2012-09-21 13:42:26

የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ፦ የሃይማኖት ምልክቶችን ማክበር


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ በአሁኑ ወቅት ጸረ ሃይማኖት የሆኑትን ሃይማኖትን የሚያረክሱ እየተፈጸሙ ያሉት ተግባሮች ርእስ ሥር የሰጡት መግልጫ ከካይሮ የአል አዝሃር ታዋቂው የምስልምና ሃይማኖት መንበረ ጥበብ አድናቆት እንደተሰጠበት ተገልጠዋል።
ሃይማኖትን የሚያረክስ የሚያንቋሽሽ ተግበር በተባበሩት መንግሥታት ጭምር በጥንካሬ የተወገዘ ሆኖ፣ በቅርቡ የተቀረጸው የምስልምና ሃይማኖት የሚያረክስ ተብሎ የሚነገርለት የተቀረጸው የድምጽና ምስል ትርኢት እንዲሁም በፈረንሳይ፣ ቻርሊየ ሀብዶ ያወጣው የቀልድ አስቂኝ ንድፍ የምስልምና ሃይማኖት የሚያርከስ ነው ተብሎ የሚነገረለት በተለያዩ አገሮች ለተጨማሪ የተቃውሞ ሰልፍ ምክንያት እየሆነ መምጣቱ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ ጉዳይ ለተለያየ አደጋ ሊያጋልጥ ይችላል በሚል ጥረጠራም ፈረንሳይ በ 20 አገሮች የሚገኙትን የወኪሎች ቢሮ በመንግሥቷ መወሰንዋ ለማወቅ ሲቻል፣ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ጭምር በኢንዶነዢያ የሚገኘው የልኡከ መንግሥት ቢሮው እንዲዘጋ ወስኗል።
በአፍጋኒስታን በፓኪስታን ጸረ ፈረንሳይና ጸረ የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ያቀና ሰላማዊ ሰልፍ እየተካሄደው መሆኑ ሲገለጥ፣ ነቢይ መሃመድን የሚያንቋሽሽ የምስልምና ሃይማኖት የሚያረክስ በሰሜን አመሪካ የተደረሰው የተቀረጸው የድምጽና ምስል ትርኢት የቀሰቀሰው የተቃውሞ ሰልፍ ብርቱና ለተለያዩ አደጋ ሊያጋልጥ እንደሚችል የሚነገርለት፣ የተባበሩት መንግሥታ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን ሃሳብህን የመግለጥ መብትና ክብር በማንምና በምንም ምክንያት መጣስ የሌለበት የሰብአዊ መብትና ክብር እንዱ ክፍል ቢሆንም ቅሉ የሌልውን ክብር ለመንካትና ለመድገር የሚፈቅድ ማለት እንዳለሆነ በማስታወስም፣ የተደረሰው ጸረ የምስልምና ሃይማኖት የድምጽና የምስል ትርኢት እንቅፋትና አስነዋሪ ተግባር ነው በማለት ገልጠዉታል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በፈረንሳይ የጸጥታና የደህንነት ጥበቃ ኃይል፣ ነገ ፓሪስ በሚገኘው መስጊድ ፊት ባለው አደባባይ፣ በሰሜን አመሪካ የተደረሰውና የተቀረጸው ጸረ የምስልምና ሃይማኖት የድምጽ ምስል ትርኢት በመቃወም የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በኅብረት ተቃውሞአቸውን እንዲያሰሙበት የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ አድማ ውጥረትና ሁከት ሊቀሰቅስ ይችላል በሚል ስጋትም ለሁሉም ጸጥታና የሕይወት ደህንነት ዋስትና ምክንያት እንዳይካሄድ ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.