2012-09-04 11:16:11

ካርዲናል ማርቲኒ ታላቅ ሰባኬ ወንጌል


የቫቲካን ረድዮ ዳይረክተር አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ የካርዲናል ማርቲኒ ዕረፍት አመልክተው በሰጡት መግለጫ የካርዲናሉ ታላቅነት በስብከተ ወንጌል ሲመለከት ሞታቸው ከለ22 ዓመታት ካገለገሉት የሚላኖ መንበረ ሊቀ ጵጵስና አልፎ በብዙ ቦታዎች ብርቱ ኃዘን እንደፈጠረ ገለጠዋል፣ ካርዲናሉ በቃል ባስተማረዋቸውና በሰበክዋቸው እንዲሁም ስፍር ቍጥር በሌለው ጽሑፎቻቸው በተለይ ደግሞ በሐዋርያዊ ግብረ ተል እኮ አቸው ባበረከትዋቸው አዳዲስ ዘዴዎች ታላቅ ሰባኤ ወንጌል መኖራቸውና ለዘመናችን ሰው እምነትን ልዩ በሆነ ችሎታ እንደመሰከሩና እንደሰበኩም አብራርተዋል፣ ይህ ልዩ ችሎታ ካርዲናሉ በቅርባቸው የነበሩም ይሁኑ በሩቅ ይከታተልዋቸው የነበሩ ሁሉ ታላቅ ግምት እንዲሰጥዋቸው ከማድረጉ ባሻገር በመላው ዓለም የሚገኙ በስብከተ ወንጌል ኃላፊነት ወንድሞቻቸው ለሆኑ ጳጳሳትም ታላቅ ምሳሌ ሆነዋል፣
የካርዲናል ማርቲኒ የትምህርት ብቃትና ማንነታቸው እንደ ኢየሱሳዊ የቅዱስ መጽሓፍ መምህር ሲገለጥ ቃለ እግዚአብሔር መነሻቸውና ለማንኛውም ነገር የሚቀርቡበት መሠረት ነበር፣ ይህም በትምህርታቸው ጉባኤዎች በሚመሩበት ጊዜ የቅዱስ ኢግንዝጽዮ ዘሎዮላ መንፈሳውነት በመከተል ሱባኤ በሚመሩበት ጊዜ ወጣቶችንና ኅጻናትን በሚኰተኰቱበትና በሚያስተምሩበት ጊዘ ሁሉንም በቃለ እግዚአብሔር ያክኑት ነበር፣
ለብዙ ዓመታት አስተማሪና መሪ በመሆን በመንበረ ጥበብ ያገለገሉትን ካርዲናል ማርቲኒ ወደ ሚላኖ መንበረ ሊቀ ጵጵስና ያዘዋወረው የብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ቆራጥ ውሳኔ ነበር፣
መምህር መሆናቸውን እስከ መጨረሻ ሳይዘነጉ በቃል በጽሑፍ ብዙ አስተምረዋል፣ እመጨረሻ ላይ በጻፉት “ጳጳስ” በሚለው መጸሓፋቸው “ጳጳስ በመሆንህ በተለያዩ ሕገጋትና ድንጋጌዎች እንዲሁም በመቅጣትና በመከልከል ም እመናን ለመምራት አታሳብ፣ ይልቁንም ውሳጣዌ እድገትህን በቅዱስ መጽሓፍ ቃላት በማነጽ ተግባርህን በቃለ ወንጌል እንዲመራ አድርግ፣ ደረቅ በሆነ የሕግ መከታተል ይልቅ እንዲህ በማድረግ ብዙ ፍሬ ታፈራለህ” ሲሉ ጽፈዋል፣ ይህ የሚያመለክተው ሕይወታቸውና ተል እኯቸውን እንዴት በቃለ ወንጌል እንደመሩ ያመልክታል ሲሉ ለአዲሱ ስብከተ ወንጌል መሠረት ጥለው እንዳለፉ ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.