2012-09-12 14:48:07

ሶማሊያ፦ የአዲስ ርእሰ ብሔር ምርጫ


የሶማሊያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአገሪቱ ያለው የሽግግር መንግሥት ለመተካት የአገሪቱ ርእሰ ብሔር እንዲሆኑ ከትላንትና በስትያ ሓሳን ሸይክ ሞሃሙድ እንደመረጠ ሲገለጥ፣ RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከ 1991 ዓ.ም. ወዲህ የእርስ በርስ ጦርነት አመጽና ውጥረት ያልተለያት ሬፓብሊካዊት ሶማሊያን እንዲመሩ የአገሪቱ ሕዝባዊ ምክር ቤት ከእስላማዊ ወንድማማችነት ጋር ቅርበት ያላቸው የመንበረ ጥበብ መምህር የነበሩትን ሃሳን ሸይክ ሞሃሙድ በ 190 ድምጽ እንደመረጣቸው የቫቲካን ረዲዮ ጋዜጠኛ ዳቪደ ማጆረ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።
አዲሱ ርእሰ ብሔር ወዲያውኑ ከተመረጡ በኋላ ቃለ ማኅላ ፈጽመው ለሁሉም የአገሪቱ ዜጎች መልካሙን በመመኘት በሶማሊያ አዲስ የተስፋ ምዕራፍ መከፈቱ ሲያብራሩ፣ በምርጫው የተሸነፉት የሶማሊያ የቀድሞ ርእሰ ብሔር ሸይክ ሻሪፍ ሸይክ መሃመድ የአዲሱ ርእሰ ብሔር አሸናፊነት እውቅና መስጠታቸውና በአገሪቱ የሰላም ግንባታ ሂደት ቀጣይ እንደሚሆን ነው ብለዋል።
ሊመስ የተሰየመው የመልክዓ ምድር ስነ ፖለቲካ ጉዳይ ለሚከታተለው መጽሔት ጋዜጠኛ ማተዮ ጉሊየልሞ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ አዲሱ ርእሰ ብሔር በአገሪቱ የተለያዩ ክልሎችን ከሚቆጣጠሩት ቡድኖች ጋር ግኑኝነት መፍጠርና መወይየት ከሶማሊያ ጎረቤት አገሮች ጋር እንዲሁም በአገሪቱ የመከላከያ ኃይሎቻቸው ለሰላም መረጋገጥ ከተሰማሩት ጋር ጭምር ግኑኝነት መፍጠር ይኖርባቸዋል። የጸጥታው ኃይል ለአዲሱ የአገሪቱ መንግሥት ጸጥታና ደህንነት ዋስትና መሆናቸውም የታወቀ ነው፣ ስለዚህ በግኑኝነትና በውይይት ላይ የጸና ፖለቲካ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.