2012-09-24 14:27:19

በቤተ ክርስትያን አገልግሎት የሰላም መሣሪያ


እ.ኤ.አ. ከባለፈው ጥር 2012 ዓ.ም. የሐዋርያዊ ቤተ ኑዛዜ ልኂቅ ዓቢይ አለቃ ብፁዕ ካርዲናል ፎርቱናቶ ባልደሊ በጠና ታመው በሕክምና ሲረዱ ቆይተው እ.ኤ.አ. ዓርብ መስከረም 21 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው መገለጡ የሚታወስ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ፣ RealAudioMP3 ብፁዕ ካርዲናል ባልደሊ ትጉህ ለሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎትና ለወንጌል ታማኝነት አብነት በማለት የሚገልጣቸው የሐዘን መግለጫ መልእክት ማስተላለፋቸው የጠቆመው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ፣ ቅዳሜ ልክ ከምሽቱ 06 ሰዓት በሮማ ሰዓት አቆጠጠር በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ያረገው የግብአተ መሬት ሥርዓተ ቅዳሴ የመሩት የብፁዓን ካርዲናሎች አፈ ጉባኤ ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ሶዳኖ ባሰሙት ስብከት፣ ነፍሰ ኄር ብፁዕ ካርዲናል ባልደሊ መላ ሕይወታቸው ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት የሰዉ፣ ቤተ ክርስትያንን በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ በመሆን በተለያዩ አገሮች ተልከው ያገለገሉ፣ በኢጣሊያ ኡምብሪያ ክፍለ ሃገር፣ በፐሩጃ አውራጃ ከተማ ቫልፋብሪካ የተወለዱ በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘ አዚዚ መንፈሳዊነት የታነጹ የኡምብሪያ ሰበካ ካህን ትሁት የዋህና ባለ እንጀራ እንደ ገዛ እራስ በሚያፈቅር ክርስትያናዊ ሕይወት የሚደነቁ የቅዱስት መንበር ልኡክነት አገልግሎታቸው በወንጌላዊ ብፅዕና መርህ በመግለጥ በአንጎላ በሳው ቶመና ፕሪንሰ በረፓብሊካዊት ዶመኒካን በፐሩ ቀጥለው በስትራስበርግ በኤውሮጳ ኅብረትና በፈረሳይ የቅድስት መንበር ልኡክ በመሆን ያገለገሉ የሰላም መሣሪያ የቤተ ክርስትያን ልጅ” በማለት እንደገለጡዋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.