2012-09-28 13:58:19

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ የቅዱስ አጎስጢኖስ ወቅታዊነት


በጀርመን ሰሜናዊ ባቪያራ የሚገኘው ከዉርዝቡርግ ሰበካ ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ክብር ቅዱስነታቸው ለእረፍት በሚገኙበት ካስተል ጋንዶልፎ ሐዋርያዊ ሕንጻ አጎስቲኑስ የተሰየመም የቅዱስ አጎስጢኖስ ሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያዊ ፍልስፍናዊ ድረሰቶችን ማእከል ያደረገ ለክብራቸው የቀረበው የውሁድ RealAudioMP3 ጥዑም ሙዚቃ ትርኢት መከታተላቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው በትርኢቱ ማብቅያ ባሰሙት ቃል፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ ለወቃዊው ዓለም ተጋርጦና መሰረታውያን ጥያዌዎች መልስና መወጣጫ መንገድ የሚጠቁም ወቅታዊነት ያለው መሆኑ በማብራራት፣ የዚህ የቤተ ክርስትያን አቢይ አባት ሊቅ ቅዱስ ወቅታዊነት የቤተ ክርስትያን ነቢይነት ባህርይ የሚያጎላ ነው እንዳሉ የገለጠው የቅድትስ መንበር መግለጫ አያይዞ የተለያየ የውሁድ ጥዑም ሙዚቃዊ ኅብረ ቅኝት ተክኖ የቀረበው የሚዚቃ ትርኢት የቅዱስ አጎስጢኖስ የቲዮሎጊያ የሥነ መንፈሳዊነት የፍልስፍና ሊቅነት በጠቅላላ ምሉእ ሊቅነቱ የሚያጎላ ከመሆኑም ባሻገር ቅዱስ አጎስጢኖስ ለማወቅ የምናደረገው ጥረት የተቆናጸበ ሳይሆን ምሉእነት ያለው እንዲሆን የሚያነቃቃ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
የቅዱስ አጎስጢኖስ ኅልውና በጊዜ እና በወቅት የሚታጠር እንዳልሆነም ከድርሰቶቹ ለመገንዘብ እንችላለን ያሉት ቅዱስ አባታችን አክለውም፣ ለሰው ልጅ ውስጣዊ ትግል ጭንቀትና አለ መርካት ቅዱስ አጎስጢኖስ እጅግ ቅርብ መሆኑና፣ ሰብአዊ ፍጡር እውነትን እግዚአብሔርን ለመፈለግ የሚያደርገወ ጥረት የሚመሰክር፣ የሰው ልጅ እውነትና ፍጹምነት የመሻት ባህርይ ለቅዱሳን ብቻ ሳይሆን ሰብአዊ ፍጡር የሚመለከት መሆኑ ያረጋግጥልናል ብለው በመጨረሻ የውሁድ ሙዚቃ ቅኝት ትርኢት ላቀረበላቸው የዉርዝቡርግ ሰበካና ትርኢቱ እንዲረጋገጥ አሰተዋጽኦ ለሰጡትን ሁሉ አመስግነው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.