2012-09-12 14:34:29

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በመካከለኛው ምስራቅ ለእምነትና ለተስፋ ምልክት ነው።


የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በመካከለኛው ምስራቅ ክልል እ.ኤ.አ. ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ለማከናወን የወሰኑት 24ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ዑደት በማስመልከት፣ RealAudioMP3 ትላትና ጧት በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ሕንፃ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የቅዱስነታቸው የሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በመካከለኛው ምስራቅ የእምነትና የተስፋ ምልክት እንደሆነ በማበከር፣ እ.ኤ.አ. መስከረም 14 ቀን በይሩት በሚገኘው ራፊቕ ሐሪሪ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በክልሉ ሰዓት አቆጣጠር ልክ አንድ ሰዓት ከ 45 ደቂቃ እንደሚደርሱና እ.ኤ.አ. መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. ሮማ በሚገኘው ቻምፒኖ የአየር ማረፊ በሮማ ሰዓት አቆጣጠር ዘጠኝ ሰዓት ከ አርባ ደቂቃ በመግባት የሚጠቃለል መሆኑ ገልጠዋል።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የበይሩት 24ኛው ዓለም አቀፍ ሐዋርያዊ ጉብኝት ቀዳሚው ዑደት በሐሪሳ የግሪክ ሥርዓት በምትከተለው መልኪታ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ባሲሊካ፣ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር ባድባ ሕንፃ፣ በብከርከ የማሮኒታ ሥርዓት ለምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ፓትሪያርክ ሕንፃ እሁድ የሐዋርያዊ ጉብኝት ማጠቃለያ መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚያሳርጉበት ፊርማቸውን በማኖር ለመካከለኛ ምሥራቅ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሐዋርያዊ ምዕዳን የሚለግሱበት በይሩት የሚገኘው ዋተርፍሮንት ማእከል እንደሚሆን አብራርተው፣ ቅዱስነታቸው በበይሩት ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው ተጀምሮ እስከ ሚጠቃለልበት ቀን ድረስ ቆይታ የሚያደርጉበት እ.ኤ.አ. በ 1997 ዓ.ም. ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በበይሩት ሐዋርያዊ ጉብኝት ፈጽመው ወጣቶችን በመቀበል ሥልጣናዊ አስተምህሮ በለገሱበት ሐሪሳ በሚገኘው የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ውኪል ሕንፃ እንደሚሆንም አባ ሎምባርዲ ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን በይሩት በሚገኘው ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በአገሪቱ ርእሰ ብሔር በሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤትና በሕግ መወሰኛ የበላይ ምክር ቤት ሊቀ መናብርት በአገሪቱ በሚገኙት የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎች አቀባበል ከተደረገላቸው በኋላ በርእሰ ከተማይቱ የሙስሊሞችን (ሺዒቶች፣ ሱኒቶች፣ ድሩሲንና አላዊትን) ማኅበረሰብ የሌሎች ክርስትያን ማኅበርሰቦችንና የሊባኖስ አራቱ ፓትሪያርኮችን እንደሚገበኙና በፈረንሳይኛ ቋንቋ ስድስት ይፋዊ ንግግሮችን እንደሚያሰሙና በአገሪቱ ለምትገኘው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ለመለገስ አጭር ሥልጣናዊ ንግግር እንዲሁም እሁድ እኩለ ቀን ጸሎት መልአከ እግዚአብሔር ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ አጭር ሥልጣናዊ ስብከት እንደሚያሰሙ ገልጠው ምናልባትም ወደ ቫቲካን ለመመለስ ከሚነሱበት አየር ማረፊያ አሸኛኘት በሚደረግላቸው ወቅት አጭር ንግግር ያሰሙ ይሆናል ካሉ በኋላ፣ ቅዳሜ ከአገሪቱ የፖለቲካና የባህል አካላት የሃይማኖት መሪዎች ጋር ተገናኘተው፣ በዚያኑ ዕለት ማምሻውንም ከወጣቶች ጋር እደሚገናኙ ገልጠዋል።
ይህ የር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛና ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ዱካን የሚከተል የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉብኝት መሪ ቃል “Pax vobis- ሰላም ለእናንተ ይሁን” የሚል የእርግብ የወይራ ምልምል ቅርንጫፍ የክርስቶስ መስቀል ምስል አዘል የሊባኖስ አገራዊ ቀለም አረንጓዴ የተኖረበት ዓርማ መሆኑ አባ ሎምባርዲ በማስታወስ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምንም’ኳ በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት ባለበት የጸና ቢሆንም ቅሉ የሰላም የተስፋ ምልክት ለመሆንና ለክልሉ ሕዝብ ቅርብ መሆናቸው ለመመስከር ያላቸው ጽኑ ፍላጎት የሚያረጋግጥ ነው” ካሉ በኋላ “የሐውርያዊው ጉብኝት መልእክት ፖለቲካዊ ገጽታ የሌለው ከመላው የአገሪቱ የተለያየው የኅብረተሰብ ክፍል ገና ከወዲሁ የእንኳን ደህና መጡ መልእክት የተንጸባረቀበት መሆኑ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ራይ ከሁሉም ጋር በመገናኘት ያረጋገጡት መልእክት ነው።” ሲሉ የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.