2012-09-24 14:35:10

የህዝብ ንብረትና ሃብት ለሕዝባዊ አገልግሎት ማስፈጸሚያ


የሮማ ኅየንተ ብፁዕ ክርዲናል አጎስቲኖ ቫሊኒ ለሮማ ሰበካ ሳምታዊ መጽሔት በቅርቡ በኢጣሊያ በተለያዩ ክፍለ ሃገሮች በተለይ ደግሞ በላዚዮ ክፍለ ሃገር በሕዝባዊ ሃብት እርሱም ለሕዝባዊ አገልግሎት ማስፈጸሚያ የገንዘብ ሃብት ለግል ጥቅም ማዋል የሚታየው የማባከንና አለ አግባብ የሕዝብ ንብረት ለግል ጥቅም የማዋሉ RealAudioMP3 በመታየት ላይ ያለው የምግባረ ብልሽውና ወንጀል በማስመልከት ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ተከስቶ ባለው የኤኮኖሚና የቁጠባ ቀውስ ምክንያት፣ ቤተ ሰቦች ዜጎች ለኤኮኖሚ ችግር ተጋልጠው፣ ያለው የኤኮኖሚ ቀውስ ለመቅረፍ በሚጠይቀው መርሃ ግብር በመሳተፍ መሥዋዕትነት እየከፈሉ ባሉበት ወቅት አንዳንድ የከተማ መሥተዳድር አባላትና የፓለቲካ አካላት ለሕዝባዊ አገልግሎት ማስፈጸሚያ መዋል የሚገባው የገንዘብ ሃብት ለግል ጥቅም ለማዋል ሲራወጡና ሲያባክኑ ማየቱ እጅግ የሚያሳዝን በዝምታ መታለፍ የማይገባው ወንጀል ነው” በማለት “ሁሉ ካለው ኃላፊነት አንጻር ጋር የሚስተካከል ገብረ ገባዊ ኃላፊነት አለው፣ ስለዚህ ተጠያቂነቱ በዚህ የሚመዘን ነው” ብለዋል።
“La Civiltà Cattolica-ካቶሊካዊው ሥልጣኔ” ለተሰየመው የኢጣሊያ የኢየሱሳውያን ማኅበር ለሚያዘጋጀው ሳምንታዊ መጽሔት ምክትል ዋና አዘጋጅ አባ ሚከለ ሲሞነ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ሕዝብ በፖለቲካ ሰልፎች ላይ ያለው እምነቱ ሲያሽቆለቁል፣ ሕዝብ ያመጣው ምርጫ ሳይሆን፣ የፖለቲካ ሰልፎች የተሰጣቸው ኃላፊነት አለ መወጣት የቀሰቀሰው ተግባር ነው። የፖለቲካ ሰልፎች በተለያዩ የውይይት መድረኮች ሳይቀር የሚታይባቸው ፖለቲካዊ መንተባተብ፣ የሚነዙት ንግግር ከላቸው ኃላፊነት አንጻር ጋር ሲገምገም እምብዛም የማያሳምን ሆኖ ነው የሚገኘው። ይህ ሳይበቃ የሚያሳይቱ ምግባረ ብልሽት የሕዝቡ በፖለቲካ ሰልፎች ላይ ያለው እምነት ከዜሮ በታች እንዲወርድ ያደረገ ጉዳይ በአሁኑ ሰዓት በመስፋፋት ላይ ላለው ለጸረ ፖለቲካ-የፖለቲካ እንቅስቃሴ ምክንያት ሆነዋል። በሌላውም ረገድ የአንዳንድ የፖለቲካ አካላት ምግባረ ብልሽት ሕዝብ በብሔራዊ ምርጫ ለድምጸ ተዓቅቦ ውሳኔ የሚገፋፋ፣ የመምረጥ መብት ያለው ድምጽ ከመስጠት መቆጠብ እንዲል የሚገፋፋ፣ የድምጸ ተዓቅቦ መራጭ ህዝብ ብዛቱ ከፍ የሚያደርግ ነው” ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባለፈው ቅዳሜ ክርስትያን ዴሞክራሲ የፖለቲካ ሰልፎችን የሚያቅፈው ዓለም አቀፍ የክርስትያን ዴሞክራሲ ማኅበር አባላትን በመቀበል በሰጡት መሪ ቃል፦ “መጽሐፈ ጥበብ ጠቅሰው፣ ሁሉም ካለው ኃላፊነት አንጻር የሚገመገምና የሚሰጠውም ፍርድ የእያንዳንዱ የኃላፊነት ደረጃ ግምት የሚሰጥ፣ ሁሉ እንደየ ኃላፊነት ይመዘናል የሚል ነወ ሲሉ፣ ተስፋ ለማስቆረጥ ሳይሆን ሁሉ ከተሰጠው ኃላፊነት ጋር የሚስማማ ሕይወት እንዲኖር፣ ዕለታዊ ሕይወት ከሚሰጠው ኃላፊነት ጋር በማጣመር መኖር የሚያነቃቃ፣ ከሚሰጠው ኃላፊነት ጋር የሚመዛዘን የበቃ ሕይወት እንዲኖር የሚመክር ቃል ነው” ብለው፣ “በአሁኑ ሰዓት በመስፋፋት ላይ ያለው የተዛማጅ ባህል ማለትም ሁሉም ያው ነው የሚል ሁሉንም በአንድ ደረጃ ደምድሞ የሚያስቀምጥ ዝግመትና ልቅ ባለ ቤትነት ባህል መስፋፋት መሠረት የሚታየው ጉድለት በማኅበረሰብአዊነት ሥር እንዳይጤን የማድረጉ ግፊት በማሕበራዊ ሕይወትና በፖለቲካው ዓለም ጭምር የሚታይ ነው። ይኽ አይነቱ ሂደት ተኃድሶ የሚያግድ መንገድ ነው” ካሉ በኋላ በመጨረሻ ወቅቱ የፖለቲካ ሰልፎችና የፖለቲካ አካላት ኅዳሴ ምንኛ አስፈላጊ መሆኑ የሚያሳስብ ከመሆኑ ባሻገር መራጩ ሕዝብ ለፖለቲካ ሰልፎች የሚሰጠው ግምገማም ሆነ ገዛ እራሱ ለፖለቲካ ሰልፍ የአባልነት ምርጫው በርእዮተ ዓለማዊ ስበት ሳይሆን ግብረ ገብ ላይ የጸና እንደሚሆን በማድረግ የመራጩ ሕዝብ አዲስ መልክአ ምድራዊ ቅርጽ የሚያሰጠው ሁኔታ መሆኑ በማብራራት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.