2012-09-17 09:45:10

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የመልአከ እግዚአብሔር ጉባኤ አስተምህሮ


እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እኵለ ቀን ጸሎት መልእከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ በብዙ ሺሕ የሚገመቱ በዚህ 24ኛው ዓለም አቀፍ የሊባኖስ ሐዋርያዊ ዑደት ጸጋ ለመቀበል ለተሰበሰቡት ምእመናን ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ በማለት እስተምህሮ ሲያቀርቡ RealAudioMP3 “በዚህ ዛሬ ሁሉም ክርስትያኖችና የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮች በተገኙበት ዕለት ለእመቤታችን ዘ ሊባኖስ ቅድስት ድንግል ማርያም አመ አምልካ በመማጠን ስለ ሁሉም ለመለኮታዊ ልጅዋ በተለይ ደግሞ ለሶርያ ሕዝብና ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብ የሰላሙ ጸጋ ታማልድልን” ካሉ በኋላ የዚያ ክልል ሕዝብ ስቃይ የሚወልደው ግጭትና አመጽ በቅርበት ለሚያውቀውና ለሚኖረው ሁሉ የሰላም ጸጋ በማርያም አማላጅነት ተማጽነዋል።
አሁንም ያ ክልል የጦር መሣሪያ ድምጽ የሚሰማበት፣ የጋለሞታና አለ ወላጅ የቀሩት ልጆች ዕምባ እየፈሰሰበትም መሆኑ ገልጠው፣ አመጽና ጥላቻ ሕይወቱን ከቧት ይገኛል፣ ሴቶችና ሕጻናት ቀደምት የዓመጹ ስለባ ናቸው፣ ለምን ይህ ሁሉ አስደንጋጭ የጭንቀት ሁኔታ? ካሉ በኋላ የዓለም አቀፍ ማኅበርሰብና አረብ አገሮች በዚያ ክልል ገቢራዊ ሊሆን የሚችል የእያንዳንዱ ሰብአዊ ፍጥሩ ክብር፣ ሰብአዊ መብትና የሃይማኖት ነጻነትን የሚዋስ መፍትሔ ያፈላልጉ ዘንድ ጥሪ አቅርብው፣ “ሰላም ለመገንባት የሚሻ ሌላው መወገድ የሚገባው ጠላት አድርጎ መመልከቱ ግፊት ጭርሶ ማስወገድ ይኖርበታል፣ ካንተ የተለየው ሰው መከበርና መፈቀር ያለበት ሰብአዊነቱን መመለከት ቀላል አይደለም፣ ሆኖም ግን ሰላም ለመገንባትና ወንድማማችነትን ለማጽናት ከተፈለገ መከበር ያለበት ጉዳይ ነው (ዮሕ. 2፣ 10-11፤ ጴጥ. 3፣8-12 ተመልከት)።
ለሊባኖስ ለሶሪያ በጠቅላላ ለመካከለኛው ምስራቅ እግዚአብሔ ሰላሙን እንዲሰጥ፣ የጦር መሣሪያ እሩምታ ሁሉ ጸጥ እንዲያሰኝ አመጽንም እንዲወገድ ሁሉም የህዝቦች ወንድማማችነትን እንዲገነዘቡ በማርያም አማላጅነት ተማጥነው፣ በሥፍራው ከተገኙት ብፁዓን ጳጳሳትና ፓትሪያርኮች ጋር ሆነው፣ ለመካከለኛው ምስራቅ የቅድስት ድንግል ማርያም የእናትነት ጥበቃ ተማጥነው፣ በእግዚአብሔር እርዳታ አስፈላጊ ለሆነው ሰላምና የዘርና የሃይማኖት ልዩነት የማይል ለተወሃደ የወንድማማችነት ኑሮ ግንባታ በመተባበር ሁሉም ለዚህ ዓላማ እንዲጠመድ የሚያስችለው ለውጥ እንዲታደል በማርያም አማላጅነት ተማፅነው ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ደግመው ሐዋርያዊ ቡራኬ ከሰጡ በኋላ በዚህ ሐውርያዊ ዑደት ወደ አረፉበት ሃሪሳ ወደ ሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ልኡክ ሕንጻ መሄዳቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.