2012-09-12 14:37:59

አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የሚያነቃቃ ብርታት


በየዓመቱ በካቶሊካዊው የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበርሰብ አዘጋጅነት የሚከናወነው የሕዝቦች ግኑኝነት የተሰየመው ባህላዊ መንፈሳዊና ማኅበራዊ ጉባኤ መሠረት በሳረየቮ የተካሄደው እ.ኤ.አ. የ 2012 ዓ.ም. መርሃ ግብር ትላትና ከሰዓት በኋላ መጠናቀቁ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፍራንቸስካ ሳባቲነሊ ካጠናቀሩት RealAudioMP3 ዘገባ ለመረዳት ሲቻል፣ ይህ የሁሉም ሃይማኖት መሪዎች የባህል ተወካዮች ጭምር የሚያሳትፈው በሳራየቮ የተካሄደው የዘንድሮው የሕዝቦች የጋራው ግኑኝነት መርሃ ግብር በማስመልከት የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅበረሰብ መሥራች የኢጣልያ የማኅበራዊ ትብብርና የውህደት ጉዳይ ሚኒስትር ፕሮፈሰር አንድረያ ሪካርዲ የተካሄደው ጉባኤ ገምጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውም ልእክት ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ገልጠዋል።
የአሲዚው መንፈስ በሁሉም ሥፍራና በሕዝቦች መካከል ለማነቃቃት ያቀደው የቅዱስ ኤጂዲዮ ማኅብርሰብ ያነቃቃው ዓላማ ዘንድሮ በሳራየቮ ለማካሄድ ላሳየው ቆራጥ ፍላጎት ተጋርጦ እንደነበርና የዛሬ 20 ዓመት በፊት ኃይማኖታዊ ጎሳዊ ጥላቻ ያነሳሳው ዕልቂትና ዓመጽ በተከሰተባት በ 1986 ዓ.ም. የሁሉም ሃይማኖቶች የጋራው ውይይት ሃይማኖቶች የሰላም መሣሪያ መሆናቸው የሚያበስረው ቃል በሁሉም ስፍራ ለማስፋፋት በየዓመቱ የሚካሄደው የሕዝቦች ግኑንኘት በሳራየቮ ሲካሄድ ተስፋ መሆኑ ገልጠው፣ የሁሉም ሃይማኖቶች የሰላም ኃላፊነት የሚያነቃቃ ሃይማኖት የሰላም እንጂ የጥላቻና የአመጽ ምክንያት ፈጽሞ መሆን እንደሌለበት ብቻ ሳይሆን አመጽና ጥላቻ ጸረ ሃይማኖት ጭምር መሆኑ ዳግም የተገነዘበበት ጉባኤ ነበር ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ቦዝኒያ የጦርነት ፍራቻ ሳይሆን የባልካውያን የመጻኢ ሁነት ከኤውሮጳ ኅብረት ጋር ለሚኖረው ፖሊቲካዊ ኤኮኖሚያዊ ማኅበራዊ ግኑኝነት ላይ ያተኮረ የመጻኢ ችግር የተጋረጠባት አገር መሆንዋ በተካሄደው የሳራየቮ የሕዝቦች ግኑኝነት ጉባኤ መክፈቻ የኢጣሊያ መራሔ መንግሥት ማርዮ ሞንቲና እንዲሁም የኤውሮጳ ኅብረት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሄርማን ቫን ሮምፑይ በመገኘት ባሰሙት ንግግር የመሰከሩት ጉዳይ መሆኑ ሚኒስትር ሪካርዲ ማብራራታቸውንም ጋዜጠኛ ሳባቲነሊ ያጠናቀሩት ዘገባ ይጠቁማል።
በጉባኤው የተሳተፉት የቭርህቦስና የሳራየቮ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲላንል ቪንኮ ፑልጂች ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የተካሄደው የሕዝቦች ጉባኤ በጦርነትና በአመጽ በደማችው ከተማ የተስፋና የሰላም ምልክት መሆኑ ገልጠው፣ የሕዝቦች መቀራረብ መደጋገፍ መከባበር የሚያጎለብትና ለአገሪቱ የፖለቲካ አካላት ለውይይትና ለሰላም እቅድ የሚያነቃቃ ነው። የሕዝቦች እኩልነት የሕግ ሉአላዊነት የተረጋገጠባት አገር ግንባታ የሚያበረታታና ለዚህ ዓላማ የአገሪቱና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ድጋፍና ትብብር የጠራ ጉባኤ እንደነበርም ካብራሩ በኋላ በቦስኒያ ሄርዘጎቪና የኤውሮጳ አብነትት ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው ብለዋል።
የስደተኞችና የተጓዦች ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል አንቶኒዮ ማሪያ ቨሊዮ በበኩላቸው ባሰሙት ንግግር በቦዝኒያ ሄርዘጎቪና የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ በተመለከተ ለውህደትና ለአብሮ መኖር ድጋፍ ማእከል ያደረገ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን የሚቀርበው ሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ ያስገኘው ውጤት ጠቅሰው፣ በዚህ ማኅበራዊ ክስተት ብዙውን ጊዜ ቤተ ክርስትያን ለብቻዋ እንደምትተውና ሆኖም ግን በዚህ ሳትበገር በሕዝቦች መካከል ሰላም ለማረጋገጥና የስደተኞችና የተፈናቃዎች ሰብአዊ መብትና ክብር ጥበቃ ለወንጌል ታማኝ በሆነ ተግባር በመመስከር አቢይ አስተዋጽኦ በመስጠት ላይ ትገኛለች።
በመጨረሻም ብፁዕነታቸው በቅርቡ ዓለም አቀፍ የስደተኞችና የተፈናቃዮች ጉዳይ የሚከታተለው ማኅበር በመጥቀስም በዓለም 214 ሚሊዮን ስደተኞች እንዳሉ ገልጠው ቤተ ክርስትያን በመሠረታዊ ድጋፍ አቅርቦት ላይ ሳትታጠር ለሰላማዊ አብሮ መኖር ዓላማ ባተኮረ ሰብአዊ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ሕንጸት መሠረት ምእመናን በሚያሳትፍ እቅድ የምታቀርበው መሆኑንም ገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.