2012-09-16 16:55:10

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን” (ኤፈ. 1፣3)።


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. እ.ኤ.አ. መስከረም 14 ቀን 2012 ዓ.ም. በመካከለኛው ምስራቅ ወንድሞችን በእምነት ለማጽናት ለክልሉ ብፁዓን ጳጳሳት “ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምስራቅ” በሚል ርእስ ሥር የደረሱት የድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ልገሳ ማእከል ያደረገው በሊባኖስ ያካሄዱት 24ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በርእሰ ከተማ በይሩት ማእከላዊ ሥፍራ በሚገኘው ዋተርፍሮንት አደባባይ ከ 350 ሺሕ በላይ የሚገመቱ ምእመናን በተገኙበት በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴና ሐዋርያዊው ምዕዳኑን በመለገስ አጠናቀዋል።
ቅዱሰነታቸው ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ውድ ወንድሞቼና እህቶቼ፦ “በክርስቶስ ኢየሱስ በሰማያዊ ስፍራ በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ የባረከን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን” (ኤፈ. 1፣3)። ቤተ ክርስትያን በመካከለኛው ምስራቅ ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለመካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ለመለገስ በነዚህ ቀናት በመካከላችሁ በመገኘቴ እግዚአብሔር ይመስገን። ካሉ በኋላ በአንጽዮኪያ ለማሮናዊ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ብፁዕ አቡነ በቻራይ ቡትሮስ ራይን ልባዊ ሰላምታንና ምስጋናን በማቅረብ፣ እዛው ለተገኙት የመካከለኛው ምስራቅ፣ የላቲንና የምስራቅ ሥርዓት ሥርዓት ለሚከተሉት በክልሉ ለሚገኙት ከተለያዩ በመካከለኛው ምስራቅ የምትገኘው ካቶሊክ ቤተ ክርስትያንን ወክለው ለተገኙት የካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ብፁዓን ፓትሪያርኮችና ሊቃነ ጳጳሳትና ጳጳሳትን ሰላምታን ካቀረቡ በኋላ፣ ሁሉንም በቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዙሪያ የተሰቀለውን ሞትን አሸንፎ የተነሣውን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመቀደስ እዛው የተገኙትን የመካከለኛው ምስራቅ ካቶሊካውያን ምእመናን እንዲሁም የረፓብሊካዊት ሊባኖስ ርእሰ ብሔር ሱለይማን የአገሪቱ ባለ ሥልጣናት የመንግሥት ተጠሪዎችና የተለያዩ ሃይማኖቶች መሪዎች ሰላምታን አቅርበው፥ “በዚይህች ዕለተ ሰንበት ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማንነት ‘እናንተ ማን ትሉኛላችሁ’ በሚለው ጥያቄ ላይ ያተኮረው የተነበበው የማርቆስ ወንጌል፣ ጌታችን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በፊሊጶስ ቂሣርያ ወደ አሉ መንደሮች በመሄድ ሰዎች እርሱን ማን እንደሚሉት ጥያቄ ሲያቀርብ የገዛ እራሱ ኅልውና ትርጉም ለይቶ ለማሳወቅ የመረጠው ሁነት ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በስቅለቱና በትንሣዌው የደህንነታችን ማእከል የሆነውን ሁነትና ለቤተ ክርስትያን ልደት መሠረታዊ ምክንያት ወደ ገለጠባት እየሩሳሌም በመሄድ፥ “ሰው እኔን ማን ይለኛል” (ማር.8፣ 27) በማለት ላቀረበው ጥያቄ የተሰጠው መልስ፦ “አንዳንዶች መጥምቅ ዮሐንስ ሌሎችም ኤልያስ ሌሎችም ከነቢያት አንዱ ነው” የሚል መሆኑ ቅዱስነታቸው በመጥቀስ “ዛሬ በጉዞአችን በተለያዩ አስቸጋሪ በተስፋ መቁረጥ ጎዳና ላይ እያሉ ኢየሱስን ያገኙት ለሕይወታቸው መሠረታዊ መልስ ጋር የተገናኙ ስንት ናቸው? ይህ ሁነት የእውነት መንገድ ጋር ለመግናኘት የሚፈቅድ ነው? በመንገዱ እርሱን ለመከተል የሚመርጡትና በሱታፌ ከእርሱ ጋር በሐዋርያት ማኅበረሰብ ለመኖር እነሆኝ የሚሉት የእርሱን እውነተኛው ማንነት ይገነዘባሉ። ጴጥሮስ ከእርሱ ጋር ለመኖር የመረጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የማንነት ጥያቄ፦ ‘አንተ መሲህ ነህ’ (ማር. 8፣ 29) በማለት የሰጠው መልስ የማያወላውል ትክክለኛ መልስ ቢሆንም ቅሉ ገና በቂ አልነበረም፣ ምክንያቱን አሁንም እርሱን ለመከተል የመረጡት የኃሰት ጊዚያዊ ተስፋ እንዳያስቀድሙ የእርሱ ሳይሆን ሕዝቡ የገዛ እራሱን ፍላጎት መግለጫ እንዲሆን ከሚያቀርቡት የሚያወላውል መልስ ነጻ ለማውጣት ኢየሱስ ማንነቱን በሙላት ለይቶ እቅጩን ለመግለጥ ይሻል”።
የሚቀበለው ስቃይና ከትንሣኤው በፊት የሚጋፈጠው ስቅለት ግልጽ በማድረግ እርሱ እውነት መሆኑ እንዲገነዘቡ፣ ስቃይ መከራ የሚጋፈጥ እውነተኛ መሲህ፣ ኃያል ፖለቲከኛ ነጻ እውጭ እንዳልሆነ የገዛ ሕይወቱን መሥዋዕት እስከ ማድረግ ለአብ ፈቃድ ታዛዥ አገልጋይ መሆኑ የዕለቱ አንደኛው ንባብ የትንቢተ ኢይሳያስ ላይ በማተኮር፣ ነቢዩ የሚገለጠውን የኢየሱስ ማንነት የሚያስቀድም መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ ይህ የተገለጠው ማንነት ግራ የሚያጋባ ያልተጠበቀ ሆኖ ነው የተገኘው። እርሱን ለመከተል የሚሻ ሁሉ እንደ እርሱ አገልጋይ መሆን እንደሚጠበቅበት ገሃድ በማድረግ ጴጥሮስ የኢየሱስ መሲህነት ስቃዩንና ሞትን ማእከል ያደረገውን ማንነት ለመቃወም ያሳየው ቁጣ ኢየሱስ እንደገሰጸውም አመልክተዋል።
“እርሱን ለመከተል የሥልጣን የምድራዊ ልዕልና ሳይሆን ገዛ እራስን ለመካድ ወደ ሚመራው የገዛ እራስ ሕይወት ስለ ክርስቶስና ስለ ወንጌል የሚሰዋ በመጨረሻም እውነተኛ የህይወት ድህነት የሆነውን የገዛ እራስን መስቀልን ተሸክሞ እርሱን መሸኘትን ይጠይቃል። ይኽ መንገድ ወደ ትንሣዌ ወደ እውነተኛይቱ ሕይወት የሚመራ ከእርሱ ጋር አቢይ ጥልቅ ውህደትን የሚያጎናጽፍ ነው። ይኸንን አገልጋይ የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመከተል መወሰን ለተግባሮቻችን እስትንፋስ የሆነውን ቃሉን ማዳመጥና ከእርሱ ጋር ጥልቅ ውህደት ሊኖረው ይገባል” ካሉ በኋላ አያይዘውም፣ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚጀመረው “የእምነት ዓመት” ያወጁበት ምክንያትም ሲገለጡ፣ “እያንዳንዱ ምዕመን በዚህ የልብ መለወጥ በሚጠይቀው መንገድ በታደሰ መንፈስ እንዲጠመድ” በማለት እንደሆነም ገልጠዋው፣ የእምነት ዓመት ሁሉም እምነቱንና ተአምኖተ ሃይማኖትን ልብ እንዲልና ኢየሱስ ክርስቶስንና ወንጌሉንም የመከተሉን ምርጫ እንዲያሳይል አበረታተዋል፣
ከቅዱስ ያዕቆብ መልእክት የተወሰደውን ሁለተኛው ምንባብ፣ የኢየሱስ እውነተኛ ተከታይ መሆን የሚጠይቀው ተጨባጭ ተግባር “…እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ” (ያዕ. 2፣ 18) በሚለው ቃል ሥር ቅዱስ አባታችን አብራርተው፣ ቤተ ክርስትያን አገልጋይ ክርስትያኖችም በኢየሱስ አምሳያ አገልጋዮች እንዲሆኑ መጠራታቸው ሊጣስ የማይገባው ትእዛዝ መሆኑ ቅዱስነታቸው አስገንዝበዋል።
“አገልጋይነት ለክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የማያሻማ ወሳኝ መለያ ነው ( Gv 13,15-17)” የቤተ ክርስትያንና የክርስትያኖች ጥሪ አገልጋይነት፣ እንደ ጌታችን በነጻ ለሁሉም አለ ምንም ልዩነተ እና አድልዎ አገልጋይ በመሆን የፈጸመውን አገልግሎት መኖር ማለት መሆኑ በማስገንዘብ “ሞትና ውድመትን የሚያዛምተው ዕልባት ያጣው አመጽ በተከናነበው ዓለም የሰላም የፍትህ አገልጋይ መሆን በእውነቱ ወድማማችነትና ውህደት የሰፈነበት ኅብረተሰብ ለመገንባት ሰላምንና ፍትህን ማገልገል ቅድሚያ የሚሰጠው ምርጫ መሆን እንዳለበት” ቅዱስ አባታችን ካሳሰቡ በኋላ “ወድ ወንድሞቼና እህቶቼ ጌታችን ሁሉም በሰላምና በክብር ለመኖር እንዲችሉ ለመካከለኛው ምስራቅ የሰላምና የእርቅ አገልጋዮችን ይልክ ዘንድ እጸልያለሁ፣ ሰላምና ፍትህ የዚህ ክልል ክርስትያኖች መልካም ፈቃድ ካላቸው ሰዎች ጋር ሆነው የሚሰጡት አንገብጋቢ ምስክርነት ነው”። ሁሉም በዕለታዊው ሕይወቱና ኑሮው የሰላም አገልጋይ ሆኖ እንዲገኝም ጥሪ አቅርበው፣ ሁሉም በቤተ ክርስትያን ውስጥ በቅድሚያ የእግዚአብሔርና የወንድሞች አገልጋይ መሆኑ ምሥጢረ ጥምቀት የተቀበለው ሁሉ ለሁሉም በተለይ ደግሞ ለተነጠሉት በድኽነት ጫንቃ ስር ወድቀው ለሚገኙት ሰብአዊ ክብር እንዲጠበቅለት በማገልገል ተግባር ለመጠመድ ተጠርተዋል” ብለዋል።
በመጨረሻም ቅዱስ አባታችን በሥጋና በመንፈስ የሚሰቃዩት ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን በመጥቀስ ስቃያቸው ትርጉም የሌለው እንዳልሆነና በተለይ ደግሞ አገልጋዩ ክርስቶስ ለሚሰቃዩት ሁሉ ቅርብ እንዲሆን፣ በመካከላችንም እንዳለና የፍቅሩንና ፈጽሞ የማይተወውን መሆኑንም በተጨባጭ የሚያጎሉ ሰዎች እንዲገኙም ጸልየው በክርስቶስ ተስፋ የተሞላችሁ ናችሁ በማለት ያሰሙትን ስብከት አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.