2012-09-07 11:07:47

የር.ሊ.ጳ. ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ (05.09.12)


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፧ ዛሬ ለዕረፍት ብለን ያቋረጥነውን ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ ትምህርተ ክርስቶስ በቫቲካን እንጀምራለን፤ የጸሎት ትምህርት ቤት ብለን የጀመርነውን እና አብረን በዕለተ ትምህርተ ክርስቶስ ያስተንተነውን ትምህርት ለመቀጠል እፈልጋለሁ፣
ዛሬ በራእዩ ለዮውሐንስ ስላለው ጸሎት ለመናገር እወዳለሁ፣ እንደምታውቁት ራእዩ ለዮውሐንስ የአዲስ ኪዳን የመጨረሻ መጽሐፍ ነው፣ መጽሐፉ እጅግ ከባድ ቢሆንም ታላቅ ሃብት ይዞ ይገኛል፣ መጽሐፉ ሕያው እና መንዘፍዘፍ ከሞላበት በጌታ ቀን የተሰበሰበች የክርስትያን ጉባኤ ጸሎት ጋር ያገናኘናል (የዮሐ ራእ1፤10)፣ ጽሑፉ የሚከተለው ጥልቅ መስመርም ይህ ነው፣
አንድ አንባቢ ለማኅበሩ ከጌታ ለወንጌላዊው ዮሐንስ የተሰጠ መልእክት ያቀርባል፣ አንባቢውና ማኅበሩ የመጽሐፉ ዋና ንግግር እድገትን ያቆማሉ፣ ከመጀመርያ ጀምሮ “መጽሐፉን የሚያነብብ ሰው ብፁዕ ነው፤ የዚህ ትንቢት ቃላት የሚያዳምጡም ብፁ ዓን ናቸው (1፤3) በማለት መልካም ምኞትን ይገልጻል፣ በመካከላቸው ከሚደረግ ውይይት የጸሎት ማኅሌት ይፈልቃል፤ ይህም እስከ መገባደጃው በልዩ ልዩ ይዞቶች እንዲያሸብርቅ ያደርገዋል፣ መል እክቱን የሚያስተላልፍ አንባቢን በማዳመጥና ግብረ መልስ የሚሰጠውን ማኅበር በማዳመጥ በመታሰብ ጸሎታቸው የእኛ ጸሎት ይሆናል፣
የዮሐንስ ራእይ መጀመርያ ክፍል (1፡4-3፤22) ጸሎት በሚያሳርግ ማኅበር አማካኝነት ሦስት ተከታታይ ዝንባሌዎች ያቀርብልናል፣ የመጀመርያው (1፡4-8) በአዲስ ኪዳን ልዩ በሆነ ጭውውት ያውኑ በተሰበሰበ ማኅበርና በአንባቢው መካከል የሚዳብር ውይይት “ጸጋ እና ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን” (1፡4) በሚል ቡራኬ የሞላበት መልካም ምኞት ይናገራል፣ አንባቢው ይህ መልካም ምኞት ምንጩ የት መሆኑ በማመልከት ይቀጥላል፣ይህ ቡራኬ የመፍጠርና የማዳን ዕቅድ በኅብረት ከሚሠሩ ከቅድስት ሥላሴ ከእግዚብሔር አብ ከመንፈስ ቅዱስ እና ከኢየሱስ ክርስቶስ ይመንጫል፣ ማኅበሩ ጸጥ ብሎ ያዳምጣል፣ የኢየሱስ ስም በሚሰማበትም ጊዜ በደስታ ተሞልተውና በማቆብቆብ “ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።” (1፡4-6) የሚለውን የምስጋና ጸሎት ያሳርጋሉ፣ በክርስቶስ ፍቅር የተከለለው ይህ ማኅበር ከማእሰረ ኃጢአት ነጻ እንደሆኑና በአጠቃላይ ለእርሱ ብቻ የሚገባ የኢየሱስ ክርስቶስ መንግሥት እንደታወጀ ይሰማቸዋል፣ በጥምቀት የተሰጣት የእግዚአብሔር ህልውናን ለመላው ዓለም የማዳረስ ተልእኮን ታስታውሳለች፣ኢየሱስን በቀጥታ እየተመለከተች ይህንን የምስጋና በዓል የሰው ልጅን ለማዳን “ክብርና ኃይል” የእርሱ መሆኑን በላቀ ስሜት ትገልጣለች፣ የክርስቶስ ምስጋና ማኅሌቱን የምትደመድመዉም በመጨረሻው “አሜን” ነው፣ እነኚሁ አራት የመጀመርያ ኍልቆች ታላቅ ሃብት ያላቸው ምልክቶች ይሰጡናል፣ ጸሎታችን ከሁሉም አስቀድሞ የሚናገረን እግዚአብሔር ማዳመጥ መሆን እንዳለበት ይነግሩናል፣ በብዙ ንግግር ሰጥመን ስለምንገኝ እግዚአብሔር ለማዳመጥ ያለን ልማድ እጅግ ትንሽ ነው፣ ከሁሉም በላይ እግዚአብሔር ሊለን የሚፈልገውን ለማዳመጥ አስፈላጊውን ውሳጣዊና ውጫዊ ጸጥታን አናስከብርም፣ ከዚህም ባሻገር እነኚህ ኁልቆች የሚያስተምሩን ነገር ሁሌ የልመና ባህርይ ያለው ጸሎታችን እግዚብሔርን ስለርቅሩ ኃይል ተስፋና ደህንነት ላመጣለን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰጠን የምስጋና ጸሎት መሆን እንዳለበት ነው፣
አንባቢው እንደገና አዲስ ሃሳብ በማምጣት ማንበብ ሲጀምር በክርስቶስ ፍቅር ልቡ ለተማረከው ማኅበሩን ያገኘውን የእግዚብሔር ህልውና በሕይወታቸው እንዲያኖሩት ያሳስባቿል፣ እንዲህም ይላል “እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ።” (1፡7) የሰማያውነቱ ምልክት በሆነው በደመና ወደ ካረገ በኋላ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁ ሰማይ በወጣው መንገድ እንደግና ይመጣል፣ በዛን ጊዜ ሕዝብ ሁሉ ቅዱስ ዮሐንስ በወንጌሉ እንደሚገልጸው ያውቃታል “የወጉትን ያዩታል ይላል” (19፡37) ያኔ የመሰቀሉ ምክንያት ስለሆነው ስለ ኃጢኦቶቻቸው ያስተንትናሉ፤ ልክ በቀራንዮ ሲሰቀል እንደነበሩ ሆነው “ደረታቸውን እየመቱ(ሉቃ 23፡48) ለበላቸው ይቅሬታ እየጠየቁ ዳግም እስከሚመጣ እርሱን በመከተል ከእርሱ ጋር አንድነት እንዲፈጥሩ ይጥራሉ፣ ማኅበሩ ስለዚህ ጉዳይ በማሰላሰል “አዎ! አሜን” ይላል፣ እሺ በማለት ማኅበሩ አንባቢው ያቀረበላቸውን ጥሪ በሙላት እንደተቀበሉት ይህም እንዲሆን በመለመን ይገልጣሉ፣ ይህ ጸሎት ማኅበሩ እግዚአብሔር ባሳየው ፍቅር ማለት እስከ በመስቀል ላይ ተንጠልጥሎ ሞት ያሳየውን ፍቅር በማስተንተን እንደ ክርስቶስ ሐዋርያት በኅበረት እንዲኖሩ ይለምናሉ፣ ከእግዚአብሔርም መልስ ይመጣል “ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ። አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል” (1፡8) እግዚአብሔር የታሪክ መጀመርያና መጨረሻ ሆኖ ይገለጣል የማኅበሩ ልመናንም ተቀብሎ በልቡ ያኖራል፣ በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ነበር አለም ይኖራልም እንደባለፈው ሁሉ በዛ ጊዜና ለወድፊት እስከ ዓለም መጨረሻ ከሕዝቡ ጋር ይኖራል፣ ይህ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ነው፣ እዚህ ጋር ሌላ አስፈላጊ ነገር እንገናለን፤ ሳናቋርጥ ዘወትር የምናሳርገው ጸሎት የእግዚአብሔር በሕይወታችንና በታሪካችን መኖሩን ያሳየናል፣ ይህ የእግዚአብሔር ከእኛ ጋር መኖር እንድንኖር ያደርገናል ጨለማ በሆኑ አንዳንድ የሰው ልጅ ተግባሮችም ሳይቀር ታላቅ ተስፋ እየሰጠ ይመራናል፣ ከዚህም ባሻገር እያንዳንዱ ጸሎት በተናጠል ብቻችን የምናሳርገውም ሳይቀር አለመልስ የሚቀር መካን ወይም የሚነጠል ጸሎት የለም፣ ማንኛው ጸሎት የሕይወት ሥር ሆኖ ክርስትያናዊ ኑሮአችንን ቍርጠኞችና ንቁዎች ሆነን እንድንኖር የሚደግፍ ነው፣
(በምዕራፍ 1፡9-22) የማኅበረ ክርስትያኑ ሁለተኛው የጸሎት ደረጃ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ያለውን ግኑኝነት ጠለቅ ባለ መንገድ ሲያራቅቅ እንመለከታለን፣ ጌታ ይታያቸዋል ይናገራቸዋል በመሀከላቸው ሆኖም ይሠራል፤ ማኅበሩም በበለጠ ወደ ጌታ በመቅረብ ጸጥ ብሎ ያዳምጣል በልበ ሙሉነት በመቀበልም ግብረ መልስ ይሰጣል፣ ከአንባቢው በቀረበው መል እክት ቅዱስ ዮሐንስ ክርስቶስን በአካል እንዳገኘውና ይህንን ልዩ ት ዕይንት የተፈጸመው በፓትሞስ ደሴት ሲሆን ምክንያቱም “የእግዚአብሔር ቃልና የኢየሱስ ምስክርነት” (1፡9) እንዲሁም “የጌታ ቀን” (1፡10) የተባለችው ዕለተ ትንሣኤ የሚከበርባት እሁድ መሆኑን ይጠቅሳል፣ ቅዱስ ዮሐንስ “በመንፈስ ይወሰዳል” (1፡10)፣ መንፈስ ቅዱስ ይማርከዋል ኢየሱስን ለመቀበል የነበረውን ችሎታ ከፍ በማድረግ ያየውን እንዲጽፍ ያዘዋል፣ ጌታ በማዳመጥ የሚገኘው ማኅበር ጸሎት ቀስ በቀስ እይ ተመልከት አስተንትን በሚሉ ቃላት ተሸኝቶ አንቢባው ያቀረበልትን መል እክት በልቡ እያኖረ በማስተንተን ቃላቱን የገዛ ራሱ ያደርገዋል፣
ዮሐንስ “የመለከት ድምጽ የሚመስል ታላቅ ድምጽ” (1፡10) ይሰማል፣ ድምጹም በታናሹ አስያ ለሚገኙ “ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስትያናት” (1፡11) በእሳቸው አማካኝነትም ለሁሉም እና የሁሉ ግዜ አብያተ ክርትያናት ከእረኞቻቸው በአንድነት መልእክት እንዲልክ ያዘዋል፣ ከኦሪት ዘፀአት (20፡18) የተወሰደው “የመለከት ድምጽ የሚመስል” የሚለው አገላለጽ በደብረ ሲና ለሙሴ የተገለጠውን መለኮታዊ ሁኔታ ሲያሳስብ ከዓለማችን ባሻገር ያለው እግዚብሔር ከሰማዩ የሚናገር ድምጹን ያመለክታል፣ እዚህ ጋር ይህ ድምጽ ከሙታን ተለይቶ ለተነሣው ክርስቶስ ሲያመለክት ከእግዚአብሔር አብ ክብር በእግዚአብሔር ቃል በጸሎት ለሚገኘው ማኅበር ይናገራል፣ በዚህ ተገልጾ ዮሐንስ “ድምጹን ለማየት” ዞር ባለበት ጊዜም “ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየ፣ በመቅረዞችም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየ” (1፡12-12) ይህ የሰው ልጅ የሚለው አነጋገር ዋነኛ የዮሐንስ ቃል ሆኖ ኢየሱስ ክርስቶስን ያመለክታል፣ የወርቅ መቃርዞቹ ከበሩ ሻማዎች የሚያመለክቱት በጸሎት ሥር ዓተ አምልኮ የምትገኝ የዘመናት ሁሉ ቤተ ክርትያንን ያመለክታሉ፣ የሰው ልጅ የሆነው ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ የብሉይ ኪዳን የሊቀ ካህናት ልብስ ለብሶ በቤተ ክርስትያኑ መሀከል ይገኛል፤ በዚህም ሥር ዓት ከአባቱ ጋር የአማላጅነት ሥራውን ይፈጽማል፣ በዚሁ አምሳላዊ የዮሐንስ መልእክት በብሉይ ኪዳን እግዚአብሔርን በሚገልጹ ትዕይንት እጅግ የሚያሸብርቅ ከሙታን የተነሣ የክርስቶስ ምስል ይከተላል፣ “ራሱና የራሱ ጠጕሩ እንደ ነጭ የበግ ጠጕርና እንደ በረዶ ነጭ ነበሩ” (1፡14)፣ ይህ የእግዚአብሔር ዘለአለማውነትና ትንሣኤ ሙታንን ያመለክታል፣ ሁለተኛው ምልክት የእሳት ምልክት ነው፣ ይህም በብሉይ ኪዳን ሁለት የእግዚአብሔር ጠባዮችን ለመግለጽ ይጠቀሙት ነበር፣ አንደኛው እግዚአብሔር ከሰው ልጅ ጋር ያለውን ፍቅር ሁሌ ሕያው የሚያደርግ ቀናተኛ ፍቅሩን ሲሆን ይህ የሚያቃጥል እሳታዊ ፍቅር ከሙታን ተለይቶ በተነሣው ኢየሱስ ፊት ያሸብርቃል “ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ” (1፡14) ይላልና፣ ሁለተኛው የዚህ ምልክት ባህርይ ደግሞ “የሚበላ እሳት” (ዘዳ 9፡3) ሆኖ ክፋትን የሚያሸንፈው የማይበገር ችሎታ ነው፣ እንዲሁም ክፉ ነገርን ለመግጠምና ለማጥፋት የሚሄዱ የኢየሱስ እግሮች “በእሳት ቀንጦ እንደ ነጠረ ናስ ይመስሉ ነበር” (1፡15)፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ድምጽም “እንደ ታላቅ የፏፏቴ ውኃ ድምፅ ነበር” (1፡15)፣ ይህም ድምጽ ነቢይ ሕዝቅኤል እንደሚለው እስከ ኢየሩሳሌም የሚጓዝ “የእስራኤል አምላክ የእግዚአብሔር ክብር” ነጐድጓዳዊ ኃይል አለው (43፡2)፣ ከዛም ሌሎች ሶስት ምልክቶች ይከተላሉ፣ በዚህም ኢየሱስ ለቤተ ክርስትያኑ ምን እንደሚያደርግ ያመለክታል፣ ሁሌ በግራ እጁ አኑሮ ይጠብቃታል፣ ኢየሱስ ቤተ ክርስትያኑን በእጁ አኑሮ የመንከባከብ ምልክት እጅግ አስፈላጊ ነው፣ ቃላቱም እንደ ከሁለት በኩል ስለት ያለው ሰይፍ በኃይል ከአፉ ይወጣል፣ “ፊቱም በሙሉ እንደሚያበራ ፀሐይ ነበረ” በዚህም መለኮቱን ያሳያታል፣ ዮሐንስ ይህን አስደናቂ ራእይ ካየ በኋላ ነፍሱን ይስታል እንደ ሞተ ሰው ሆኖ በእግሩ ሥር ይወድቃል፣
ከዚህ የግልጸት ራእይ በኋላ ሐዋርያው ጌታ ኢየሱስን እፊቱ ላይ ተደቅኖ ያየዋል፣ ይናገረዋል ምንም እንደማይሆን አረጋግጦለትም እጁን በራሱ ላይ ያኖረዋል፣ ከሙታን የተነሣው የተሰቀለው ኢየሱስ መሆኑንም ራሱን ይገልጥለታል ለአብያተ ክርስትያናት መል እክት እንዲያደርስም ያዘዋል (1፡17-18)፣ ለዮሐንስ ይህ ተመኵሮ እጅግ ጥሩ አጋጣሚ ነው፤ ምክንያቱም በግርማው ፊት በቆመ ጊዜ ኅልናውን ስቶ እንደሞተ ሲወድቅ የሕይወት ጓደና የሆነው ጌታ እጁን ያኖርለታል በግራ እጁም ይሸከመዋል ለእኛም እንዲሁ ይሆናል፣ የኢይሱስ ጓደኞች ነን ስለዚህ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ ሲገለጥልን እንደዚሁ አስፈሪ አይሆንልንም ነገር ግን እንደ ከጓደኛ መገናኘት ይሆናል፣ ማኅበረ ክርስትያኑም እንደ ዮሐንስ ይህንን የልዩ ብርሃን ግኑኝነት በአንድነት ዕለት ተዕለት ከጌታ ኢየሱስ ጋር የመገናኘትን ተመኩሮ እያጣጠመች የዚሁ ግኑኘት ሃብትና እርሱ የሚያስከትለው የእያንዳንዱ የህልውና ቦታን የሚሞላ መሆኑን እያበሰሩ ደስ ብሎአቸው ያጣጥሙታል፣
በመጀመርያው የዮሐንስ ራእይ ክፍል በምናገኘው በሶስተኛ እና የመጨረሻ ደረጃ (የዮሐ ራእ 2-3) አንባቢው ሰባት ይዘቶች ያሉት መል እክት ኢየሱስ በአካል ሲናገር ያቀርብላቸዋል፣ ይህም ወደ ሰባቱ በታናሹ ኤሽያ በኤፈሶን አከባቢ ለሚገኙ አብያተ ክርስትያናት ነው፣ የኢየሱስ ንግግር በእያንዳንዱ ቤተ ክርስትያን ሁኔታ ገለጻ ይጀምራል፣ ይህ ለሁሉ ጊዜ አብያተ ክርስትያናት ይዘረጋል፣ ከዛ ኢየሱስ በእያንዳንዱ ቤተ ክርስታያን ሕይወት ውስጥ ይገባልና ያለውን ብርሃናዊና ጨለማዊ ጐናቸውን በመግለጥ “ንሥሓ ግቡ ተለወጡ” “ያለህን ጠብቅ ያዝ” “በመጀመርያ ታደርገው የነበርከውን ሥራ አድርግ” “ስለዚህ ትጋ ንስሓም ግባ” የሚል ኃይለኛ ጥሪ ያቀርባል፣ እነኚህ የኢየሱስ ንግግሮች በእምነት የተደመጡ እንደሆነ ወዲያውኑ ሊሰሩ ይጀምራሉ፣ በጸሎት ያለችው ቤተ ክርስትያንም የኢየሱስ ቃልን በመቀበል ትለወጣለች፣ ጌታ በአጽንኦት ሰባት ጊዜ “ጆሮ ያለው መንፈስ ለአብያተ ክርስትያን የሚለውን ያዳምጥ” በማለት እንደሚጠይቀው ሁላቸውም አብያተ ክርስትያናት ለመንፈስ ቅዱስ ክፍት በመሆን ጌታን ጸጥ ብለው ማዳመጥ አለባቸው፣ ማኅበረ ክርስትያኑ የጌታን መል እክት ሲቀበል መል እክቱን በማዳመጥ የመጸጸት የንስሐ የጽናት በፍቅር የማደግ እና ለጉዞ ምሪት የማግኘት መንፈስ ያደረዋል፣
ውዶቼ የዮሐንስ ራእይ በጸሎት የተጠመደች ማኅበር ያቀርብልናል፣ ምክንያቱም የኢየሱስ በመካከላችን መገኘት የሚጐለብተው ሁሌ በጸሎት ስለሆነ ነው፣ ካለማቋረጥ እና በጦፈ መንገድ እንደጸለይንበት መጠን ከእርሱ ጋር እንዋሃዳለን፣ እርሱም በእውነት በሕወታችን ውስጥ ገብቶ ደስታን ሰላም እየሰጠ ሕይወታችንን ይመራል፣ ኢየሱስን እንዳወቅነው እንዳፈቀርነውና እንደተከተልነው መጠን በጸሎት ከእርሱ ጋር ለመገናኝት ጉጉግት ያደረናል እንዲህ በማድረግም ለሕወታችን ሰላም ተስፋና ኃይል እናገኛለን፣









All the contents on this site are copyrighted ©.