2012-09-17 13:40:27

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ግዜው የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ክርስትያኖች አመጽ ያከትምለት ዘንድ የሚተባበሩት ወቅት ነው”።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሊባኖስ ባካሄዱት 24ኛው ዓለም ዓቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት በሊባኖስ ብከርከ የማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን መንበረ ፓትሪያርክ ሕንጻ ፊት ባለው አጸደ ከሊባኖስና ከተለያዩ RealAudioMP3 የመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የተወጣጡ ከ25 ሺሕ በላይ ከሚገመቱት ወጣቶች ጋር በመገናኘት “ግዜው ሙስሊሞችና ክርስትያኖች አመጽ ያከትምልከት ዘንድ የሚተባበሩት ወቅት ነው” የሚል ቅዉም ሓሳብ ላይ ያተኮረ መሪ ቃል ለግሰዋል። ለሚሰቃዩት በተለይ ደግሞ ከሶሪያ ለመጡትን ወጣቶች በአገሪቱ አንዣቦ ያለው ውጥረትና ዓመጽ ጠቅሰው ለሕዝቡና ለአገሪቱ ቅርብ መሆናቸው ገልጠዋል።
በተካሄደው ግኑኝነት ፍጻሜ ቅዱስነታቸው ከሊባኖስ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ጋር በመንበረ ፓትሪያርክ በሚገኘው ፍልሰታ ለማርያም ጸሎት ቤት ውስጥ የጋራ ጸሎት በመድገም አጭር ግኑኝነት ማካሄዳቸው ሲገለጥ፣ ለወጣቶች በሰጡት መሪ ቃል፣ ጦርነት አመጽና ውጥረት እንዲያከትም ለሚደረገው ጥረት መነሻው ወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል መሆን እንዳለበት በማሳሰብም፣ በካቶሊክ ቤተ ክርስትያን በየዓመቱ ከሚዘጋጀው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጋር የሚመሳሰል የመካከለኛው ምስራቅ የወጣቶች ቀን የሚል መጠሪያ በተሰጠው ግኑኝነትም ከተሳተፉት ውስጥ አንዲት ወጣት በቅዱስነታቸው ፊት ባሰማቸው ንግግር፣ “ምንም’ኳ በክልሉ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ ቢሆንም ቅሉ በሥፍራው ቅዱስነታቸው መገኘት በመካከለኛው ምሥራቅ ላለው ለጦርነት ምርጫ አመክንዮና ተስፋ ቀቢጽነት የሚጋፈጥ የሰላምና የተስፋ ምልከት ነው” በማለት ስትገልጥ፣ ቅዱስ አባታችን ባሰሙት ቃል “ወጣቱን የክልሉ የኅብረተሰብ ክፍል ለማበረታታት የሊባኖስ ወጣቶች በጠቅላላ የመካከለኛው ምስራቅ ወጣቶች ለአካባቢያቸው የብሩህ መጻኢ ተስፋ ናቸው” ካሉ በኋላ “እንደ አገራችሁ አብነት እንደ ክርስቶስ ሁሉንም ለመቀበል የተከፈተ ልብ ይኑራችሁ፣ ሰለዚህ ህልውናችሁ ወሳኝና እጅግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።
“እናንተ ሙስሊሞችና ክርስትያን ወጣቶች የዚህ ድንቅ አገር ተስፋ ናችሁና በጋራ ለሰላምና ለስምምነት ግንባታ ንቁበማለትም የወጣቱ ብርታት የሚደነቅ መሆኑም ጠቅሰው፣ ከሶሪያ የመጡትን ወጣቶች በመመልከትም፦ ያለው ወቅታዊው ሁኔታ እግምት ውስጥ በማስገባት “ነጻና ሰብአዊነት ለተካነው ማኅበረሰብ ግንባታ እንዲነቁ’ አሳስበው፣ “ለአገራችሁና ለቤተሰቦቻችሁ ር.ሊ.ጳ. ቅርብ መሆናቸው ንገሩ፣ ሶሪያ በጸሎታቸው ትውስት መሆንዋንም አረጋግጠው፣ ያለው ዓመጽ ያከትምለትም ዘንድ ወቅቱ ሙስሊሞችና ክርስትያኖች በመተባበር ለሰላም ግንባታ አብረው የሚንቀሳቀሱበት ግዜ ነው። ስለዚህ በተስፋ መቁረጥ በመደናገርና ፍርሃት ተሰናክለው ለተለያዩ አደንዛፅ እጸዋት እጃቸውን ከመስጠት ታቅበው ለክርስቶስ ፍቅር ክፍት በመሆን የፍቅሩ አብሳሪዎች ለመሆን ትጉ” ካሉ በኋላ ቤተ ክርስትያን ከጎናችሁ ነች በእናንተ ላይ ተስፋ አላት” ሲሉ የሰጡት መሪ ቃል እንዳጠቃልሉ ለማወቅ ሲቻል፣ ይህ በእንዲህ እንዳለም በዚሁ ግኑኝነት ለመሳተፍ በኪርኩክ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ልዊስ ሳኮ የተሸኙት የኢራቅ ወጣቶች መሳተፋቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ብፁዕነታቸው ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄዱት ቃለ ምልልስ “ወጣት መጻኢነትን የሚወክል አካል ነው፣ ሰለዚህ የቤተ ክርስትያን የአገር የኅብረሰብ መጻኢ በእነርሱ የሚወከል ነው” ብለዋል።
“ቤተ ክርስትያን እናት እንደ መሆንዋ መጠን፣ ይኸንን የእናትነትዋ ባህርይ በሁሉም ብፁዓን ጳጳሳት በእረኛነት መንፈስ እየተኖረ መገለጥ ያለበት በመሆኑም፣ ብፁዓን ጳጳሳት ከህብረተሰብ ውጭ ተገለው ሳይሆን፣ በኅብረተሰብ ውስጥ የሚኖሩ ናቸው። ወጣቱን የማዳመጥና የመደገፍ ኃላፊነት አለባቸው። “በኢራቅ ያለው ሁኔታ አጅግ አስቸጋሪ በመሆኑም የአገሪቱ ማኅበረ ክርስትያን በተለይ ደግሞ ወጣቱ የኢራቅ ክፍለ ኅብረሰብ አገሩን ጥሎ ለመሰደድ የተገደደበት ሁኔታ ሆኖ እንደሚገኝ ህብዝ ተስፋ ቆርጦ ምንም አይነት ተጨባጭ ለውጥ ለማየት የማይችልበት እያደረገው ያለው የጸጥታና የደህንነት መጓደል ለስደት ምርጫ አስገዶት ይገኛሉ” ብለዋል።
ከቅዱስ አባታችን ጋር የተካሄደው ግኑኝነት ያሰጠውና የቀሰቀሰው ተስፋ በግኑኝነት ጊዜ ታጥሮ የሚቀር እንዳልሆነም ሲያመልክቱ፣ “ሙስሊሞችና ክርስትያኖች በጋራ በመሥራት ወጣቱ የመካከለኛው ምስራቅ ካለው የክልሉ ሕዝብ ብዛት አንጻር ሲታይ 95% የሚሸፍን ነው። ስለዚህ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል በማነቃቃት ወጣቱን የሰላም ገንቢ ማድረግ ለሰላም ግንባታ ማፋጠን መሠረት ነው። ወጣቱ መደገፍና መርዳት እንዲሁም ማነጽ አገርን መገንባትና መደገፍ ማለት ነው” ብለዋል።
በተካሄደው ግኑኝነት ለመሳተፍ ከግብጽ ከመጡት ወጣቶች ውስጥ አንዱ አላይን የተባለው ወጣት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባካሄደው ቃለ ምልልስ፣ ወደ ሊባኖስ በመሄድ ከቅዱስ አባታችን ጋር በመገናኘት ለመካከለኛው ምስራቅ በጠቅላላ ለዓለም የክርስቶስ ተከታዮች መሆናቸው ለመመስከር ያለመ ነው። በእውነቱ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ሁኔት እግምት ውስጥ በማስገባት ከመካከለኛው ምስራቅ አገሮች የተወጣጡ 25 ሺሕ ወጣቶች ይገኛሉ የሚል ግምት አልነበረኝም፣ ለክርስቶስ ኢየሱስ ለቅዱስ አባታችን ለቤተ ክርስትያናችን ያለን ኃይለኛው ፍቅር ስበት ምንኛ ብርቱ መሆኑ ይመሰክራል። ቅዱስ አባታችን በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የደረሱት ሐዋርያዊው ምዕዳን በክልሉ ተገኝተው ለመለገስ በመወሰናቸው ለክልሉ ማኅበረ ክርስትያን የእምነት ጽናት ለተለያዩ ሃይማኖቶች ትብብር ማነቃቂያ ነው። ቅዱስ አባታችን ለሙስሊምና ለክርስትያን ወጣቶች ያነጣጠረ የሰጡት መሪ ቃል ለመስማት መቻሉ ጸጋ ነው” ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.