2012-09-24 14:47:07

ቺለ፦ አራተኛው የካቶሊካውያንና የማኅበራዊ ሕይወት ቀን


እ.ኤ.አ. በሚቀጥለው ጥቅምት ወር 2012 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሳምንት የቺለ አራተኛው የካቶሊካውያንና የማኅበራዊ ሕይወት ቀን እንደሚታሰብ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ የካቶሊካዊያንና የማኅበራዊ ሕይወት RealAudioMP3 ጉባኤ በአገሪቱ አንቶፋጋስታና ኮንሰፕሲዮን ከተማ የሚከናወን መሆኑ የገለጠው ፊደስ የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ማኅበራዊ ድረ ገጽና የድጋፍ ድረ ገጽ የሚያነቃቃ ማለትም ድረ ገጽ መሣሪያ አገልግሎት ለሁሉም ጥቅም ለሰብአዊ እድገት የሚበጅ እንጂ የሰው ልጅ ክብር ለሚቀናቀን ተግባር መዋል እንደማይገባው በጥልቀት አስተምህሮ የሚሰጥበትና ውይይት የሚደረግበት ጉባኤ እንደሚሆን በማስታወቅ፣ ይህ በሳንቲያጎ ደል ቺለ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ ቶማስ ዘ አኵይኖ መንበረ ጥበብና በቺለ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት በመተባበር የሚዘጋጀው ጉባኤ ዋነኛው ዓላማም ወንጌል ሁሉንም የሁሉንም የሕይወት ገጽታ የሚያበራ መሆኑ በማስተንተን በዚህ ዘርፍም ምሁራንና የባህል አካላትን ለውይይት ማነቃቃት የሚል መሆኑም የዜናው አገልግሎት አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.