2012-09-04 11:06:26

እግዚአብሔር ፍቅር ነው: ሆኖም ግን ብዙ ክርስትያኖች እንደፈሪሳውያን ያፈቅሩታል፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ በነዲክቶስ 16ኛ ትናንትና እሁድ እኩለ ቀን በካስተልጋንደልፎ ሐዋርያዊ አደራሽ ከተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን ጋር የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመጥቀስ ከአስመሳይ ሃይማኖተኘነት አደጋ የሚያድን የወንጌል ሕግን በየዕለቱ እተግባር ላይ መዋል መሆኑን አመልክተው ባለንበት ዘመን ብዙ ክርስትያኖች ፈሪሳዊ በሆነ አስመሳይነት እንደተጠቁ ገልጸዋል፣
በትክክለኛ መንገድ ካልተመላለሱ ኅሊና ዘወትር ይወቅሳል፣ ከዚህ ኅሊናዊ ወቀሳ ነጻ ለመሆን ሽፍንፍን ባለመንገድ ግላዊ ጥቅምን አስቀድሞ ከይሉኝታ ለመዳን ብዙ ሰዎች በአስመሳይነት እየተጓዙ የዚህ ዓለም ነገሮችን ሲያመልኩ ይታያሉ ብዙ ክርስትያንኖችም እንዲያው፤ ይህ ፈተና ከጥንት ጀምሮ በእግዚአብሔርና በሰው ልጅ መካከል ያለውን ግኑኝነት ለማደፍረስ ሲፈታተን የኖረ ነው፣ ቅዱስነታቸውም በትናንትናው አስተምህሮ አቸው ይህን በማመልከት መድኃኒቱም ሕገ እግዚአብሔር መከተል ነው፣ ሕገ እግዚአብሔር የሰው ልጅን ከእኔነት ነጻ አውጥሮ እውነተኛ ነጻነትና ሕይወት ባለው ኑሮ ያደርሰዋል ሲሉ እግዚብሔር በቅዱስ መጽሐፍ የሰጠን ሕግ ትርጉም እንዲህ ሲሉ ገልጠዋል፣
“ለዚህም ሕግ በቅዱስ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ጫና ወይም ጨቋኝ ቀንበር አልተመለከተም ነገር ግን እንደ ክቡር የእግዚአብሔር ስጦታ የእርሱ አባታዊ ፍቅር ምስክር በሕዝቡ አጠገብ ለመኖር የመውደዱ ፍላጎት እና ባለኪዳኑ ሆኖ በዚሁ ሕግ የፍቅር ታሪክ ለመጻፍ እንደፈለገ ያመለክታል” ብለዋል፣
አያይዘውም ቅዱስነታቸው ጥንታዊውን የእብራውያን የነጻነት ጉዞ እና ውጣ ውረድ እንደ ምሳሌ በመጥቀስ “የሰው ልጅ ልብ በእንዲህ ያለ አስተሳሰብ ከእግዚአብሔር ጋር የሚስማማ ከሆነ ምንም ችግር የለም፣ ሆኖም ግን እብራውያን እግዚአብሔር ሲሸናቸውና ሲረዳቸው እያዩ ሙሴ በሰጣቸው ሕግም እየመራቸው ችግር ላይ ወድቀዋል፣
“ችግሩ የተነሣው ሕዝቡ እግዚአብሔር በሰጣቸው ቦታ በስላም መኖር ሲጀምሩ የተሰጣቸውን ሕግ ትተው ዋስትናና ደስታ በእግዚአብሔር ሕግና ቃል ሳይሆን በሌሎች ነገሮች በሃብት በሥልጣንና ጣዖት በማመልክ ሊያገኙት ሞክረዋል እንደእውነቱ ከሆነ ግን እነኚህ ነገሮች ሁሉም የከንቱ ከንቱ ናቸው፣ እግዚብሔርን ከሕይወታቸው አወጡት፣ ምንም እንኳ ሕጉ ዘለዓለማዊ ሆኖ ቢኖር እነርሱ ግን ይህንን የሕይወት ሕግ ሌላ ትርጉም ሰጡት፣ ፈረሳውያን ይህን መለኮታዊ ሕግ እንደሽፋን ሊጠቀሙት ጀመር፣ የሕይወት ጉዞ አቸው የዚህ ተቃራኒ እያለ በሕገ እግዚአብሔር ሽፋን ግላዊ ጥቅማቸውን የሚያገኙበት ምድራዊ ኑሮና ሥልጣን የሚያካብቱበት መሣርያ አደረጉት፣ እንዲህ በማድረግም ሃይማኖት እውነተኛ ትርጉሙ አጠፋ፣ እንደ እውነቱ ከሆኑ ሃይማኖት ማለት እግዚአብሔርን በመስማት የህልውናችን እውነት የሆነው ፍቃዱን መፈጸም ነው፣ ሆኖም ግን በዚህ ፈሪሳዊ ተግባር የእግዚአብሔር ፍቃድ ሳይሆን ለገዛ ራሳቸው እንዲመቻቸውና የእግዚአብሔርን ቦታ ተክተው በክብር እንዲኖሩ ባኖርዋቸው ወግና ሥርዓት ይከተላሉ፣ ይህም ለማንኛው ሃይማኖት አደገኛ ሁኔታ ነው፣ ኢየሱስም በጊዜው ይህንን ነው ያወገዘው፣ የሚያሳዝነው ግን ይህ ፈሪሳውነት አሁንም በክርስትና ሥር ሰዶ መኖሩ ነው፣” ሲሉ ወደ እውነተኛው አምልኮ እና እግዚአብሔርን ሰምቶ ፍቃዱ በመፈጸም እውነተኛ ፍቅራችንን እንድገልጽለ አደራ ካሉ በኋላ የመል አከ እግዚአብሔር ጸሎት አሳርገዋል፣
በመጨረሻም ምእመናኑንና ነጋድያኑን በተለያዩ ቋንቋዎች ባመሰገኑበት ወቅት በፈረሳይኛ ቋንቋ ባቀረቡት ሰላምታ በቦታው ለተገኘው ሊባኖሳውያን አመስግነው በጸሎታቸው እንደሚያስብዋቸው አረጋግጠው አገራቸውን ለመጐበኘት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጠዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.