2012-09-10 16:00:37

መናገርንና መስማትን ከሚነሳን ኃጢአት ነጻ ለመሆን እንታገል


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እኩለ ቀን የተለመደውን የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝ ኢየሱስ የፈወሰውን ድዳና ደንቆሮ ሰው በመጥቀስ “ድዳንዎችና ደንቆሮዎች ከሚያደርገን ከኃጢአት ነጻ ለመሆን እንታገል” ሲሉ አስተምረዋል፣ ከምእመናንና ነጋድያን ጋር የመልአከ እግዚአብሔር ካስረጉ በኋላም ወደ ሊባኖስ ሊያደርጉት የታቀደው ሐዋርያዊ ጉብኝት በእግዚአብሔር ፈቃድ እንደሚከናውን ሆኖም ግን “ለዓመጽና ለፍጥጫ መታከት የለብንም” ሲሉ በመካከለኛው ምሥራቅ ያለው የሕዝብ ሥቃይ አስታውሰዋል፣ እንዲሁም በኮሎምብያ እየተካሄደ ያለው የሰላም ድርድር ስኬታም እንዲሆን አበረታትተዋል፣
ቅዱስነታቸው ለም እመናኑ በተለያዩ ቋንቋዎች ባቀረቡት የምስጋናና የሰላምታ ክፍል በፈረሳይኛ በሊባኖስ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የሚፈጥርላቸውን የተፈራረቀ ስሜት እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ከሊባኖስና አከባቢው ለሚመጡ ሕዝበ ክርስትያን ባሻገር የሊባኖስ ሕዝብንና ባለሥልጣኖቻቸውን የማግኘት አጋጣሚ ደስታ እንደሚሰጠኝ ሁሉ በዛ አከባቢ ያለውን ሁሌ ድራማዊ የሆነ ሕዝቡን ዕረፍት የማይሰጥ መጨረሻ የሌላቸውና የማያቋርጡ እጅግ አሳዛኝ የሆነ ኑሮም ያሳስበኛል” ሲሉ በሊባኖስ በሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት በጥቅምት ወር 2010 ዓም የተከናወነ የመሀከለኛው ምሥራቅ ጳጳሳት ሲኖዶስ ፍሬ የሆነው ድሕረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን ላይ ፊርማቸውን እንደሚያኖሩ ገልጠዋል፣
“በየዕለቱ ወደር በሌለው ሥቃይ ተዘፍቀው የሚገኙ እና አንዳንዴም በሚያስዝን ሁኔታ በሕይወታቸውና በቤቶሰቦቻቸው በሚዘንመው ሞት እየተቀዘፉ የሚገኙ የብዙ የመሀከለኛ ምሥራቅ ነዋሪዎች ዕክል ይገባኛል፣ ከሁሉ የሚያሳስበው ደግሞ ትንሽ ፋታና ሰላም ለማግኘት ቤተሰቦቻቸውና ንብረታቸው ጥለው በየቦታው በስደት ተብትነው የሚሰቃዩ ጉዳይ ነው፣ መፍትሄ ማግኘት ከበድ ያለ ይመስላል ሆኖም ግን “ለዓመጽና ለፍጥጫ እጃችን መስጠት የለብንም” በዚሁ ችግር ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ወገኖች በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የተደገፉ የውይይትና የዕርቅ ጥረቶች ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው መሆናቸውን መዘንጋት የለባቸውም፣ ይህም ለዞኑም ይሁን ለመላው ዓለም ሰላምና መረጋጋት አስፈላጊነትን በልብ በማኖር ነው፣ በሊባኖስ የማደርገው ሐዋርያዊ ጉብኝትም መላው መሀከለኛው ምሥራቅንም በማጠቃለል ጌታ ለሐዋርያቱ “ሰላሜን እሰጥችዋለሁ” እንዳለው በዚሁ የጌታ ሰላም ምልክት እንዲሆን እመኛለሁ” ሲሉ በዞኑ ስላለው ሁኔታ እንደሚያስቡና እንደሚጸልዩ ገልጠዋል፣
በመልአከ እግዚአብሔሩ ጉባኤ አስተምህሮ ደግሞ ኢየሱስ ድዳውንና ደንቆሮውን ልጅ ሲፈውስ ኤፋታ ተከፈት የሚል ቃል እንደነበርና ልጁ ከመፈወሱ በፊት ዝግና ብቸኛ እንደነበር ምክንያቱም ከሌሎች ጋር ለመወያየት አይችልም ነበርና ከተፈወሰ በኋላ ግን ለሌሎችና ለዓለም ክፍት ሆነ፣ በዘመናችን ግን ከሕዋሳት ሳይሆን ሌላ ዓይነት የሰው ልጅ መዘጋትና ብቸኝነት እንዳለ እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“የሰው ልጅ ዋነኛ ሁኔታን የሚመለከት ቅዱስ መጽሐፍ ልብ ብሎ የሚገልጠው የውስጥ የልብ መዘጋት ጐልቶ ይታያል፣ ኢየሱስ ሊፈውሰው የመጣው ይህንን ነው፣ ሊከፍተው ነጻ ሊያወጣውና ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ጋር ያለውን ግኑኝነት አስተካክሎ በሙላት እንዲኖር ልቡን ለመክፈት መጣ፣ “እርሱ ሥጋ የለበሰው የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ልቡ ድዳና ደንቈሮ ስለሆነ በልቡ የሚናገረውን የፍቅር ድምጽ የሆነውን የእግዚአብሔር ድምጽ ለመስማት እንዲችል እና የሰው ልጅም በበኩሉ የፍቅር ቋንቋ ለመናገር እንዲችል ከእግዚአብሔርና ከሌሎች ጋር ለመገናኘት እንዲችል ነው” ሲሉ በምስጢረ ጥምቀት ሥር ዓት የሚደረገው ካህን በምራቁ የተጠማቂው ጆሮና ልሳን በመንካት ኤፋታ ተከፈት የሚለውም ለዚህ መሆኑን አስታውሰዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.