2012-09-12 16:52:29

የር.ሊ.ጳሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (12.09.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ባለፈው ዕለተ ሮብ በአንደኛው የዮሐንስ ራእይ ክፍል ስላለው ጸሎት ተናግሬ ነበር፣ ዛሬ ሁለተኛውን ክፍል እንመለከታለን፣ አንደኛው ክፍል በማኅበረ ክርስትያኑ ውሳጣዊ ሕይወት ያተኮረ ሲሆን የሁለተኛው ክፍል ትኵረቱ ደግሞ ለመላው ዓለም ይመለከታል፣ እንደ እግዚአብሔር ዕቅድም ቤተ ክርስትያን በዓለም ታሪክ ትራመዳለች የእርሱም አካል ናት፣ ከአንባቢው የቀረበለትን የዮሐንስ መልእክት በማዳመጥ ላይ የነበረችው ማኅበር እንደ “የእግዚአብሔርና የክርስቶስ ካህናት” (20፤6) በሚገለጠውን በእግዚአብሔር መንግሥት መሳተፍ ዋነኛው ተልእኮአቸው መሆኑን እንደገና በመገንዘብ ለመላው ዓለም ክፍት ትሆናለች፣ እዚህ ላይ እንዴት አድርገው ለመተባበርና ለመኖር እንዲሚችሉ ባካሄዱት ጥረት ሁለት መንገዶች ይፈልቃሉ፣ አንደኛው “የክርስቶስ አስተዳደር” ብለን ልንሰይመው የምንችል የማኅበሩ አባላት ሲሆኑ ደስታ የሚሰማቸው ሲሆን ሁለተኛው ግን “የዚህ ዓለም አስተዳደር የተከተለ ጸረ መንግሥት እና ጸረ ኪዳን ሆኖ በጠላት የተጠነሰሰ” ብለን ልንሰይመው የምንችል ሰዎችን እያታለለ በክርስቶስና በእግዚአብሔር ለተፈቀደው የሚጻረር ዓለም ለመፍጠር የሚሻ ነው፣ ስለዚህ ማኅበሩ የሚኖረውን ታሪክ በጥልቀት ለማንበብ በእምነት ከሁኔታዎች ባሻገር ለመንጠቅ በመማር በእግዚአብሔር መንግሥት ዕድገት በተግባሩ ለመሳተፍና ለመተባበር መንቃት አለበት፣ የዚህ ዓይነት ንባብና ሰቂለ ኅልናዊ አስተንትኖ እንዲሁም ተግባራቸው ከጸሎት ጋር የተሳሰረ ነው፣
ከሁሉም በላቀ መንገድ ደግሞ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በአንደኛ የዮሐንስ ራእይ የጸሎት ክፍል በሚያደርገው ጥሪ ማለት ለሰባት ጊዜ ያህል “ጆሮ ያለው ሁሉ ጌታ ለቤተ ክርስትያን የሚለውን ያዳምጥ” ብሎ በሚያቀርበው ጥሪ መሠረት ማኅበሩ ወደ ሰማይ ከፍ እንዲልና ሁኔታውን በእግዚአብሔር ዓይን እንዲመለከተው ይጠየቃል፣ እዚህ ጋር ታሪኩን ለማንበብ መነሻና መድረሻ የሚሆኑን ሶስት ምልክቶች እናገኛለን፤ እነርሱም የእግዚአብሔር ዙፋን መጽሐፉ እና የእግዚአብሔር በግ ናቸው፣ (4፡1-5፡14)
የመጀመርያው የእግዚአብሔር ዙፋን ምልክት ነው፣ በዚሁ ዙፋን የተቀመጠውን አካል ሁኔታ ዮሐንስ አይገልጠውም ምክንያቱም ከማንኛውም የሰው ልጅ አገላለጽ በላይ ነውና፣ ብቻ በዚሁ አስደናቂ ፊት መገኘት የሚያስከትለውን የመልካምነትና የደስታ ስሜትን ለመጥቀስ ይችላል፣ ይህ አካል እግዚአብሔር ነው፣ ከሃሌ ኩሉ የሆነው እግዚአብሔር በሰማዩ ተዘግቶ ሊቀር አልፈልገም ነገር ግን ከሰው ልጅ ጋር ቃል ኪዳን በማድረግ ቅርቡ ሊሆን ፈለገ፤ በታሪኩ የሚሳተፍ እግዚአብሔር ነው ይህንን የሚያደርገው በምሥጢራዊ መንገድ ሲሆን እውን ነው፤ ድምጹ በመብረቅና ነጐድጓድ ምልክቶች ይቀርባል፣ በእግዚአብሔር ዙፋን ዙርያ የሚታዩ ነገሮች ብዙ ናቸው፣ አንድ ብቻ ለሆነው የታሪክ ጌታ ባለማቋረጥ ክብርና ምስጋና የሚያቀርቡ 24 ካህናትና አርባዕቱ እንስሳ ይታያሉ፣
ሁለተኛው ምልክት ወደፊት በሚሆኑ ነገሮችና በሰው ልጆች የሚፈጸመውን የእግዚአብሔር ዕቅድ ይዞ የሚገኝ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ እና ማንም ሊያነበው የማይችለው መጽሐፉ ነው፣ እንዲህ ባለው የእግዚአብሔር ዕቅድ መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ ዮሐንስ እስኪያለቅስ የሚያደርገው ጥልቅ አዘን ይሰመዋል፣ ሆኖም ግን የዚህ ታሪክ ምሥጢር የሚያነብብ በታጣበት ጊዜ አንድ መካካሻ መንገድ ይገኛል መጽሐፉን ሊዘረጋና ሊያነች የሚችል አንድ አካል ይገኛል፣
እዚህ ጋር ነው ሶስተኛው ምልክት የሚመጣው እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል መሥዋዕት የቀረበው የእግዚአብሔር በግ ነው፣ ሆኖም ግን የትንሣኤ ምልክት ሊያሳይ ቆሞ ይታያል፣ ቀስ በቀስ ማኅተሙን የሚከፍትና የታሪክ ጥልቅ ትርጉም የሆነውን የእግዚብሔርን ዕቅድ የሚገልጥ የእግዚአብሔር በግ የሆነው ከሙታን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስም ነው፣
እነኚህ ምልክቶች ምን ይላሉ፧ የሚያስተምሩን ነገር ካለ የታሪክንና የሕይወታችን ሁኔታዎች ለማንበብ እንድንችል ትክክለኛው መንገድ የትኛው መሆኑን ያስታውሱናል፣ ከክርስቶስ ጋር የማያቋርጥ ግኑኘት በማድረግ በግላዊና በማኅበራዊ ጸሎት ልባችንና አእምሮአችን ለእርሱ ክፍት አድርገን ፊታችን ወደ እግዚአብሔር በሚገኝበት ሰማይ ያዞርን እንደሆነ ነገሮችን በአዲስ ሁኔታ ለማየት እንማራለን እውነተኛ ትርጉማቸውንም ለማግኘት እንችላለን፣ ጸሎት ፊታችንን በእግዚአብሔር ላይ ለማኖር እንደሚፈቅድልን ክፍት መስኮት ነው፣ ይህም በሕይወት ጉዞአችን የተያያዝነው ዓላማ አቅጣጫ ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔር ፍቃድ ምድራዊ ጉዞ አችን እንዲያበራና በጦፈ መንገድና ኃላፊነታዊ በሆነ መንገድ እንድንኖረው ይረዳናል፣
ማኅበረ ክርስትያኑ ታሪክን ጥልቅ በሆነ መንገድ እንዲያነበው ጌታ እንዴት አድርጎ ይረዳቸዋል፧ ብለን የጠየቅን እንደሆነ ከሁሉም አስቀድሞ የሚኖሩትን የዛኔ ኑሮ በእውነት እንዲኖሩት በመጥራት ነው፣ መልአኩ የመጽሐፉ የመጀመርያዎቹን አራቱን ማኅተሞች ይከፈታል፣ ቤተ ክርስትያኒቱ የምትኖርበትን ዓለም ይመለከታል፣ ቤተ ክርስትያኒቱ በምትኖርበት ዓለምም የተለያዩ ጥፋቶች እንዳሉ ይገልጣል፣ የሰው ልጅ የሚፈጽማቸው ጥፋቶች ለመግዛትና ለመጨበጥ ካላቸው ፍላጎት የተነሣ እንዲሁም አንዱ ከሌላው ለመብለጥ ከሚደረግ ትግል የተነሣ እስከ መግደል የሚደርስ ዓመጽ (ሁለተኛው ማኅተም) ወይንም የሰው ልጆች የተሰጥዋቸውን ሕጎች ባለማክበር የሚነሣ የፍትሕ መጕደል (ሶስተኛው ማኅተም) ጥፋቶች ይታያሉ፣ ከእነዚህ ጋርም የሰው ልጅ የሚቀበላቸው ክፉ ነገሮች እንደ ሞት ረሃብ ሕመም (አራተኛ ማኅተም) ይታያሉ፣ በእነዚሁ ድራማቲካዊ የሆኑ ፍጻሜዎች ማኅበረ ክርስትያኑ ዘወትር ተስፋ እንዳትቈርጥ ትጠራለች፣ የጸላኤ ሠናይ ሁሉ ቻይነት የሚመስለው በእውነተኛው የእግዚአብሔር ሁሉ ቻይነት እንድሚሸነፍ በጽናት ማመን እንዳለባትም ትነገራለች፣ መል አኩ የሚከፍተው የመጀመርያው ማኅተምም የሚከተለው መል እክት ይገኝበታል፣ ዮሐንስ “አየሁም፥ እነሆም፥ አምባላይ ፈረስ ወጣ፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠው ቀስት ነበረው፥ አክሊልም ተሰጠው፥ ድልም እየነሣ ወጣ ድል ለመንሣት።”(6፡2) ብሎ ይተርካል፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ መጥሮ ነገሩን ለማመዛዘን ብቻ ሳይሆን ወዲያውኑ እንዲያሸንፈው የእግዚአብሔር ኃይል ይገባል፣ የነጭ ምልክት የድል ምልክት ነው፣ እግዚብሔር በሞት ጨለማ ውስጥ ገብቶ በመለኮታዊ ሕይወት ብርሃኑ እንዲያበራው ይህን ያህል ቅርብ ሆነ፣ በፍቅሩ እሳት እንዲያነጻው የዓለም ክፋትን በራሱ ላይ ወስደ፣ (ይቀጥላል)








All the contents on this site are copyrighted ©.