2012-08-29 15:12:44

የር.ሊ.ጳ. የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ (እ.ኤ.አ. ነሐሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም.) ፦ “ክርስትያኖች አለ ምንም አድር ባይነት ወንጌላዊ እውነትን እንዲመሰክሩ”


ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ዛሬ “የክርስቶስ ፍቅር ለአድር ባይነት ገበያ አይውልም” በተሰኘው ሓሳብ ላይ በማነጣጠር የተለመደው የዕለተ ረቡዕ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ በቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ሰማእነት አብነት ያደረገ አስተምህሮ ማቅረባቸው የቅድስት RealAudioMP3 መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስነታቸው ለበጋው እረፍት ከሚገኙበት አካስተል ጋንዶልፎ ሐዋርያዊ ሕንጻ አጸደ ነሐሴ 29 በላቲን ሥርዓት የሚከበረው የቅዱስ ዮሓነስ መጥምቅ ሰማዕትነት ዝክረ ዕለት ጠቀስ በሆነው የትምህርተ ክርስቶስ አስተምሆአቸው እንዳመለከቱት፦ “ዛሬም የክርስትናው ሕይወት ዕለት በዕለት ለቃለ ወንጌል ታማኝነት ላይ የጸና ሰማዕትነትን እንዲከፈልበት ግድ ይላል፣ የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ሰማዕትነት እምነት ከእግዚአብሔር ጋር የሚጸናው ትሥሥር እራስን በመካድና በመስዋትም ሰው ለመልካምና ለእውነት ታማኝ እንዲሆን የሚያበቃው መሆኑ እንዲገነዘብ ያደርገዋል። እንደ ዮሐንስ መጥምቅ ከክፋት ከሐሰት መንፈስ ጋር ተመሳስሎ ለመኖር ምርጫ እምቢ እንድንል በእግዚአብሔር ጎን በጸሎት ጸንተን እንድንኖር ተጠርተናል። ብለዋል።
ውድ ወንድሞቼ በማለትም፦ “የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የሰማዕትነት ክብረ በዓል የዘመኑ ክርስትያን የክርስቶስን ፍቅር እውነቱንና ቃሉን ላስመሳይነት ገበያ ሳናወርድ እንድንኖር የተጠራን መሆናችን ያስታውሰናል። እውነት እውነት ነች እና ለድርድር የምትጋለጥ አይደለችም።”
በትክክል ለእውነት የሚገለጠውና የሚኖረው ፍቅር የሚጠይቀው መመዘኛ በዮሐንስ መጥምቅ ቃልና ሕይወት ምስክርነት መገለጡና ለዚህ ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ ያዛባው ዓለም የተገባ አብነት ትቶልን እንዳለፈና በእኛ ውስጥ ክርስቶስ እንዲያድግና የሕይወታችንና የተግባሮቻችን የአእምሮአችን እሳቤ መሪ ለሆነው ክርስቶስ ዕለት በዕለት ለወንጌሉ የታማኝነት ሰማዕት ሆኖ ለመገኘት የሚያስፈልገው ብርታት ዮሐንስ መጥምቅ በሕይወቱ የመሰከረ መሆኑ ቅዱስ አባታችን ሲገልጡም፦ “ለጸሎት የሚሰጠው ጊዜ የባከነ ወይንም ከምናደርገው ተግባርም ይሁን ከሐዋርያዊ ግብረ ኖልዎ አገልግሎት የተሰረቀ ጊዜ ማለት አይደለም። ታማኝ ጽኑ ተረጋግቶና ደስተኛ ሕይወት ለመኖር የሚያበቃ ኃይል የሚሰጠን እግዚአብሔር መሆኑ እንድንረዳ የሚያስችለን የጸሎት ሕይወት ብቻ ነው። ካሉ በኋላ የቅዱስነታቸውን አስተምህሮ ለመቀበል ከውጭና ከውስጥ አገር የተሰባሰቡት በብዙ ሺሕ ለሚቆጠሩት ምእመናን በተለያዩ አበይት ቋንቋዎች ያቀረቡት ትምህርተ ክርስቶስ አጠር በማድረግ ድጋሚውን በማሰማት ለሁሉም ሰላምታን አቅርበው ሐዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.