2012-09-17 09:52:51

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለአቢያት ክርስትያን ውህደት


ዛሬ በቻርፈት በሚገኘው የሶሪያ ሥርዓት በምተከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ሕንጻ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ከሌሎች አቢያተ ክርስትያን ዓበይት መንፈሳውያን መሪዎች ጋር መገናኘታቸው ሲገለጥ፣ በዚህ የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያንና በሊባኖስ የፕሮተስታንት አቢያተ ክርስትያን መንፈሳዊያን RealAudioMP3 መሪዎች ጋር ተገናኝተው ሓሳብ ለሓሳብ የመለዋወጥ አጭር ውይይት ካካሄዱ በኋላ፣ ለተገኙት የሃይማኖት መሪዎች ሁሉ የደረሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለግሰው ከዚህ የሁሉም አቢያተ ክርስትያን ውህደት የወንጌል ምስክርነት ታማኝነቱን የሚያጎለብት ምስክርነት በማበከር የተካሄደው ግኑኝነት ፍጻሜ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሮማ ሰዓት አቆታጠር ልክ ክሰዓት በኋላ አራት ሰዓት ከ አርባ አምስት ደቂቃ አገረ ቫቲካን ወደ ሚገኘው ሐዋርያዊ መንበራቸው ለመነሳት በይሩት ወደ ሚገኘው ራፊቅ ሃሪሪ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ተዛውረው፣ የሊባኖስ ብፁዓን ጳጳሳት የተለያዩ የመንግሥት አበይት አካላት የሪፐብሊካዊት ሊባኖስ ርእሰ ብሔር በክብርት ባለ ቤታቸው ተሸኝተው የተሳተፉበት የመሰናበቻ ሥነ ሥርዓት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባሰሙት መልእክት ለተደረገላቸው አቀባበልና መስተንግዶ ከልብ አመስግነው፣ የአገሪቱ ርእሰ ብሔር ላስደመጡት መልካም መልእክት እንዲሁም ሐዋርያዊ ጉብኝቱ የተዋጣለት እንዲሆን አቢይ አስተዋጽኦ ለሰጡት ለፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ በቻራ ቡትሮስ ራይን ለሌሎች በሊባኖስ የላቲንና የምስራቅ ሥርዓት ለምትከተለ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ጳጳሳት ምእመናን ካህናት ገዳማውያን የዘርአ ክህነት ተማሪዎች ሁሉንም ከልብ አመስግነው፣ ወደ እናንተ የመጣው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ በመቀበል ያሳያችሁት ፍቅር የአገራችሁ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል የሚመስክረው ሁነት ነው ካሉ በኋላ፣ ደግመው የዚህ ሐዋርያዊ ጉብኝት ዋነኛ የሆነው ዓላውን ዘክረው፣ በማርያም አማላጅነትም የሰላማዊ ማህበራዊ ኑሮ የተለያዩ ሃይማኖቶች የጋራው ሰላማዊ ኑሮ አብነት ለሆነቸው ለሊባኖስ ጸልየው፣ እግዚአብሔር ሊባኖስና ነዋሪዎቿን ይባርክ፣ የደስታና የሰላሙ ብርሃን ይለግስ፣ እግዚአብሔር መካከለኛውን ምስራቅ ይባርክ፣ መለኮታዊ ቡራኬውንም አትረፍርፎ ያድላችሁ በማለት መሰናበታቸው ተገልጠዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.