2012-09-17 09:34:38

ቅዱስ አባታችን ለመካከለስኛው ምስራቅ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የደረሱት ሐዋርያዊ ምዕዳን በመለገስ መሪ ቃል ሰጡ።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የደረሱት ከትላንትና በስትያ ሃሪሳ በሚገኘው በቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ ፍሪማቸውን ያኖሩበት ለመካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት “በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን ድኅረ ሲኖድስ” ርእስ ያደረገው ሐዋርያዊ ምዕዳን እሁድ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ባሳረጉት RealAudioMP3 መሥዋዕተ ቅዳሴ መለገሳቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው የድኅረ ሲኖዶስ ሰነድ በመለገስ ባሰሙት ሥልጣናዊ መልእክት እንዳመለከቱት፦ እ.ኤ.አ በ 2010 ዓ.ም. “ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምስራቅ፣ ሱታፌና ምስክርነት” በሚል ርእስ ሥር “ያመኑት ሁሉ አንድ ልብና እንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር…(ግብረ ሐዋ. 4፣ 32) ቃል መርህ በማድረግ እንዲካሄድ እግዚአብሔር ለሰጠው የመካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ጸጋን ለማመስገን መሆኑ ገልጠው፣ የሲኖዶስ አበው እንዲሁም የብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ ኤተሮቪች ለሰጡት አስተዋጽዖ አመስግነዋል።
ሰነዱን በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሲያስረክቡ አቢይ ደስታ እንደተሰማቸውም ገልጠው፣ የለገሱት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለሁሉም በዚያ ክልል ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ካህናት ደናግል ዓለማውያን ምእመናን ሁሉ ለጥልቅ ጥናትና አስተንትኖ ምክንያት እንደሚሆን ካመለከቱ በኋላ፣ እያንዳንዱ በተጠራበት ተልእኮ አማካኝነት የሚገልጠው ደስታ ታድሶ በዚህ የሱታፌና የምስክርነት ሰነድ ተበረታትቶና ጸንቶ የሰነዱን የሥርወ እምነት ሥነ ቤተ ክርስትያናዊ መንፍሳዊውና ሐዋርያዊው ግብረ ኖልዎ ባጠቃላይ አንቀጻዊው የቤተ ክርስትያን ትምህርት የሚመለከተው ይዞታው እንዲተገብር መጠራቱንም ገልጠው፣ ሁሉም የሊባኖስና ጠቅላላ የመካከልኛው ምስራቅ ምእመናን ክርስቶስ ቀድሞ ያመለከተው የኖረው መንገድ ለመከተል የሚያግዝ ሐዋርያዊ ምዕዳን ነው ብለዋል።
ሰነዱ ለእያንዳንዱ ሰው ቅርብ የሆነው የፍጹም ቅዱስ አንድና ሦስት ለሆነው እግዚአብሔር የሚሰጠው የእምነት የተስፋና የፍቅር ሱታፌ ምስክርነት በአገሪቱና በእያንዳንዱ ማኅበረሰብ ዘንድ ታማኝ የሚያደርግ እንደሚሆን ያላቸው እምነት ቅዱስነታቸው ከገለጡ በኋላ “በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኚ ቤተ ክርስትያን በዚህ ክልል የተረጋገጠው ልዩና የተወደደችው መሬት እውን የሆነው የድህነት አናሥር ምንጭ አማካኝነት ታማኝና ጽናት የተሞላው የሰው ልጅ ለግልጸተ እግዚአብሔር ለሚሰጠው መልስ መንገድ ያመለከተው የአበው የእምነት ዱካ ተከተይ፣ ያለፉት በአንቺ ዘንድ የተወለዱት አርአያ ከሆኑት ቅዱሳኖችሽ የተመሰከረውን ወደዚያ እግዚአብሔር የእያናንዱ እንባ ወደ የሚያብስበት *(ራዕይ 21፣4) ሰማያዊቷ ኢየሩሳሌም ለምታደርጊው ጉዞ መልስ አግኚ” ካሉ በኋላ “የወንድማማችነት ሱታፌ ያ ያንድ ኅብረ ሰው የበኽር ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ የተገለጠው ኵላዊ ወንድማማችነት በክልሉ ለምትገኘው ቤተ ክርስትያን በዕለታዊ ሕይወትዋ እንዲያበረታታት መክረው፣ በዚያ ክልል የዛሬ 2000 ዓመት የተኖረው በቃሉ የተገለጠው ወንጌል ዛሬም እንያስተግባ ነው” ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.