2012-09-28 14:05:30

የቅድስት መንበር ለወንድማማችነት ለሰላምና ለፍትህ ጥበቃ አስተዋጽኦ


የቅድስት መንበር የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ዶሚኒክ ማምበርቲ ክትላትና በስትያ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተገኝተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የልኡካነ መንግሥታት ደህንነትና ጸጥታ ጥበቃ ለማረጋገጥ የደነገገው ውሳኔ እርሱም በልኡካነ መንግሥታት ላይ ሊፈጸም RealAudioMP3 የሚችለውን ወንጀል ቀድሞ ለመቆጣጠርና ለማስወገድ የሚያዘው ውሳኔ ቅድስት መንበር የምትከተለው መሆኑ በይፋ የሚገልጥ ሰነድ ማስረከባቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ወንድማማችነት ፍትህና ሰላም በሕዝቦች መካከል እውን ለማድረግ የሕግ ልኡላዊነት እንዲጠበቅ ቅድስት መንበር የምታምንበትና በሁሉም ዘንድ ገቢራዊ እንዲሆን ቅስቀሳ የምታካሂድበት ክብር መሆኑ የሚያብራራው ብፁዕ አቡነ ማምበርቲ ለተባበሩት መንግሥታት ባስረከቡት ሰነድ መጠቀሱ ያስታወቀው የቅድት መንበር መግለጫ በማያያዝ፣ በተባበሩት መንግሥታት የጸደቀው የልኡካነ መንግሥታት ሕይወት ዋስትና የሚመለከተው ውሳኔ ይኸንኑ ሃሳብ የሚያበክር መሆኑና ቅድስት መንበር በሕግና ፍትህ የዓለም አቀፍ ሥርዓት እርሱም ወንጀል ለመቆጣጠር በሚድረገው ሂደት ትኩረት ብቻ ሳይሆን ለደንቡ ገቢራዊት አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት የሰው ልጅ ሰብአዊ ክብርና ሰላምን የሚያናጉትንን የወንጀል ቡድኖች እንቅስቃሴ ለመግታት በሚደረገው ጥረት ትብብር የምታደርግ መሆንዋ የሚያረጋገጥ እንደሆነም አስታውቀዋል።
ቅድስት መንበር የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔ ተከትሎዋ በይፋ ስታስታውቅ፣ የልኡካነ መንግሥታት ደህንነት ዋስትና እንዲያገኝ ብቻ ሳይሆን ለአሸባሪያን ጥቃት ኢላማ ሊሆኑ ይችላሉ ለሚባሉት አካላትና ክልሎች የሚሰጠው የጸረ አሸባርያን ጥበቃ ንቁ እንዲሆን የሚል ጭምር መሆኑ ብፁዕ አቡነ ማበርቲ ባስረከቡት ሰነድ ተመልክቶ እንደሚገኝም የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.