለበጋው ዕረፍት ከሚገኙበት ከካስተል ጋንዶልፎ ከተማ ካለው ጳጳሳዊ ሕንጻ እ.ኤ.አ. ቅዳሜ መስከረም 29 ቀን 2012 ዓ.ም. ለከተማይቱ ማኅበረሰብ እንዲሁም በዚህ የበጋው ዕረፍት በካስተል ጋንዶልፎ ጳጳሳዊ ሕንፃ ለቆይታቸው በተለያየ መስክ አገልግሎት ላበረከቱት እዚያ RealAudioMP3 ለሚገኘው ጳጳሳዊ ሕንፃ ሠራተኞች ብሎም ለጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ ለአልባኖ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማርቸሎ ሰመራሮ፣ ለሰበካው ውሉደ ክህነት ገዳማውያን እና ዓለማውያን ምእመናን ቅዱስነታቸው በየእሁዱ በደገሙት ጸሎት መልአከ እግዚኣብሔር የተሳተፉት ከውጭ እና ከውስጥ መጥ መምእናኖች ለከተማይቱ የመንግሥት አካላትና መስተዳድር አባላት ሁሉ የምስጋና ቃል መለገሳቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
እ.ኤ.አ. ይህ በተገባው ጥቅምት ወር የሚካሄደው የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ፣ የእምነት ዓመት መክፈቻና ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ዝክረ 50ኛው ዓምት ላይ ትኵረት ያደረገ መሆኑን ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን እነዚህ አበይት የቤት ክርስትያን ፍጻሜዎች አስታውሰው፣ በዚህ የበጋው ዕረፍታቸው አነዚህ አበይት ፍጻሜዎች ላይ በማስተንተን ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለማሰናዳት በጸሎትና በአስተንትኖ በጥልቅ ጥናት ጭምር በተገባ ሁኔታ ለማሳለፍ እንዲችሉ ለተቀረበላቸው ትብብር በሁሉም አስፈላጊ ዘርፍ አስተዋጽዖ ላበረከቱት ሁሉ ሲያመሰግኑ፦ ካስተል ጋንዶልፎ ሁለተኛይቱ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የሮማ ጳጳስ መንበር” መሆንዋ ዘክረው፣ “በረቡዓዊ የትምህረት ክርስቶስ አስተምህሮ በየእሁዱ በደገሙት ጸሎት መልአከ እግዚኣብሔር ለተሳተፉት ዓለማውያን ምእመናና እነሱንም በማስተናገድ ጭምር የሓዋርያዊ መንበር ሠራተኞች የሰጡት አስተዋጽኦ የሚደንቅ ነው” ብለዋል።
የአልባኖ ጳጳስ፣ የተለያዩ የጸጥታ ኃይል አስከባሪ አባላት ጳጳሳዊ የስዊዘርላንድ ዘብ፣ የቅድስት መንበር የጸጥታ ኃይል አባላት አለማውያን ምእመናን ካህናት ደናግል ለቅዱስነታቸው ያሳዩት ፍቅር ቅርበትና ክብር ጠቅሰው ከልብ በማመስገን፦ “በቅርቡ በሎረቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በመሄድ የር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ 23ኛው ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለማርያም ጥበቃ ለማስረከብ አልመው የፈጸሙት የሎሬቶ ሐዋርያዊ ጉብኝት ዝክረ 50ኛው ዓመት፣ እንዲሁም አዲስ አስፍሆተ ወንጌል ላይ ያተኮረ በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ሊካሄደው የተወሰነው ሲኖዶስ፣ የእምነት አመት ጅማሬ፣ ማኅበረሰብ ሁለመናውን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ለድህነት ቃሉ እንዲከፍት ለመደገፍ ቤተ ክርስትያን የወጠነችው መርሃ ግብር የሚተገበርበት ወር ነውና ሁሉም ለዚህ ቅዱስ መርሃ ግብር እንዲጸልይ” አሳስበዋል።
ሁሉም የተቀበለው የጥሪ ጸጋ መሠረት ሕይውቱን በመምራት በተገባ ሁኔታ ለመኖር እንዲችል በእምነት ማደገ እንዳለበት ቅዱስነታቸው በማሳሰብ፣ “ጥቅምት ወር የቅድስት ድንግል ማርያም ዘሮዛርየም ወር ነውና እርሷ ሁላችንን በእምነት በመደገፍ የሁሉም መልካም ሃሳብ እግዚአብሔር ይባረከውም ዘንድ ቅድስት ድንግል ማርያም የቤተ ክርስትያን እናት፣ የሁላችን እናት ታማልድልን” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.