2012-09-28 14:02:35

በይሎሩሲያ፦ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ


በበይርሎሩስያ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ብፁዕ አቡነ ክላውዲዮ ጉጀሮቲ በአገሪቱ በሚገኙት ወህኒ ቤቶች ሐዋርያዉ ጉብኝት እንዲያካሂዱ ላቀረቡት ጥያቄ ከአገሪቱ መንግሥት በተሰጣቸው ፈቃድ መሠረት በኮቫለንኮ ስይሮሞሎኦቶቭ ስታትከቪች በሊያኪ ዳንሺየቪክ ሎቦቭና ሰቨሪነች የሚገኙት ወህኒ ቤቶች RealAudioMP3 የጎበኙ ሲሆን፣ መንግሥት የሰጠው ፈቃድ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ኩላዊ ግብረ ገብ ሥልጣንና የቅድስት መንበር ሰብአዊ አገልግሎት የሚመሰክርና እውቅና የሚሰጥ ምልክት መሆኑ ተገለጠ።
ብፁዕ አቡነ ጉጀሮቲ በጎበኙዋቸው የበይሎሩሲያ ወህኒ ቤቶች ከሁሉም እስረኞች ጋር በመገናኘት ስለ ሁኔታቸውና በወህኒ ቤት ያለው ደንብና ሥርዓት በተመለከተ ከሁለተኛ አካል ሳይሆን በቀጥታ በወህኒ ቤት ካሉት እስረኞች አፍ በማዳመጥ፣ በአገሪቱ የእስረኞች ሁኔታ በቀጥታ ከሚመለከተው የአገሪቱ ዜጋ መረጃ እንዲያገኙ ማገዙ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ለሁሉም በወህኒ ቤቱ ለሚገኙትና ለቤተሰቦቻቸውም ጭምር የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ቅርበትና በቅዱስነታቸው ጸሎት ኅያዋን መሆናቸው እንዳረጋገጡ አስታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.