2012-09-21 18:21:35

ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል ታማኝ ምስክሮች ያስፈልጋሉ፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና በካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ የአዲስ ጳጳሳት ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል፣ ጳጳሳቱ ለተለያዩ ሃገረ ስብከቶች ለማገልገል በቅርቡ የተሾሙ ሲሆኑ ስለ ጳጳሳት የሚያስብ ማኅበር ለስልጠና ባዘጋጀው ጉባኤ ተሳትፈው በጉባኤ ፍጻሜ ላይ ነው ከቅዱስነታቸው ጋር የተገናኙት፣ ቅዱስነታቸው ጳጳሳቱ “እግዚአብሔርንና የሰው ልጆችን ለማገልገል የተጠሩ በመሆናቸው በዘመናችን ታማኝ የስብከተ ወንጌል ምስክሮች የሚይጠይቅ ስለሆነ ከእሳቸው የሚፈለገውም ይህ ስለሆነ ታማኝ የስብከተ ወንጌል ምስክሮች በመሆን የጌታ ወንጌልን እንዲያበስሩ” አደራ ብለዋል፣
እያንዳንዱ ሰው ባለበት ሁኔታ ከክርስቶስ ጋር እንዲገናኝና ጽኑ እምነት እንዲኖረው መርዳት ያለባቸው ጳጳሳቱ መሆናቸውን ያመለከቱ ቅዱስነታቸው ለጳጳሳቱ አጥበቀው የለመኑት ለእንተላዕለ ኩሉ ቤተ ክርስትያን የእምነት አንድነት እንዲጠብቁ አሳስበዋል፣ እምነት ታማኝ ምስክሮች ያስፈልገዋል ለዚህም ጳጳሳት መጀመርያ የእምነት መስካሪ ስለሆኑ የእምነት ሕይወት በመኖር ምእመናኑን በምሳሌ መሸኘት እንዳለባቸው አሳስበዋል፣
“በቅድምያ የእግዚአብሔር አገልጋይ ሳይሆኑ የሰው ልጆች አገልጋዮች መሆን አይቻልም፣ ይህንን አገልግሎት በድል ለመወጣት ከሁሉ አስቀድማችሁ ግላዊ ቅድስናችሁን ለመጠበቅ በየዕለቱ በጸሎት የእግዚአብሔር ቃልን በማሰላሰልና በቅዱስ ቁርባን እየተመገባችሁ ለአገልግሎታችሁ የሕይወት ኃይል ምንጭ ሆኖ እንደደም ሥር መሆኑን መዘንጋት የለባችሁም፣” ሲሉም ጳጳሳት በቅድስና የተካኑ በቃላቸውና በተግባራቸው ምሳሌ እንዲሆኑ አደራ ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው አያይዘው በቅርቡ ሊካሄድ ታቅዶ ባለው የአዲሱ ስብከተ ወንጌል ሲኖዶስ በማስታወስ በምሥጢረ ጥምቀት የቤተ ክርስትያኑ አካል የሆኑ ምእመናን ሁላቸው ለስብከተ ወንጌል የተጠሩ ናቸው፣ ጳጳሳትም ለዚህ ተልእኮ መሳካት ሱታፌና መተባበር እንዲኖር በየሃገረስብከቶቻቸው ብርቱ ጥረት ማድረግ እንዳለበቸው እንዲህ ሲሉ ተማጥነዋል፤ “ስብከተ ወንጌል የልዩ ሰዎች ሥራ ብቻ አይደለም፤ ነገር ግን መላው ሕዝበ እግዚአብሔር በእረኞቹ ተመርቶ ማድረግ ያለበት ተልእኮ ነው፣ እያንዳንዱ ምእመን በማኅበረ ቤተ ክርስትያንና ከእርሷ ጋር በመሆን ቃለ ወንጌልን መስበክና መመስከር እንዳለበት ኃላፊነት ሊሰማው ይገባል” ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው ለስብከተ ወንጌሉ ተግባራዊነት አደራ ካቀረቡ በኋላ ያተኮሩበት ሌላ ነጥብ ስለ ትምህርቱ ወይንም ስብከቱ የእምነት ይዞታ ነው፣ ባለንበት ዘመን ለሚነሱ የእምነት ጥያቄዎች ሁሉ በደንብ ለመመለስና ለማስረዳት እንዲቻል ዘንድ ጳጳሳት የእምነት መሠረታዊ ይዘትን አጠር ባለ ትምህርት እንዲያዘጋጁ በዚህም ለብዙ የዘመናችን ጥያቄዎች መልስ ሊገኙ እንደሚቻል አሳስበዋል፣ የዚህ ዓይነት አጭር ትምህርተ ክርስትያን መልስ ለመስጠት ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ክርስትያን ጽኑ መንፈሳዊ ሕንጸት እንዲኖረውም ይረዳል፣
ቅዱስነታቸው በመጨረሻ ያስታወሱት ነገር ሁለተኛ የቫቲካን ጉባኤን ነበር፣ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የአዲስ ስብከተ ወንጌል የአዲስ ጴንጠቆስጤ በር ከፋች መሆኑን ገልጠዋል፣
“የግዝያት ችግሮች ቢኖሩም ቤተ ክርስትያን በሰፋችበትና ተጓዘችበት ቁጥር የዚሁ የአዲስ ጴንጠቆስጤ ውጤቶችና ክትለቶች አልተለይዋትም፣ ይህም ከተቅዋማዊ መዋቅር እስከ መንፈሳዊ ከምእመናን መሳተፍ እስከ መታደስ በመንፈስ ቅዱስና እስከ ቅድስና ይሸኝዋታል፣ ሲሉ የቫቲካን ጉባኤ ድንግጋጌዎችን መርሳት እንደሌለባቸው በማሳሰብ በሐዋርያዊ ቡራኬ ግንኝቱን ደምድመዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.