2012-09-19 14:42:31

ደቡብ ሱዳን፦ "Radio Good News- የአዲስ ዜና" ራዲዮ ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ ላይ አደጋ መጣሉ


በደቡብ ሱዳን የሚገኘው "Radio Good News- የአዲስ ዜና ሬዲዮ ጣቢያ" ለተሰየመው ለካቶሊካዊ ራዲዮ ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ አባ ዶን ቦስኮ ኦኬንግ በአንዳንድ ወጣቶች መደብደባቸውና ይጓዙባት RealAudioMP3 የነብረቸው መኪና መዘረፋቸው ሚስና የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
አባ ዶን ቦስኮ ኦኬንግ ላይ ጥቃት የፈጸሙትን ወንጀለኞችን ለመለየት የክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ምርመራ እያካሄዱ ሲሆን፣ አደጋው የራዲዮ ጣቢያ ተባባሪ ጋዜጠኖችን በመሸኘት ላይ እያሉ የደረሰባቸው መሆኑንም የገለጠው ሚስና የዜና አገልግሎት አክሎ፣ ጥቃቱ የጣሉት ወጣቶች በግል ውሳኔ ተነሳስተው ወይም ሆን ተብሎ በተደረጃ ቡድን የተላኩ መሆናቸው ገና በውኑ የታወቀ ነገር የለም ብለዋል።
አባ ኦከይንግ በደቡብ ሱዳን የሩምበክ ሰበካ አባል የኬንያ ተወላጅ የካቶሊካዊው የአዲስ ዜና ራዲዮ ጣቢያ ዋና አስተዳዳሪ ከመሆናቸው በተጨማሪም የራዲዮ ጣቢያው የሚገኝበት በማሏአል ባድ የቅዱስ ልበ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያን ቆሞስ መሆናቸው ያስታወሰው ሚስና የዜና አገልግሎት አክሎ የኡጋንዳና የኬንያ መንግሥታት በደቡብ ሱዳን የሚገኙት ዜጎቻቸው ለደህንነትና ጸጥታ ዋስትና የጁባው መንግሥት የተቻለው እንዲያደርግ ግፊት ከማድረግ አለመቆጠባቸውንም ያመለክታል።







All the contents on this site are copyrighted ©.