2012-08-29 15:17:44

የቅዱስ አጎስጢኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ “ቅዱስ አጎስጢኖስ ደስታን ፈለገ፣ በተሳሳተ ቦታ በመፈለጉም ሳያገኛት ቀረ፣ ተስፋ ሳይቆርጥ ፍላጋውን ሲቀጥል እግዚአብሔርን አገኘ”


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 28 ቀን 430 ዓ.ም. በሂጶ በወቅታዊቷ አልጀሪያ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ ሊቅ የቤተክርስትያን አበው የቤተ ክርስትያን ሊቅ ጳጳስ ቅዱስ አጎስጢኖስ በሰማያዊ ቤት የተወለደበት ቀን መሆኑ በቤተ ክርስትያን የታሪክ ማኅደር የተረጋገጠ ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ለዚህ አቢይ RealAudioMP3 የቤተ ክርስትያን ሊቅ ቅዱስ ሕይወት ታሪክ የፍስፍናና የቲዮሎጊያ የሥነ መንፈሳዊ ቲዮሎጊያ ጥልቅ ጥንታዊ ጽሑፎቹ ላይ ያላቸው ጥልቅና የተመሰጠ ስሜት የሚታወቅ ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው ይኸንን ቅዱስ “የሕይወት ጉዞ ጓደኛ” በማለት በተለያየ ወቅት እንደገለጡትም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
በዚህ ትላትና በኵላዊት ቤተ ክርስታያን ተዝከሮ ለዋለው የቅዱስ በዓል ምክንያት መለስ ብለን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በተለያየ ወቅት ስለ ቅዱስ አጎስጢኖስና በሥነ እውቀት ዘርፍና በሥነ ሕይወት ብሎም በዕለታዊ ሕይወቱ እውነትን ፍለጋ ያደረገው ጥልቅ ምርምርና አስተንትኖ ርእስ ዙሪያ የሰጡት አስተንትኖ ስንመለከት፦ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ላቀረቡት ይፋዊ የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ርእሰ ጉዳይ በማድረግ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ ደስታን ጠፍሮ ለመያዝ ብሎም በኪሱ አጎሩ በመቆጣጠር እፎይ ለማለት የማይታክተው ፍላጎቱን በመከተል ያደረገው ፍለጋ በወጣትነት ዕድሜው የተከተላቸው እሴቶች የሚያመለክት ሲሆን፣ ሆኖም እውነትኛ ደስታን ለመጨበጥ በተጨባጩ ዓለም ወይንም በቁሳዊ ሃብት የሚገኝ ነው በማለት እውቀቱ ሁሉ በዚሁ ዘርፍ ሲያፈስ፦ “የሚያልፈውን ቅጽበታዊ አላፊው ጊዜ ብቻ ላይ በማተኮር፣ ዘላቂውን ደስታ ለመኖር መንገድ አድርጎ ካለ ድካም ዘላቂውን በቅጽበታዊ ሁነት በመሻት የሚጨበጥ አድርጎ በማሰብ ካለ ምንም ውጣ ውረድ ጥልቅነት በሌለው መንገድ እውነትን ፈልጎ ለማግኘት ያደረገው ጥረት ፍርሃት እንዳለውና እውነት አስፈሪ መሆኑና የተከተለው መግነድ እራሱ በእውነት እንዳይገኝ በውስጠ ታዋቂነት የሚያመለክት መሆኑና ቅዱስ እጎስጢኖስ እውነትን ብዚህ መንገድ በመፈለግ መጣሩ ያመለክትልናል” በማለት አብራርተው፣ በዚህ መንገድ በመጓዝ ላይ እያለ አጎስጢኖስ ሆኖም በዚህ ሳይረካ እውነትን ለመፈለግ ካለ መታከት ሲታገል፣ እርሷን በመፈለግ ጎዳና በሚፈጽማቸው ስሕተቶች ሳይሰናከልና ተስፋም ሳይቆርጥ ፍለጋውን በመቀጠል ያንን እውነት የሆነው እግዚአብሔርን በውጫዊው ጉዳይ ላይ በሙሉ ኃይሉ ሲፈልግ ነገር ግን እያለ በውስጡ ለገዛ እራሱ እጅግ የቀረበ መሆኑ እንደተረዳውም ቅዱስ አባታችን ሲገልጡ፦ ውዶቼ ማናችንም በሚያደርገው የእምነት ጎዞ መከራና ችግር ቢያጋጥመውም በቤተ ክርስትያን ሕይወት ብዙ በማይሳተፍ ወይንም እግዚአብሔር እንደሌለ አድርጎ የሚያስብ ቢሆንም ተስፋ ሳይቆርጥ እውነትን በመፈለጉ ፍላጎት እያደገ እርሷን በገዛ እራስ መሆናዊ ውስጥና በነገሮች ጥልቅ መሆን ዘንድ ለማግኘት ሳይታክትና ሳይፈራ ፍለጋው መቀጠል እንዳለበት ቅዱስ አጎስጢኖስ በቃሉና በሕይወቱ በማስተማር፣ በዚህ ጎዳና እውነትን እንድናይና ከእርሷ ጋር እንድንገናኝም እግዚአብሔር ብርሃኑን እንደሚያድለንና ሊፈቀርና እንደሚያፈቅረን ገዛ እራሱ ፍቅር መሆኑ ሊገልጥልን በሚሻው በእግዚአብሔር የፍቅር ግለት በእርሱ ቀድመን የተፈቀርን መሆናችንን ያረጋግጥልናል” እውነትን በመፈለግ ጉዞ ብቻችን እንዳልሆን የቅዱስ አጎስጢኖስ የፍልስፍናና የቲዮሎጊያ እንዲሁም መንፈሳዊ ሕይወቱ ጽሑፎች ያረጋግጥልናል ሲሉ እ.ኤ.አ. ነሐሴ 25 ቀን 2010 ዓ.ም. ባቀረቡት የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ እንደገለጡም የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
በኢጣሊያ የቅዱስ አጎስጢኖስ ገዳማውያን ማኅበር አለቃ አባ ሉቻኖ ደ ሚኪየሊ የቅዱስ አጎስጢኖስ ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ “ወደ ውስጣችን ወደ ልባችን እንድንገባ እውነት በውስጣችን እንዳለችና በዚያ እርሷ ባለችበት ሥፍራ እግዚአብሔር እንደሚናገረን” አረጋግጦልናል። የዚህ ቅዱስ የሕይወት ጉዞ “የተወሳሰበ ጭንቀት የተሞላው እንደነበርና ጭንቀቱና የተወሳሰበው ሕይወቱ ተስፋ ሳያስቆርጠው እውነትን በመፈለግ ጎዳና መለወጥን መታደሉ” ያረጋግጥልናል። ይኽንን የመለወጥ ጎዞውም በፍልስፍናና በቲዮሎጊያ ጥናቱ በስብከቶቹ በሥነ እውቀት የተከተለውም ሥልት በቅደም ተከተል በማስቀመጥም ትልቅ መንፈሳዊ ውርሻ ትቶልናል ካሉ በኋላ የቅዱስ አጎስጢኖስ ቅዱሳት ትሩፋት ከስምንተኛው ክፍለ ዘመን አዲህ በኢጣሊያ ፓቪያ ከተማ በቅዱስ ጴጥሮስ ዘሰማየ ወርቅ ባሲሊካ ታቅቦ እንደሚገኝም አስታውሰው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠናቀዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.