2012-08-29 15:23:41

ሊባኖስ ቅዱስ አባታችንን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ መሆንዋ የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን አረጋገጡ


ቀደም ተብሎ የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል መግለጫ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 14 ቀን እስከ መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሊባኖስ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ግብኝት እንደሚፈጽሙ አሳውቆ እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ ይኽ ሊረጋገጥ ሁለት ሳምንታት የቀረው RealAudioMP3 የቅዱስነታቸው የሊባኖስ ሐዋርያዊ ጉብኝት በአገሪቱ ሕዝብ በጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ የሊባኖስ ክርስትያን የመገናኛ ብዙሃን ያረጋግጣሉ።
ይህ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሊባኖስ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ በሊባኖስ ከፈጸመቱ ሐውርያዊ ጉብኝት ቀጥሎ ልክ በ15 ኛው ዝክረ ዓመት የሚከናወን ሲሆን፣ ለሊባኖስ ብቻ ሳይሆን ለመላ መከካለኛው ምስራቅ አቢይ ተስፋ መሆኑ ቮክስ ደ ላ ካሪተ የተሰየመወ በሊባኖስ የሚገኘው ክርስትያን ራዲዮ ጣቢያ አስተዳዳሪ ሲሞነ ሙባራክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ በአሁኑ ወቅት በሊባኖስ የሚገኙት የተለያዩ ክርስትያን የመገናኛ ብዙሃን ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በማስተዋወቅ፣ የሕይወት ታሪካቸው አስተምህሮቻቸው የፍጸሙዋቸው ዓለም አቀፍ ሐዋርይዊ ጉብኝቶችና ዓላማቸውንም በማስተዋወቅ ላይ እንደሚገኙ ካብራሩ በኋላ፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ከጥቅምት 10 ቀን እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2010 ዓ.ም. ካቶሊካዊት ቤተ ክርስታያን በመካከለኛው ምስራቅ ሱታፌና ምስክርነት፦ ‘ያመኑት ሁሉ አንድ ልብና አንዲት ነፍስ ሆነው ይኖሩ ነበር…’ (ግብረ ሓዋ. ምዕ. 4 ቍ. 32)’ ርእስ ዙሪያ ተካሂዶ የነበረው የመካከለኛው ምስራቅ ብፁዓን ጳጳሳት ሲኖዶስ መሠረት የደረሱት ድኅረ ሲኖዶስ ሐዋርያዊ ምዕዳን በመካከለኛው ምስራቅ ለምትገኘው ክቶሊካዊት ቤተ ክርስታያን ፊርማቸውን በማኖር ለመለገስ” ታልሞ የሚከናወን መሆኑና ይኽ ቅዱስ አጋጣሚም እግዚአብሔር ለመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝብ ቅርበትና አሳቢነቱን በተለያየ መልኩ የሚያብራራ ነው ብለዋል።
ይኽ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለመካከለኛው ምስራቅ ሕዝብ ጥሪና ማሳሰቢያም ነው። እርሱም በተስፋ እንድንኖር የሚጠራና በእምነት እንድንኖር የሚያሳስብ በእምነት የሚያጸና ነው። ስለዚህ በዚያ ተስፋ ዕለት በዕለት በሚፈተንበት ክልል የክልሉ ክርስትያን ማኅበረሰብ የክርስቶስ ታማኝ ምስክር እንዲሆን የሚያነቃቃ በመከባበር በትዕግሥት በመኖር የእውነተኛ ነፃነትና ሰላም ምስክሮችና የሰላም መሣሪያ ሆነን እንድንገኝ የሚያጸና ሐዋርያዊ ጉብኝት ነው።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ሐዋርያዊ ጉብኝት በመካከለኛው ምስራቅ ሰላምን ቅርብ የሚያደርግ በዚህ ክልል ባለው እልባት ባጣው ውጥረት አማካኝነት ተስፋ በዛለበትና በደከመበት ክልል ተስፋ እምነትና ፍቅር የሚያነቃቃ ኵላዊት ቤተ ክርስትያን ለዚያ ክልል ሕዝብ ምንኛ ቅርብ መሆንዋ ሕያው ምስክርነት መሆኑ ገልጠው፣ የክልሉ ክርስትያን የመገናኛ ብዙኃን የወንጌል መልእክት የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ትምህርት ያሰማሉ፣ የወንጌል መልእክትም የሰላም መልእክት ነው። ስለዚህ በተለያዩ ኃይማኖቶች መካከል የጋራው ውይይት የሚያነቃቁ በሥርጭቶቻቸው የምስልምን ሃይማኖት ተከታዮችን በመጋበዝ ሃይማኖት የሰላም መሣሪያ መሆን መሆናዊ መለያቸው እንደሆነ የሚመሰከርባቸው መሣሪያዎች ናቸው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.