2012-10-01 15:13:56

ሶማሊያ፦ አል ሸባብ ኪሲማዮን ለቆ ወጣ


በሶማሊያ የአል ቃይዳ የቀኝ እጅ ተብሎ የሚነገርለት የምስልምና ሃይማኖት አክራሪው ኃይል በአገሪቱ ለሰላምና ጸጥታ ጥበቃ ከተሰማራው የአፍሪቃ ኅብረት ኃይል በተሰነዘረበት ጥቃት ሳቢያ በሰማሊያ RealAudioMP3 ደቡባዊ ክልል ከሚገኘው ዋና ምሽጉ ከሆነው ኪሲማዮ ክልል ለቆ ለመውጣት መገደዱ ሲገለጥ፣ የአል ሸባብ ታጣቂ ኃይል ቃል አቀባይ ታጣቂው ኃይል ኪሲማዮ ለቆ ለመውጣት በገዛ እራሱ የመረጠው ወታደራዊ ስልት ነው ማለታቸው ሲታወቅ።፣ እስላማዊው ታጣቂው ኃይል ኪሲማዮን ለቆ ከመውጣቱ በፊት በጠቅላላ በወህኒ ቤት አጉሯቸው የነበሩትን እስረኞችን ነጻ ሲለቅ፣ ሦስት በስለያ ክስ መስርቶባቸው የነበሩት እስረኞች ላይ የሞት ፍርድ ቅጣታ መፈጸሙ ይነገራል።
በኬይንያ ጦር ኃይሎች የሚመራው በሶማሊያ የአፍሪቃ ኅብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል፣ አል ሸባብ ኪሲማዮን ለቆ ወጥተዋል ሲል በማስታወቅ፣ የኪሲማዮ ጸጥታና ደህንነት በዚህ የአፍሪቃ የሰላም አስከባሪ ኃይል እጅ ቁጥጥር ሥር እንደሚሆን ገልጠዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ተከስቶ ያለው ሁኔታ የአል ሸባብ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ጫካ በመመለስ በክልሉ በሚገኙት የጸጥታ ሃይል አባላትና በሶማሊያ የመከላከያ ኃይል አባላት ላይ የተለያዩ ያጥፍተህ ጥፋና የደፈጣ ጥቃቱን ለማጧጧፍ የሚገፋፋው ሊሆን እንደሚችል ይነግራል።







All the contents on this site are copyrighted ©.