2012-09-21 13:30:08

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሎሬቶ ሐውጾተ ኖውሎ መርሃ ግብር ይፋ ሆነ


ከቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ትላትና ከተሰጠው መግለጫ ለመረዳት እንደተቻለው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. የር.ሊ.ጳ. ዮሐንስ 23ኛ የሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ዝክረ 50ኛው ዓመት ሐውጾተ ኖልዎ ምክንያት በሎሬቶ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ ሐውጾተ ኖልዎ RealAudioMP3 እንደሚያካሂዱ ታውቀዋል።
እ.ኤ.አ. ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ከአገረ ቫቲካን በሄሊኮፕተር በመነሣት በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከጠዋቱ 10 ሰዓት ሎሬቶ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማእከል ደርሰው ቀጥለው ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በመሄድ በቁዱስ ቁርባን ፊት አስተንትኖና ማርያማዊ ጸሎት ደግመው እንዳበቁም ልክ በ10.00 ሰዓት ክሰላሳ ደቂቃ በዚያ ቅዱስ ማርያማዊ ቅዱስ ሥፍራ በሚገኘው አጸደ መሥዋዕተ ቅዳሴ መርተው ከፈጸመ በኋላ 01 ሰዓት ከ 15 ደቂቃ በሞንቶሮሶ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ማእከል በሚቀርብላቸው የምሳ ግብዣ ማዕድ ተቋድሰው ቆይታ በማድረግ፣ በኢጣሊያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀትር በኋላ ልክ 05.00 ሰዓት ቫቲካን ወደ ሚገኘው ሐዋርያዊ መንበራቸው ተነስተው ልክ 06.00 ሰዓት ላይ አገረ ቫቲካን እንደሚደርሱ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ ይጠቁማል።








All the contents on this site are copyrighted ©.