2012-09-19 14:37:25

Il Cortile dei gentili - የአሕዛብ ቅጥር ግቢ፦ ዓለም ከ-ወይም-አለ እግዚአብሔር


እ.ኤ.አ. መስከረም 13ና 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በዚያች ሉተራናዊ ባህልና በተለይ ደግሞ በአሁኑ ወቅት ሃይማኖትና ግብረ ገብ የሚያገል ቅጥ አልቦ ዓለማዊነት ባህል እጅግ በስፋት በሚታይባት ስለ እግዚአብሔርም ሆኖ ባጠቃላይ ሃይማኖታዊ ርእሰ ጉዳይ በማይነሳባት አገረ ስዊድን ጳጳሳዊ የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ምክር ቤት RealAudioMP3 Il Cortile dei gentili - የአሕዛብ ቅጥር ግቢ በሚል ርእስ ሥር አማንያንና ኢአማንያን ሊቃውንትና ምሁራን በአንድ ጥላ ሥር በማገናኘት ስለ ሃይማኖት ነክ ጉዳዮች በተመለከተ በፍልስፍናና በቲዮሎጊያው ብሎም በሌሎች የትምህርት ዘርፎች ሥር ዓውደ ጥናት በማዘጋጀት ከኢአማንያን ጋር ውይይት ለማካሄድ ያስጀመረው መርሃ ግብር መሠረት ማካሄዱ ቀደም ተብሎ መገለጡ የሚዘከር ሲሆን፣ የተካሄደው ዓውደ ጥናት በማስመልከትም የዚህ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃንፍራንኮ ራቫዚ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ “ሃይማኖትና እምነት በግል ደረጃ እንጂ በማኅበራዊ ሕይወት አለ ማንጻባረቅ የሚል ባህል በጎላባትና ገቢራዊነቱ በሚገርም ሁኔታ በሚኖርባት በሲዊድን እግዚአብሔር ርእሰ ጉዳይ አድርጎ መወያየት ማንም የጠበቀው አልነበረም፣ ከዚህ አንጻር ሲታይ ዓውደ ጥናቱ ግቡን መቷል ለማለት ይቻላል። የስዊድን ወቅታዊ የስነ ጽሑፍ ባህል ላይ በማተኮር በዚሁ ባህል ጎልቶ የሚታየው የልቅ አለማዊነት ሥነ ሃሳብ በመለየት ይኽ ባህል ስለ ህልወተ እግዚአብሔር እንዲወያይ ዓለም አለ-ወይም ከ-እግዚአብሔር ጋር በሚል ርእስ ሥር የሚጠይቅ ዓወደ ጥናት ማረጋገጡ ለሁሉም ማስደነቁ፣ በአገሪቱ ሃይማኖት ከማኅበራዊ ሕይወት ጨርሶ የተወገደ በቤተ ክርስትያን ውስጥ ብቻ ታጥሮ መቅረት የዛሬ ሩቅ ጅማሬው ግምት በመስጠት ነው” ብለዋል።
“በስዊድን የሚያምን የማያምን እምነትን እርግፍ አድርጎ የተወው ሁሉ ስለ ሃይማኖትና እምነት በተለይ ደግሞ በይፋ ስለ እግዚአብሔር ይወያያል ብሎ ማንም አልጠበቀውም፣ ትልቅ አግርሞት ሳያሳድርም አልቀረም” ብለዋል።
ዓውደ ጥናቱ በስቶኮልም በሚገኘው በንጉሣዊ የሥነ ምርምር ተቋም እንዲካሄድ ጥረት ያደረጉትና የተካሄደው ዓወደ ጥናት የመሩት በቅድስት መንበር የስዊድን ልእክተ መንግሥት ኡላ ጉድሙንድሶን መሆናቸው ለማወቅ ሲቻል፣ በዚህ ተቋም አንድ የካቶካዊት ቤተ ክርስትያን ካርዲናል ንግግር ሲያሰማ እሳቸው የመጀመሪያ መሆናቸውም ይነገራል። ከዚህ ዓወደ ጥናት ጋር ጎን ለጎን ወጣቶች ያሳተፈ “የአሕዝብ ቅጥር ግቢ ለወጣቶች” በተመሳሳይ ርእሰ ጉዳይ ሥር መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይህ የወጣቶች ዓወደ ጥናት በፍርይሹሰት በሚገኘው በኤውሮጳ አቢይ ተብሎ በሚነገርለት በችግር ላይ የሚገኙትን ወጣቶች ሕንጸት ተንከባካቢ ማእከል መካሄዱ ብፁዕነታቸው ገልጠው፣ ጽኑ እምነት ያላቸውና ኢአማንያን ወጣቶች በበኩላቸውም ጥልቅ ተነጻጽሮ ሲያደርጉ ማየቱ ለሁሉም ሳያስገርም አልቀረም። ኢሃይማኖታዊና ኢግብረ ገባዊ የሥነ ሰብአዊነት ባህል የሚከተል ከጠቅላላ 10 ሚሊዮን የስዊድን ሕዝብ ብዛት ውስጥ አምስት ሺሕ ብቻ መሆኑም ሲነገር፣ ስለዚህ በአገሪቱ ያንዣበበው ስለ ሃይማኖትና ስለ እምነት ግድ የማይለው ባህል በዚህ ዓይነቱ አወደ ጥናት ቀርቦ መግጠሙ ትልቅ እርምጃ ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.