2012-08-29 15:29:37

ቤተ ክርስትያናዊ እንቅስቃሴ ለባህላዊ ዝግጁነት


እ.ኤ.አ. ነሐሴ 30 ቀን 2012 ዓ.ም. የሚጠናቀቀው በኢጣሊያ አረዞ አውራጃ በሚገኘው በካማልዶሊ ባሕታውያን ገዳም የጉባኤ አዳራሽ “ወንጌል በታሪክ ሂደት፦ የቫቲካን ሁለተኛው ጉብኤ አስተምህሮ” በሚል ጠቅላይ ርእስ ሥር ቤተ ክርስትያናዊ እንቅስቃሴ ለባህል ዝጉጅነት የተሰየመው ማኅበር ያዘጃግጀው የቲዮሎጊያ ሳምንት መርሃ ግብር እየተካሄደ መሆኑ ሲገለጥ፣ የዚህ ማኅበር ሊቀ መንበር ካርሎ ቺሮቶ RealAudioMP3 ከቫቲካን ልኡክ ጋዜጠኛ ማርኮ ጉዌራ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ የዚህ የቲዮሎጊያዊ ሳምንት ዓወደ ጥናት ማእከል ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መሆኑ ገልጠው፣ ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ኅልዮ በመንደርደር የጉባኤው አንኳር መልእክቱ ላይ በማተኮር ከታሪክ ጋር አዛምዶ በማንበብ ታሪክ ሠሪው እግዚአብሔር ታሪክ የእዚአብሔር ድርጊት በምሆኑም ወንጌል በታሪክ ሂደት በተመለከተ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ የሚሰጠው አስተምህሮ በቲዮሎጊያ መሠረት የሚያብራራ ነው።
ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ በታሪክ ሂደት ምን ማለት ነው? በታሪክ ሂደት ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ምን ይለናል? ለነዚህን ጥያቄዎች ቲዮሎጊያዊ መልስ ለመስጠት በቅድሚያ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ለቤተ ክርስትያን አካሄድ አግባብና ጠባይ አርአያ ነው። ስለዚህ ቤተ ክርስትያን ለታሪክ ለምታቀርበው ጥያቄ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ አብነትና ታሪክ የእግዚአብሔር ሥራ መሆኑ ታምኖ በዚህ መልኩም እንደ እግዚአብሔር ፍላጎት በመመራት በዚህ ረገድም በታሪክ ሂደት ተጨባጭ ምርጫዎችን ማረጋገጥ ለሚለው መሠረታዊ ሐሳብ በቲዮሎጊያ አዋቅሮ እና ተንትኖ የሚገልጥ ዓወደ ጥናት ነው ብለዋል።
በዚህ ከመላ ኢጣሊያ የተወጣጡ 150 ካቶሊካውያን ሊቃውንት እያሳተፈ ያለው የካማልዶሊ ዓወደ ጥናት ተጨባጭ ባልሆነ በቲዮሊጊያዊ ንድፈ ሓሳብ ላይ የሚያተኩር ሳይሆን ክርስትያናዊ ጥሪ ከታሪካዊ እውነታ ጋር ማለት ከሚኖርበት ታሪካዊ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የሚነጻጸርበት ነው።
ተጨባጩን ሁኔታ ማንበብ፣ ማለትም በክርስትያናዊ ዓይን ተመልክቶ በማንበብ የጊዜ ምልክቶችን በመለየት ታሪክን በምሉእነት በመገንዘብ በዚህ መልኩ ታሪክን በማንበብ በዓለማችን ለሚከሰቱት የተለያዩ ችግሮች አዳዲስ መፍትሔዎች ለማቅረብ፣ ከዚህ ቀደም ለተከሰቱት ችግሮች መፍትሔ ናቸው ተብለው ቀርበው የነበሩትን ገምግሞ ክርስትና ህዳሴ መሆኑ ከመረዳት የመነጨ ሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ መሠረት ያደረገ የታደሰ መፍትሔ ለማቅረብ የሚጥር ዓወደ ጥናት ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.