2012-09-24 14:43:54

ብፁዕ አቡነ ፊዚከላ፦ ቃለ እግዚአብሔር ለዓለም ማስተላለፍ


የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሪኖ ፊዚከላ ትላንትና የተጠናቀቀው የኢጣሊያ ብሔራዊ የካቶሊክ ተግባር ማኅበራት ሊቀ መናብርትና በሰበካዎች የካቶሊክ ተግባር ማኅበራት ተጠሪዎች ያሳተፈው ጉባኤ ለማስጀመር ያረገው መሥዋዕተ ቀዳሴ መርተው ባሰሙት RealAudioMP3 ስብከት፦ ቃለ እግዚአብሔር ወደ ሁሉም ሥፍራ ማድረስ የሁሉም ክርስትያን ጥሪ ነው። ካሉ በኋላ የጉባኤው መርህ ቃል እምነትና ግብረ ገብ ለተካነ መልካም ሕይወት፣ ካቶሊክ ተግባር፣ የአካባቢ ቤተ ክርስትያንና ኵላዊት ቤተ ክርስትያን” የተሰኘውን ጠቅሰው ከጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመቀጠል የእርሱን ዱካ በመከተል ሁላችን ቃሉን ለመዝራት የተጠራን ነን ያሉት ብፁዕ ኣቡነ ፊዚከላ አያይዘው “ኃላፊነታችንም የማንኛውም ዓይነት ቃል ዘሪዎች አለ መሆናችን ነው” ምክንያቱም የጌታችን ሥራ ቢሆንም ለእግዚአብሔር ቃል ፍርያማነት “ዘሪው የሚዘራውን ዘርና ዘሩን የሚያኖርበት መሬት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባዋል። በቃሉ የተለወጠ የሚዘራው ቃል ፍርያማነቱ የተረጋገጠ ነው። ስለዚህ እውነተኛው ልኡክ እውነተኛ የጌታ ቃል አብሳሪ በአጋጣሚ ተኩኖ የሚኖር ተልእኮ አይደለም። እግዚአብሐርንና ቃሉን ማወቅ ወሳኝ ነው” ብለዋል። ቃሉን ያመነ ሁሉ የሰው ልጅ ወደ ሚኖርበት ሥፍራ ሁሉ ቃሉ ለማድረስ መጠራቱ እንዲገነዘብ በሚያብራራ መልክ አጠር በማድረግ የአዲስ አስፍሆተ ወንጌል ዓላማና ትርጉሙን ማብራራታቸው ለማወቅ ተችለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.