2012-09-24 15:15:42

የር.ሊ.ጳ የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ (23.09.12)


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በካስተል ጋንደልፎ ሓዋርያዊ አደራሽ ከምእመናን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት ባቀረቡት አስተምህሮ “በመካከለኛ ምሥራቅ ስለሚገኙ ክርስትያኖች ስለ ሰላም መጸለይ እንዳለብን” አሳስበዋል፣ RealAudioMP3
ቅዱስነታቸው በአስተምህሮአቸው ባለፈው ሳምንት በሊባኖስ ያደረጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በማስታወስ ለስኬታማነቱ ዋና የሆነው የምእመናኑ ጸሎት ስለሆኑ ለሁላቸው በጸሎት ለሸኝዋቸው ምስጋና አቅርበዋል፣ በተለያዩ ቋንቋዎች ምስጋናና ትምህርት ባቀረቡበት ወቅት ለፈረንሳየኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ባቀረቡት ሰላምታና ምስጋና “ስለ መካከለኛ ምሥራቅ ክርስትያን መጸለይ እንድትቀጥሉ ይሁን እንዲሁም ስለ መካከለኛው ምሥራቅ ሰላምና በሃይማኖትች መካከል ጤነኛ ውይይት እንዲካሄድ ጸልዩ” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ባቀረቡት ትምህርት “በምሳሌ ለመናገር ያህል ዛሬ በተነበበው ወንጌል ሁለት የተለያዩ የሞገድ ርዝመቶች እንዳሉ ይታያሉ ማለትም ሐዋርያቱ የጌታን ንግግር ከነጭራሽ አይረድዋቸውም ነበር ወይንም ጥልቀት በሌለው አመለካከት እንደነግሩ ይሰሙት ነበር ለማለት ይቻላል፣ ከጥቂት ግዝያት በፊት እምነቱን ለኢየሱስ የገለጠው ቅዱስ ጴጥሮስ፤ ጌታ ስለሕማማቱ በትንቢት ሲገልጥ ይህ ባንተ አይድረስ በማለት ዕንቅፋት ሲሆንና ጌታም ሰይጣን ከኔ ራቅ ሲለው እጅግ ይገርማል፣ ሁኔታውን ጠለቅ ብለን የተመለከትን እንደሆነ ሁለት የተለያዩ አስተሳሰቦች እንደሉ እንመለከታለን፣ አንዱ የእግዚአብሔር መንገድ ሲሆን ሌላው ደግሞ የሰው ልጆች አመክንዮ ወይም ሎጂክ ናቸው፣ ጌታን ለመከተል የሰው ልጆች ጠለቅ ያለ ለውጥ ያስፈልጋቸዋል፣ ይህ ለውጥ የአስተሳሰባቸውና የኑሮአቸውን ሁኔታ ከነጭራሱ የሚለውጥ መሆን አለበት፣ የሚያስፈልገውም ልባችንን ለቃለ እግዚአብሔር ክፍት በማድረግ ውሳጣዊ ብርሃንና ለውጥ እንዲያገኝ መፍቀድ ነው፣
“እግዚአብሔርና የሰው ልጆች የሚለያዩበት ዋነኛ ቍልፍ ትዕቢት ነው፣ በእግዚአብሔር ትዕቢት የለም፣ እርሱ ፍጹም ስለሆነ ለማፍቀርና ሕይወት ለመስጠት ሁሌ ዝግጁ ነው፣ እኛ የሰው ልጆች ግን ትዕቢት የወረረን ስለሆንን ራሳችንን ከትዕቢት መጠበቅና ከዚሁ መንጻት ያስፈልገናል፣ ይህም ሁሌ እስከ መጨረሻ መከታተል ያለብን ጉዳይ ነው፣ በተፈጥሮአችን ትናንሽ የሆንን እኛ ሁሌ ትላልቅ ሆነን መታየት እንመኛለን፣ እንዲሁም አንደኛ ቦታ ይዘን መጓዝ እንወዳለን፣ በተፈጥሮው አንደኛና ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔር ግን ዝቅ በማድረግ የመጨረሻውን ቦታ እንሰጣለን፣ ሆኖም እግዚአብሔር ዝቅ ለማለትና የመጨረሻ ለመሆን አይፈራም፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም ይህንን ሁሉ ተረድታ በትሕትናዋ ከእግዚአብሔር ጋር የምትስማማ ስለሆነች ትሕትና እንድታስተምረንና ከእግዚአብሔር እንድታማልድልን እንማጠናት በማለት ካሳሰቡ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.